የማይሸመት።

      የማይሸመት።
                       ከሥርጉተ ሥላሴ 14.05.2018 
                         (ከመንኩሲቷ ሲዊዘርላንድ።)
                 „በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት 
                 ይነፋል፣ በአሦርም የጠፋ በግብጽ ምድርም 
                    የተሰደዱ ይመጣሉ፣ በተቀደሰው ተራራ 
                   በእዬሩሳሌም ለእግዚአብሄር ይሰግዳሉ።“ 
                    ( ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፫)



ናዳ አይደል። መቃብር አይደል። ገደል አይደል። ጉድጓድ አይደል። አፋፍ አይደል። ስለምን ይሆን የሰው ልጅ ቅንነትን እንደ ጦር የሚፈራው?

ስለምን ቅንነት ሲታይ ራድ ይይዘዋል። ስለምንስ ቅንነት ሲመጣ ያንዘፈዝፋዋል። ስለምን ነው የሰው ልጅ ለቅነንት ፊት ለመስጠት ጭንቅ በጭንቅ ይሆናል?

ስለምንስ የሰው ልጅ ከቅንነት ጋር አይንህ ላፈር ይላል። ስለምንስ ነው የሰው ልጅ ለቅንነት ቢላ ይስልለታል፤ ስለምንስ ያሳድደዋል?
ስለምንስ ነው ስለቅንነት በሚተጉ ቅዱሳን ላይ ጦርነት ይታዋጀል? እኮ ስለምን ቅንነት ይፈራል?

ቅንነት እኮ ገንዘብ አያስወጣም። ቅንነት አቀበት ቁልቁለት አያስወጣ አያስወርድም። ቅንነት በርካሽ የሚገኝ ምንም ቤሳ ቤስቲ የማይጣይቅ እንደ ዝናብ እውሃ በዬቤታቸን የሚደርስ በውስጧችን ያለ አብሮን የተፈጠረ ብንጠቀምበት እኛኑ የሚያጸዳ ላውንደሪ ቤት ነው።

ቅንነት ያለው ሰው ጸጸትን አያውቅውም። ስለምን የሚጸጽተው ነገር ስለማይፈጽም።

ቅንነት በመስጠት እና በመቀበል ቀመር የሌለው፤ የሂሳብ የቁጥር ተማሪ አይደለም።

ቅንነት የማያከስር ግን የሚያተርፍ የህሊናዊነት ቤተ መንበር ነው። ቅንነት ውሃ ነው ንጡህ የሆነ። ቅንነት ለሰው ልጅ እንደ ኦክስጅን የሚያስፈልገው መንገዱን የሚያቃናለት የኑሮ መሃንዲስ ነው።
ነገር ግን አጥብቀን ፈራነው። ለማስጠጋት ተጨንቅን። ለማቅረብ ተጠዬፍነው ግን ስለምን? እኮ ስለምን?

ቅንነት ያላቸው ሰዎች ፈተናቸውን የሚያሸንፉበት መሳሪያ በእጃቸው አለ። ሌላ መሳሪያ አያሰፍልጋቸውም። ህሊናቸው ዳኛ ስለሆነ መንገዳቸውን አስተካክሎ ይመራቸዋል። ከሁሉ በላይ ፈጧሪ ከእንሱ ጋር ነው።

ቅኖች የድል እርካብ ባለቤት ናቸው። መንገዳቸው እሾኽ አሜኬላ ቢጠናበትም ግን ካሰቡት መድረሳቸው ግን አይቀሬ ነው።
ቅኖች የቀን ሰዎች አይደሉም። 

ቅኖች ዘላቂ የነፍስ ሰማዕቶች ናቸው። ቅኖች ሁልጊዜ በውስጥ አንዲቀመጡ የሚፈቀድላቸው መልካምነታቸው ብቻ ነው። አይረሱም። ዘላማዊ እና ዘላቂ ናቸው። ለዛውም የመንፈስ።

ቅኖች ወስጣቸው ብርሃን ስለሆነ ብርሃነቸውን ለመለገስ ስስታም አይደሉም። በዬደረሱበት ሁሉ መክሊታቸውን ለማቅናት ቅን እና ለጋሶች ናቸው። ቅኖችን የተጠጋ ሁሉ ልምላሜ በህሊናው ውስጥ ይስፋናል። ቅኖች ተስፋ ናቸው እና። ቅኖች የተስፋ አንባሳደር ናቸው።

በቅኖች ውስጥ የሚባክን የጥሩነት ጊዜ የለም፤ በዬደረሱበት ቦታ ሀሉ ቅን ነገር ፈጽመው ሰውን ማስደሰት ነው ተልዕኳቸው ለዚህ ነው የተፈጠሩት። በቅኖች ቤት ወዳጅም ጠላትም የለም። በቅኖች ቤት ተፈጥሮ እና ሰው ብቻ ነው። ቅኖች ዬዘመኑ አዲስ የቀን መቁጠሪያ የፊደል ገበታ ናቸው።

ቅኖችን ፈጣሪ አምላካችን ይጠብቅልን አሜን።

የኔዎቹ ለምትሰጡኝ መልካም ጊዜ ኑረልኝ ልሸልም።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።