ክብርህ እየሸሸህ ሲሄድ የመሪነት ወንበርህ መሸርሸሩን አስበህ ከታበይክበት መንበር ወርደህ ሱባኤ ግባ። 09.08.2019

 በቀይ የደም ሴል አፈጣጠር ግጭት እንደሌለው ሁሉ በኢትዮጵያዊነት ማንነት እና አማራነት ግጭት የለም። 

ተፈጥሮዋዊ ነውና።

 

 አማራ መሆኔን እወደዋለሁ፣ ሐሤትም አገኝበታለሁ።

 የዕድምታው ቅኔ ቃና በሱባኤ፣ 

በድዋ የተቃኘው ሚስጢር ሽልማቱ ወደርየለሽ ማንጠግቦህ ስለሆነ።

 

 በዘመን የኢትዮጵያዊነት ፈተና ላይ ከጠሚሩ ጀምሮ ቁንጮዎቹ ጅራት ሆነዋል። 

አማራ ሰው አይደለም ከማለት ጀምሮ ብዙ መንጠራራትን አዩን፣ እነሱ ዘጭ እኛ ከፍ። ተመስገን።

 

 በኢትዮጵያዊነት ሚስጢር የቆሞሱ አማራ ቤተሰባቸው እንጂ ጠላታቸው አለመሆኑን አመሳጥረውታል። 

ብዙዎች ሲንጠባጠቡ ጥቂቶች ነጥረው ወጥተዋል። ተመስገን።

 

 አማራና ኢትዮጵያን መነጣጠል የማይቻልበት ሚስጢር መግቦቱ ነው።

 

 በዘመን መፈራረቅ፣ መደበላለቅ አማራና ኢትዮጵያዊነት ተቀላቅለው 

ሳይሆን ተዋህደው ይገኛሉ። ስለምን? አማራ አቅሙን መግቦ አበጅቶዋታልና።

 

 ለዚህ ዘመን ቀለበት ይታሰርለት የ፷ዓመታት የዜግነት ቁማር ግባዕቱ ስለተፈፀመ።

 

 ያላበለ ኢትዮጵያዊነት ጤና ነው። ያበሉት የድዌ ሽልማተኛ ናቸው። 

እጭጌው ሂደት ያንዘረዝራቸዋል።

 

 ኢትዮጵያዊነት ፈውስ ነው።

 

 አማራ ከኢትዮጵያ ጠረን ለሰከንድ መኖር አይችልም። እስትንፋሱ ናት። ንጹህ አየሩ።

 

 አማራ እና ኢትዮጵያ የተፈጣጠሩ ናቸው።

 

  አማራ ግቡ ኢትዮጵያ ናት።

 

 ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

 

 #አላዛሯዋ ኢትዮጵያ ክህደትን በእዮራዊ ፀጋዋ የምትመክት የምስባክ አገር ናት።

 

 በናቅከው ልክ ውርዴት ሳይወርህ መንገድህን መርምር። መሪነት የምርምር ማዕከልም ነውና።

 

 ውድቀትህ እንዳይፋጠን የጆሮ አይን ወደሚገኝበት የቀደምት ጥበብ ተጠጋ፣ ንቀኽው ብትኖርም ፈውሱ እዛ ነው።

 ክብርህ እየሸሸህ ሲሄድ የመሪነት ወንበርህ መሸርሸሩን አስበህ ከታበይክበት መንበር ወርደህ ሱባኤ ግባ።


 ራሱን ለገበረለት የማይሆን መሪ የህዝብ ሙሴ የመሆን አቅሙ መሃን ነው።

 የመሪ መለኪያው የእውነት አርበኝነት ብቻ ነው።

 ከጆንያ ሙሉ እብለት የነቁጥ እውነት ጉልበት አለው።

  ለውሸት ስንቀ መርህነት የተገዛ መሪ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል። ምክንያቱም ዕብለት ወዳጅ ስለሌው።

 

 ጊዜ ሲያመልጥህ ሳያማክርህ ነው።

 የመንፈስ ጥሪት ያለው ሰብዕና ከሸፍጥ ጋር ማህበር አይመሰርትም።

 ቅን ህዝብ አይጎዳም፣ በመንፈሱ ዲታ ነውና።

 የማንነት ቀውስ ላለበት ልዝ ሰብዕና እብደት ማጫው፣ ክህደት ጫጉላው ነው።

 ዉስጥህን ሳታዉቀው መሪ ለመሆን አትሰበው። በጥዋቱ ከራስህ ጋር ጦርነት ገጥመህ ትረታለህ እና።

 ከፍታን ስታስብ ሰው ሁሉ እኩል ነውን ተቀብለህ ካልሆነ የዬፌርማታውን ዳጥ አትችለውም።

 ሥልጣን ጤነኛውን ሰብዕና ወደ ተናዳፊነት የሚቀይረው በራስ መተማመኑ ሰኔል ካሰኘው ነው

 

 የሥልጣን ሱስ ሃኪምም መፈወሻም መዳህኒት የለውም።

 ሥልጣን በሽታ ሲሆን መንገዱ ዝብጥ ይሆናል።

 ምጥ አምራች ሥርዓት አፋፋ የተናደ ዕለት ወዮለት።

 

 የማንነት ቀውስ ላለበት ልዝ ሰብዕና እብደት ማጫው፣ ክህደት ጫጉላው ነው።

 ዉስጥህን ሳታዉቀው መሪ ለመሆን አትሰበው። በጥዋቱ ከራስህ ጋር ጦርነት ገጥመህ ትረታለህ እና።

 ከፍታን ስታስብ ሰው ሁሉ እኩል ነውን ተቀብለህ ካልሆነ የዬፌርማታውን ዳጥ አትችለውም።

 ሥልጣን ጤነኛውን ሰብዕና ወደ ተናዳፊነት የሚቀይረው በራስ መተማመኑ ሰኔል ካሰኘው ነው።

 የሥልጣን ሱስ ሃኪምም መፈወሻም መዳህኒት የለውም።

 

 ሥልጣን በሽታ ሲሆን መንገዱ ዝብጥ ይሆናል።

 ምጥ አምራች ሥርዓት አፋፋ የተናደ ዕለት ወዮለት።

  የፍቅር ተፈጥሮ የአመክንዮ እንጂ የቁጥር ተማሪ አይደለም።

 ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም።

 በቅብ ያረገደ ፕሮፖጋንዳ እድገቱ የዐይን ቅንድብ ነው።

 አመራር በጥዋቱ ከሻገት ማግሥት ዕዳኛ ነው።

 

 SerguteSelassie

 

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።