ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 15, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ባልደራስ ለኢትዮጵያ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ባልደራስ ለኢትዮጵያ እንደ አባት አደሩ ሰንበት ቅኔ ዘረፈለት። „አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ካፌ ቃል አትራቁ።“   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 5 ቁጥር 7) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·         እፍታ። እንዲህ በአጭር ጊዜ በ ባልደራስ ለኢትዮጵያ ጉዳይ እመለሳለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር። ዘለግ ያለ ሃሳቤን ስለገለጽኩኝ። ብቻ አዎን ብቻ በኽረ አጀንዳችን ይሆን ዘንድ አቅሙን በበለጠ፤ በመሰመረ ሁኔታ ገንቡለት ተባልን፤ ጥበብ ያነሳቸው ፍጥረቶች እነ ማህበረ - ኦነጋውያን። ስለሆነም ደግመህ ናብኝ ማንጠግቦህ ተበላ! እና ብራና እና ቀለም ተመሳጠሩ።  የህልውና ተጋድሎ እንዲህም መራራ ነው። እንዲህም በዬፌርማታው ቀጠሮ የሚሰጥበት አይደለም። ተግ! እስኪ በል ማለት አይቻልም። ቆራጥ ውሳኔ የሚሰጠው እረኛ ያስፈልገዋል። አዲስ አበቤ ሆይ! እንደ ተመኘሁልህ ቀንቶኃ። አይዞህ ባይ ማግኘትህ ን ዕሴትህ አድርገው። ·         በር።    እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ ተዋጥን እኮ በኦነጋውያን የድንገቴ ዝብርቅ ተውኔት። ድብልቅልቅ ያደርጉታል ሁለመናውን። የሰከነውን አዬር እራሱ ይቀኑበታል። ቀናተኛ ናቸው። የረጋውን አውደ ምህረት ቀይጠው ቀወጡት። ሱናሜ ነው የኦነጋውያን ቅይጡ ቅንጡ ንጠት ። ከቶ ተግባባን ይሆን? እኔ ለረጅም ጊዜ ስጽፍበት የባጀሁትን በቅርቡ ለዘሃበሻ ልኬለት አውጥቶት ነበር። ሊንኩን ከሥር እለጥፋለሁኝ። ጉዳዩ የፈረቃም፤ የተረኝነትም አይደለም ከዛ ያለፈ ነው ብዬ ነበር። አምቀው፤ አሽገው አጥረው ይዛዋታል ልዕልት ኢትዮጵያን በቃላት ጅዶ ከሽነው። የችግሩን የውሃ ልኩን ሳታውቅ ትግል