ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 13, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እንዲህ እንደ ጨው ዘር መበተናችን እኮ ጥቃት ነው። እዛም መከራ ተሰዶም መከራ። ግን የተሻለ ዜና ነው። "በምያንማር የወንጀል ካምፖች ተይዘው የነበሩ 138 ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ" BBC

    "በምያንማር የወንጀል ካምፖች ተይዘው የነበሩ 138 ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ" https://www.bbc.com/amharic/articles/c805zvpjnlgo     "ትናንት ከተለቀቁት የ19 ሀገራት ዜጎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ኢትዮጵያውያን ናቸው" ከ 6 ሰአት በፊት "በምያንማር በሚገኙ የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሠራተኝነት ተይዘው የነበሩ 138 ኢትዮጵያውያን ተለቅቀው ወደ ታይላንድ መግባታቸውን በሀገሪቱ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምንጮች ለቢቢሲ አማርኛ ተናገሩ። የተለቀቁት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ብዛት 138 እንደሆነ ለቢቢሲ ያረጋገጠው በሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ አስፈላጊው ሰነድ ተሟልቶላቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ ገልጿል። በደቡብ ምሥራቅ እስያዋ ምያንማር ብዛት ያላቸው የሳይበር (የበይነ መረብ) ማጭበርበር የሚከናወንባቸው ካምፖች የሚገኙባት ሀገር ነች። በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ቢያንስ 154 ግቢዎች ውስጥ የሚፈጸሙት የማጭበርበር ወንጀሎች በአብዛኛው የሚከናወኑት "የሥራ ዕድል ታገኛላችሁ" በሚል ተታልለው በግዳጅ ለዚህ ድርጊት በተዳረጉ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ነው። ከእነዚህ ዜጎች መካከልም ታይላንድ ውስጥ ሥራ ታገኛታችሁ በሚል ተታልለው ወደ ምያንማር የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። የኢትዮጵያውያኑ ተጎጂዎች ወላጆች ኮሚቴ 300 ገደማ ኢትዮጵያውያንን ስም የመዘገበ ሲሆን፣ አጠቃላይ በተለያዩ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች ቁጥር "ሦስት ሺህ ይደርሳል" ተብሎ እንደሚገመት ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኢትዮጵያውያኑ መደብደብ እና በኤሌክትሪክ ሾክ መደረግን ጨምሮ የተለያዩ የማሰቃየት ቅጣቶች ይፈጸሙባቸዋል። የኢ...