ኧረ ተው አቤ ቱክቻው #ፋኖ #ተብዬው ትላለህን?

 May be an image of 1 person and baby

ኧረ ተው አቤ ቱክቻው #ፋኖ #ተብዬው ትላለህን?
 
 የናቁት ይወርሳል እንዳይሆም። የዕለት አጀንዳችሁ #ፋኖ ነው። ገቢያችሁም። ደግሞም #መንፈሱን #ትፈሩታሳችሁ። ለዚህም ነው ለሚዲያችሁ #ጉልላት አጀንዳ የሆነው። ማጣጣል፤ ማቃለል፤ አሳንሶ ማዬት አይገባም። ህዝባዊ ንቅናቄም ነው። ኢትዮጵያን ትወዳለህ የፋኖ ትጉኃንን፤ ፋኖን በመንፈስ የሚደግፋ ሳይለንት ማጆሪቲው እኮ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። ፋኖ፥ መነሻ መሠረቱን አባዬ ገበሬውን ንቀህ ይሆናልን???? "ጽንፈኛውም" ትላለህ። መንፈሱ ላይ ብታተኩር ይበጅ ይመስለኛል። ፋኖ መንፈሱ ንፁህ ነውና። የሚመራውም እኔ የማውቀው በጎበዝ አለቃ ነው። ተፈጥሯዊም ነው። ቢሮክራት፤ የፖለቲካ ድርጅት የፖሊት ቢሮ የለለው። ከዚህ ተፈጥሮው ከወጣ አደጋው ሰፊ ነው። ኢትዮጵያ ካለተፍጥሯዋ ሶሻሊዝምን ተሸከሚ ተብላ ነው እንዲህ ብትልትል የምትለው።
 
የሆነ ሆኖ በፋኖ ላይ አሉታዊ ሁኔታወችን ጠርቀምቀም አድርገህ በዛ ላይ ትጋትህ መብትኽ ቢሆንም ህዝባዊ ንቅናቄን አጣጥሎ ማዬት አይገባም። ለውጥ ተብዬው መነሻውም የአርበኛ ጎቤ መንፈስ፤ መዳኛውም በህወሃት ሲጠቃ ትንታጉ ፋኖ በአባት አደሩ ይተብኃል እንደመከተ ልብህ ያውቃዋል። ህወሃቶችም እንደሚፈሩት ታውቃለህ። ቢያንስ ሰማዕታቱን እንዴት ማክበር ተሳነህ? #የአብይዝም #ፋኖወችም #አሉልህ እኮ። አንድ ሰሞን ብቅ ብለው የተነኑ። ግን በስል ገብተው የሚያተራምሱ። መረጃ እዬሰጡ የሚያስመነጡሩ። የራሳቸውን ወንድሞች የሚያስጨርሱ። #እጅ #ሰጡ የሚባሉት እነሱ ናቸው። እንዲህ በወል ስታቃልላቸው ማዕዳችሁ አንድ ስለሆነ ከአብይዝም ፋኖወች ጋራ እንዳይከፋብህ። ሌላው ግን ፈጣሪ ያውቃል። እሱ ይዳኜው። እሱ ይጨመርበት። ነገም አብሮ መሥራት ሊኖር ይችላል። ማቃለል ለማግሥት አይበጅም። 
 
በተረፈ በድህነት ለመኖር ላልተፈቀደለት ህዝብ የፈጣሪ ጥበብ ይጠበቃል። ሰላም የአንድ ወገን ጥረት አይደለም። በጦርነትም አሸናፊ ከኖረ #በቀል እና #አመድ ብቻ ይሆናል። ለእኔ ጦርነት ግጥሜ አይደለም። ዝምታዬም ለዛ ነው። ቤትህ መቃብር ይሁን የተባለ ህዝብ ግን ምን ያድርግ? ሰፊው ተጠያቂነት እኮ ከፋኖ ይልቅ መንግሥትህ ሊሆን ይገባ ነበር። 
 
መንግሥት ሄደበት እንጂ ፋኖ አልመጣበት። ትጥቅ ፍቱ ለገበሬው ሰቅጣጭም አዋራጅም ክስተት ነው። እንደምን እንደታሰበ ይገርመኛል። ለዛውም የአርማጭሆ ልጅ የትዳር አጋር እያለች። ገበሬው አልታወቀም። የፖለቲካ ውክልና የለውም በባዕቱ ደግሞ መቀመጫ አጣ። ከህሊናህ ሆነህብትመረምረው በአማራ ህዝብ ላይ በዬደቂቃው ያለው መገፋት ለበሽታ ይጥላል። ለፈጣሪ ሰጥተነው እንጂ። እና ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው ሁሉ ወደ ተጋድሎው ስለሚተም ነው ዝምታዬ። እንጂ ብዙ በጣም ብዙ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የደከምኩበት አመክንዮ ነው። ዝምታዬ የሚተርፍ ነገር ከኖረ ብዬ ነው። ግድፈቱም ጥንካሬውም አዬዋለሁ። ጀማሪ ፖለቲከኛ አይደለሁም። ፕሮፖጋንዲስትም አልሻም።
 
ሙሉ 6 ዓመት የጭንቅ ቀለብ።ምን ሆነህስ ነው አቶኢሳያስ በላይ በእስር እያለ ሬሳ ተረከቡ ሲባል እንደ ሚዲያ ሰው ዝምታህ እራሱ ገርሞኛል። ጥሞና ላይ ስላልሆንክ። ብዙ በጣም ብዙ የመንግሥታችሁን ግድፈት ትዘሉታላችሁ። አሁን ጠሚሩ "ሸለፈታም።" ሲሉ ምን አልክ። የፋኖን እኮ ልቅም አድርገህ ታቀርባለህ። የአገር መሪ፤ የዓለም ሎሬት ግን ፀያፋን ቃል ሲጠቀሞ ሰይፍህ አልተሳለም። ኢትዮጵያ ለመዳን ግራቀኙን መዝኖ ማሄስ ይገባል። ከእርዕስ ጀምሮ ቸኩለህ ትንተና ታደርጋለህ። ይህም ጥሩ አይመስለኝም።
 
እማዳምጥህ ከልቤ ነው። ግን ሁሉንም አላዳምጥም። ለዛም ምክንያቴ ትርፍ አትሄድም ስለ ስለነበር። እንደገናም የመንግሥታችሁን ውስጥ ለማዬት ከምባትል አንድ ቦታ ያለውን ውስጠት መከታተሉ ይበጃል። በተስፋ ፈላጊወች በኩልም ግድፈት ብላችሁ የምታቀርቡትን ማዳመጥም ይገባል። 
 
በብዙ ነገር ዝም ነው እምለው። ብዙው ነገር ስለማይገባኝም። የህወሃት አሸኛኜትም ብዙ ተግባር ተፈፅሟል። ውለታ ቢሱ ቢደፋውም። ቢያንስ ለዕውነት መወገኑ ለህሊናም ለትውልድም ይጠቅም ነበር። ፋኖ ስለሚለው ሥያሜ፤ ስለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላም አዘውትረህ ስለምታነሳ አንድ ቀን ብመለስበት እወዳለሁ። ስለምርጫ ላነሳኽው ግን ጽፌበታለሁ። 
 
ሌላው አህቲ ሆናችሁ ስትሠሩ የነበረበት ዘመን ይናፍቀኛል። ዛሬ 12 ዕልፍኝ አላችሁ እና? አማራ ልጁን እንዲህ ያሳድጋል። ኢትዮጵያዊነትን አጠጥቶ፦ አዋህዶ። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
አቶ ወንድም አቤቾ በቀሪ ጉዳዮችም ስችል ቀን ትሞገታለህ። ኢትዮጵያን ከፋኖ ውጪ፤ ኢትዮጵያን ከአማራ ውጪ እወዳታለሁ ማለት ምን ማለት እንደሆን መርምረው። አስቸኳይጊዜ አዋጅ ለአምስተኛ ጊዜ የታወጀበት፦ ከዓለም ሥልጣኔ እንዲለይ ሙሉ ዓመት ኢንተርኔት የተዘጋበት ህዝብ እንዲያውም ታግሷል። ዲስፕሊኑ ሁልጊዜ ይገርመኛል። ኢትዮጵያዊነት ያለውን አቅምም እለካበታለሁ።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ክብሮቼ ደህና እደሩ። አቤዋ ትንሽ ተሞገተ።
 
ሥርጉትሻ 2024/05/2024
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።