ልጥፎች
ከኦገስት 29, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ክፋ ሃሳብ #ይጋባል። ያገባልም።ክፋ ሃሳብ #ተጓዥም ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ክፋ ሃሳብ #ይጋባል ። ያገባልም። ክፋ ሃሳብ #ተጓዥም ነው። "የቤትህ ቀናት በላኝ።" ክፋ ሃሳብ #ይዛመታል ። ሲንቀሳቀስ #ፈጣን ነው። እንደ እኔ ዕሳቤ ከብርሃን ፍጥነትም ይቀድማል የሚል ዕምነት ነው ያለኝ። ምንም እንኳን ጥናታዊ ሥራወችን ለመከወን ሁኔታው ባያመቸኝም። የሆነ ሆኖ ክፋ ሃሳብ የሰውን ልጅ ትዳሩ አድርጎ አግብቶ የመኖር አቅም አለው። ከአንዱ ክፋ አሳቢ ተነስቶ ሌላውን ለማጥቃትም ሲነቃነቅም፦ ማለትም ክፋቱን #ለማጋባት ቀላል ፎርሙላ ነው ያለው ነው። ያም መቻቻልን፤ ታጋሽነትን ነጥቆ እያጣደፈ ከሚቀቅለው የክፋ ሃሳብ ውቅያኖስ ወስዶ ይዶላል። ክፋ ሃሳብ ማስተዋል ላይ ጫና ፈጥሮ ወደ ድርጊት ተሎ የመንቀሳቀስ አቅም አለው ብዬም አምናለሁ። ለክፋ ሃሳብ #ህግ የተፈጥሮ፤ ሰው ሠራሽ #ድንጋጌወች ፤ #ባህላዊና #ትውፊታዊ ተለምዶወች ግድ አይሰጠውም። ይሉኝታ አያውቅም። ለነገሩ ይሉኝታ ያላት ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ ናት። የሆነ ሆኖ ክፋ ሃሳብ ተጣዳፊ እና ሽሚያ ላይ ዘመኑን ሁሉ ስለሚሰዋ የማጥቃት አቅሙ ኃያል ነው። ክፋ ሃሳብ የሚንቀሳቀሰው #በቲምም ነው። የቲሙ አባላት መለያቸው #ተበቅለው የማይጠግቡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፦ አዲስ አባላትን ለማፍራት ጥድፊያቸው ለጉድ ነው። ፤ #ጦርነት አነሳሹ፤ ማንኛውም ዐይነት ወንጀል፤ #ጥላቻ ፦ ዘረኝነት፤ አግላይነት፤ ተጫኝነት እኮ የክፋ ሃሳብ የቲም አባላት ናቸው። ክፋ ሃሳብ ቁንጥንጥ እና ስክነት የነሳው ነው። ምክንያቱም ማስተዋልን ተረግጦ ተልዕኮውን ስለሚያስፈጽም። ለምሳሌ አቶ "ሀ" አቶ "ለን" ሲገድለው #ገዳዩ #ክፋ #ሃሳብ ነው። አዝማቹ ክፋ ሃሳብ ነው። አቶ #ሐመርኋ አቶ ...