‹‹የም የፈውስ ምድር›› ይሉታል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በርካታ ባህላዊ መድኃኒቶች ስለሚገኙበት እንደሆነ ይወሳል፡፡ Reporter.
‹‹የም የፈውስ ምድር›› ይሉታል፡፡ ይህን ስያሜ ያገኘውም በርካታ ባህላዊ መድኃኒቶች ስለሚገኙበት እንደሆነ ይወሳል፡፡ https://www.ethiopianreporter.com/135050/ "በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ውስጥ የሚገኘው ቦር ተራራ ዋነኛው የመድኃኒት ምንጭ በመሆኑ የየም ብሔረሰብ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን ባህላዊ የመድኃኒት ለቀማ ያካሂዳል፡፡ ‹‹ሳሜታ›› ብለው የሚጠሩትን ሥርዓት ከአዋቂ እስከ ሕፃን ይሳተፉበታል፡፡" "ዘንድሮም ይኸው የለቀማ ሥርዓት በዕለተ ቀኑ የተከናወነው፣ በየም ልዩ ወረዳ ፎፋ ከተማ በሚገኘውና የቦር ተራራ መሆኑን ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡" የባህል መድኃኒት ለቀማ በቦር ተራራ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ተካሂዷል ‹‹በየዓመቱ ጥቅምት 17 በየም ማኅበረሰብ ዘንድ ልዩ ትኩረት የሚሰጥበት ቀን ነው፡፡ በአብዛኛው ኅብረተሰብ ዘንድ ልዩ ግምት የሚሰጥበት ምክንያት ለጤና ጠንቅ የሆነውን በሽታ ለመከላከልና ለማስወገድ ሲባል በባህላዊ መንገድ ጤንነትን የመጠበቅ ዘዴ ከጥንት ጀምሮ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ በመሆኑ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማው፣ ቅመማውና ሕክምናው በስፋት በብሔረሰቡ ውስጥ ሠርፆ የቆየ አገር በቀል ዕውቀት ነው፡፡›› ይህን ትውፊታዊ ሥርዓት የገለጸው ‹ቪዚት የም› የተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ነው፡፡ በመጣጥፉ እንደተገለጸው፣ በዞኑ ውስጥ የባህል መድኃኒት ከዕፀዋት (ቅጠላ ቅጠሎች፣ ስራስሮች፣ ቅርፊቶችና ከመሳሰሉት) ለቀማ የሚደረግበትና የተለቀመው ወደ መኖሪያ ሰፈር (ቤት) ተወስዶ ለሰውና ለቤት እንስሳት የሚሆን መድኃኒት ተለይቶ ይቀመማል፡፡ የተቀመመው መድኃኒት በንፁህ ዕቃ ተቀምጦ እስከ መጪው ዓመት ድረስ አገልግሎት ይ...