ልጥፎች

ከኦክቶበር 16, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ሚዛኑ ቢጠበቅ።

  #ሚዛኑ ቢጠበቅ።   "ስለ ኃጢያትህ ንሰኃ መግባትን አትፍራ የእግዚአብሄር ቸርነቱ ብዙ ነው እያልክ፤ በኃጢያት ላይ ኃጢያት አትሥራ።"   (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭)   #ምዕራፍ ፳።   ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ ዓለም አሁን ባለበት ፈታኝ ወቅት ተባብረንም አገር ማዳን ከቻልን ዕድለኞች ነን የሚል ዕድምታ ያለው ጉልበታም ሃሳብ አንስተዋል። የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ከግሎባል ጉዳዮች ጋር አያይዘው ስጋታቸውን ገልጸዋል። አገር እንዳናጣ ዓይነት።   ጥቅስ ውስጥ ያላስገባሁት ግንቦት 7 የተስፋ ማዕከል በነበረበት ጊዜ፤ በራሴ ላይ ይደርሱ የነበሩ ወጣ ገብ ጫናወች ተነስቼ፤ በህወሃት አገዛዝ የነበረው የሰብዕዊ መብት ጥሰት ለማዳን አይደለም #ተነጣጥለን ተባብረንም ኢትዮጵያ ማዳን ከቻልን ዕድለኞች ነን የሚል ጹሁፍ በዘሃበሻ እና በሳተናው ድረ ገጽ ላይ እጽፍ ነበር።    እሳቸው የማህበራዊ ሚዲያ ደንበኛ ስላልሆኑ የእኔን ጹሁፍ ከቁጥር አስገብተው ላያነቡት አይችሉም። ትናንትም ይሁን ዛሬ እዩኝ እዩኝ የሚል ሰብዕና ፈጽሞ አይቸባቸው አላውቅም።    ጭራሽ ማህበራዊ ሚዲያማ ደጋፊወቻቸው እንጂ እሳቸው የሉም። ይሄ ጥሩ ምግባር ይመስለኛል። ተግባር ይናገር ዘንድ መፍቀድ በሳል ስልት ነው - ለእኔ። የሳቸው መንፈስ የራቃቸው ጓዶቻቸው ይፈልጓቸዋል። እሳቸው ግን በአመኑበት የፖለቲካ አቋም ውስጥ ይገኛሉ።   የሆነ ሆኖ ግንቦት 7 ይጎድልበታል ተብሎ #ተነቅሶ የሚሰነዘርበትን ሙግት ትችት በሰለጠነ ሁኔታ ዕውቅና ተሰጥቶት ቢሆን ---- ኖሮ? ያን ጊዜ ታች ያለው "እረኛ ምን አለ" የሚለው የአባቶቻችን ይተብኃል ቢያደመጥ ----- ኖሮ? ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ሌላ መልክ ይኖ...

#አትድፈሩት! (" ቃለ - ትፈርሳለችን።") "ከፈረሰ" ህሊና የመነጬ አገላለጽ። ድፍረቱ ይገርመኛል። #አትድፈሯት! (ቃለ - ትፈርሻለሽን።) ባታታም አይደለችም። #ዊዝደም ናትና። የት ሄደን እኛ? የማንን ጎፈሬ የምናበጥር ይመስላችኋል?

  #አትድፈሩት ! (" ቃለ - ትፈርሳለችን።") "ከፈረሰ" ህሊና የመነጬ አገላለጽ። ድፍረቱ ይገርመኛል። #አትድፈሯት ! (ቃለ - ትፈርሻለሽን።) ባታታም አይደለችም። #ዊዝደም ናትና። የት ሄደን እኛ? የማንን ጎፈሬ የምናበጥር ይመስላችኋል?    "ጥበብስ እንደ ሥሟ ናት ብዙ ሰወችም የሚያውቋት አይደሉም።" (ምሳሌ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፳፪።)   #ምዕራፍ ፳።   እጅግ በሚቀፍ ሁኔታ ደፍረው ሲናገሩት ግርም ይለኛል ቃለ - "ትፈርሳለችን"፤ ቃለ - "ትፈርሻለሽን።" አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም ውሃ በቀጠነ ቁጥር። ማጣፊያው ባጠረው ቁጥር። "ኢትዮጵያ የለችም" የሚሉ #ድዋያን አሉ። ሥሟን እንቀይራለን የሚል #ዕብን መንፈስም አለ። " አለች አትባልም " የሚሉ የፋንታዚ አርበኞች ሚዲያም አሉ። ሁሉንም እንታዘባለን።   ደፍረው ""ትፈርሳለች" ሲሉም #ቅጭጭ አይላቸውም። ሃሳቡ #ወፈፌ ሃሳብ ነው። ዘመድ ቢገኝ ወደ ጎንድ ተክለኃይማኖት ጎራ ቢባል ድንቅ ነው። ምክንያታቸው የሁሉም ወጥ ነው። #ቅናት ነው። ፈላስፊት ኢትዮጵያ የሚቀናባት አገር ናት ልክ እንደ አንድ ሰብዕ። ህጓ ኢትዮጵያ ተደፋሪ ማንነት የላትም እና። ፍጹም ተፈሪ ናት እና።   ሀ) አብይዝም ካልመራት " ትፈርሳለች " እንድትበተን የታቀደ ሃሳብ እንዳለም ይጠቋቁማል። አጤ ሚኒሊክ፤ አጤ ኃይለሥላሴ፤ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ አቶ መለስ ዜናዊ፤ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ዘመን የለገሳቸውን ተግባር ፈጽመው ሥልጣናቸውን ለቀዋል። በሞትም፤ በሽሽትም፤ በፈቃድም። ኢትዮጵያ ግን አለች። የትም አልሄደችም። አላረገችም ወይንም ወደ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ...