የሰማይ ቤት ሸንጎ አፈ ጉባኤያዊት።

አሽካካች። ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዝዬ) „አቤቱ በመከራቸው ጊዜ ፈለግሁ፣ በገሰጽሠጽሃቸው ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ። (ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፲፮“) ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን ? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘቶማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ ? ክብር ሲወድላት -- ደግሞም ሲያምርባትም የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ አገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው ? ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግ...