ልጥፎች
ከኦገስት 9, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ክብርህ እየሸሸህ ሲሄድ የመሪነት ወንበርህ መሸርሸሩን አስበህ ከታበይክበት መንበር ወርደህ ሱባኤ ግባ። 09.08.2019
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
በቀይ የደም ሴል አፈጣጠር ግጭት እንደሌለው ሁሉ በኢትዮጵያዊነት ማንነት እና አማራነት ግጭት የለም። ተፈጥሮዋዊ ነውና። አማራ መሆኔን እወደዋለሁ፣ ሐሤትም አገኝበታለሁ። የዕድምታው ቅኔ ቃና በሱባኤ፣ በድዋ የተቃኘው ሚስጢር ሽልማቱ ወደርየለሽ ማንጠግቦህ ስለሆነ። በዘመን የኢትዮጵያዊነት ፈተና ላይ ከጠሚሩ ጀምሮ ቁንጮዎቹ ጅራት ሆነዋል። አማራ ሰው አይደለም ከማለት ጀምሮ ብዙ መንጠራራትን አዩን፣ እነሱ ዘጭ እኛ ከፍ። ተመስገን። በኢትዮጵያዊነት ሚስጢር የቆሞሱ አማራ ቤተሰባቸው እንጂ ጠላታቸው አለመሆኑን አመሳጥረውታል። ብዙዎች ሲንጠባጠቡ ጥቂቶች ነጥረው ወጥተዋል። ተመስገን። አማራና ኢትዮጵያን መነጣጠል የማይቻልበት ሚስጢር መግቦቱ ነው። በዘመን መፈራረቅ፣ መደበላለቅ አማራና ኢትዮጵያዊነት ተቀላቅለው ሳይሆን ተዋህደው ይገኛሉ። ስለምን? አማራ አቅሙን መግቦ አበጅቶዋታልና። ለዚህ ዘመን ቀለበት ይታሰርለት የ፷ዓመታት የዜግነት ቁማር ግባዕቱ ስለተፈፀመ። ያላበለ ኢትዮጵያዊነት ጤና ነው። ያበሉት የድዌ ሽልማተኛ ናቸው። እጭጌው ሂደት ያንዘረዝራቸዋል። ኢትዮጵያዊነት ፈውስ ነው። አማራ ከኢትዮጵያ ጠረን ለሰከንድ መኖር አይችልም። እስትንፋሱ ናት። ንጹህ አየሩ። አማራ እና ኢትዮጵያ የተፈጣጠሩ ናቸው። አማራ ግቡ ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው። #አላዛሯዋ ኢትዮጵያ ክህደትን በእዮራ...