ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · እፍታ። ጤናይስጥልኝ የአገሬ ቅኖች እና ቅኔዎች። እንደምን አላችሁ? ለረጅም ጊዜ ጠፋሁኝ - በምክንያት። እርግጥ ነው እሰከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ በቀንበጥ ብሎጌ እጽፍ ነበር። ከዛ ደግሞ ቀንበጥ ብሎጌ ለተወሰነ ጊዜ መሰተጓጎል ቢገጥመውም ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አድካሚ ያልሆኑ ግን በውስጤ እማምንበት አጫጭር ጹሁፎችን ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። ዕይታዬ ያመለጣችሁ ይኽውና ሊንኩ። https://www.facebook.com/pages/category/Personal-Website/Httpfbmecg-1591546727802213/ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ግን የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ ዕናቶች ዕንባ በፈቃድ ውክልና ለሚያደምጡኝ ደጋጎች መላኬን አላቆምኩኝ። አሁን ታስህሳስ ወር ነው በዚህ ወር ላይ ሰሚ የለም ክርስሚያስ ጥድፊያ ላይ ስለሆኑ ነጮቹ። ስለዚህ ታህሳስ እና ጥር አጋማሽ ረፍት ይሆናል ማለት ነው። አዲሱ ጉዳይ የማይድኑ ሃሳቦች ላይ ጊዜ ማጥፋት ትቼያለሁ። አቁሜያለሁኝ። የማይድኑ ሚዲያዎችንም አላዳምጥም። ስለዚህ ሙግቱ ቀንሷል ማለት ነው። ሌላ በልቤ ሙዳይ የነበሩ ወገኖቼ ሲያዛልጣቸው ባይም ልወቅሳቸው ግን አልደፈርኩኝም። ስለምን? መብታቸው ስለሆነ። እርግጥ ነው በልቤ ያላቸውን ቦታ እንዳያጡ ባላዳምጣቸው ስለሚሻል አቅሜን ቆጥበውልኛል። እንዳከበር...