ዕውን የኢትዮጵያ የመንግሥት አደረጃጀት #ፌድራሊዝም ነውን? የት ቦታ ይሆን አማራ በቁጥሩ ልክ ውክልና ያለው። በራሱ በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ። ይህ የፋኖ #መቅድመ የመደራደሪያ አንኳር ነጥብ ሊሆን ይገባል። የፖለቲካ ውክልና #ይሉኝታ ሊገዛው አይገባም። ፈጽሞ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።" የአማራ ህዝብ ደግነቱ፤ ችግርን ተሸክሞ መኖሩ መቀጫ እንጂ መመስገኛ፤ መከበሪያ አልሆነው። አሁን ያለው ሥርዓት ለዚህ የበቃው እኮ በአማራ ድምጽ ነው። ሌሎች የተከደኑ ጥረቶች ተዘሎ። ዕውነት ለመናገር አማራ እጁ አመድ አፋሽ ነው። ምንም ያልተደረገላቸው ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ እና ወጣቱ ባለቅኔ በላይ በቀለ ለአብነት አሉ እንጂ። ለእኔ ፌድራላዊት ኢትዮጵያ አይደለም። የፌዳሪዝልም ዕውነት ያለው አማራ ክልል ብቻ ነው። የቀደመው የመለሲዝም ክልሎች፤ የዛሬ የአብይዝም ተጨማሪ ክልሎች የፌድራሊዝም ጭላንጭል የለባቸውም። ድቅድቅ ጨለማ ናቸው። ገና ፊደል ያልቆጠሩ ልሙጥ። ልግጫ ነው። ደቡብ በጆግራፊ ነው የተደራጀው። ሌላው ደግሞ በተጫኝ #ዞጎች ። ዕውነቱ ይህ ነው። አማራ ክልል አርጎባ፤ አገው፤ ኦሮሞ፤ ቅማንት ልዩ ወረዳ፤ ልዩ ዞን አላቸው። በራሳቸው የእኔ በሚሉትም አካል ይተዳደራሉ። የሚገርመው የፖለቲካ ሥልጣን ውክልናው ዞጋቸው ሌላ ሆኖ ኮታው ግን እንደ #አማራ ይወሰዳል። የነበሩት የአገር መሪወች ሁሉ ውህድ ማንነት የነበራቸው፤ ወጥም የሆኑት አጤ የኋንስን ሳይቀር አማራ የሚከሰሰው እሳቸውም አማራ እንደሆኑ ነው። ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞ ናቸው ነው የሚባለው። አጤ ኃይለሥላሴም ቅንጣቢ የላቸውም ከአማራ ነው የሚባለው፤ ግን የአማራ ገዢ መደብ ይባላል። አጤ ሚኒሊክም ውህድ ማንነት የነ...