አበጀ /// ሥነ ግጥም
አበጀ። „ጥበብ ቤቷን ሠራች ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።“ ምሳሌ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ሥላሴ 02.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝዬ። ተዬት መጣህ ብዬ ትዝታን ብጠይቅ? ወደዬት ነህ ብዬ ናፍቆትን ብጠይቅ? መልሶ ላከልኝ የዘመን ዝንቅንቅ። ቆልቁለት አውርጄ አሳፈሬዋለሁ ዳገቱን አግዤ መጪ … በል ብዬዋለሁ ማተብ ከተገኜ ሰጋር እልካለሁ። ዳጥ ለዳጥ ስማስን ቅንነት ሰብዤ ግራምጣ ተገኜ ተዚህ ከተከዜ። መተከዝ ሲሳነኝ ለጥርስ ተሟገትኩኝ ሳቅ መግዛትም ቻልኩኝ በቦንዳ ተኳልኩኝ። እቴ ሆይ! እናቴ አስቲ ልጠይቅሽ? ልጅሽ በ ክ ት ነው በዝርዝር መዛቅሽ። አንች ሆይ! የኔይቱ እምት እመቤት፤ ልባም ደማሚቱ የቱ ላይ ተሟላ ያነ አብነቱ? ሲሶ እርቦ ሲሉ ሟርተኞች፤ ሲያሟርቱ ዜግነት ክፋዩ የሂሳብ ስሌቱ፤ በዝቶ ቀረመቱ ተዛነፍ እንዳይሆን ገደለኝ ስጋቱ። ነገን አስባለሁ ሞጥሬ አጥንቼ፤ ተስፋ ስለሆነ እሱንም ሞግቼ፤ ነገን እንዲሰጠኝ ባክኖት‘ ረትቼ። ትውልደ - ድርሻዬ የእኔ መሆን በጀ፤ መታከት ለሁሉ እንዲህ እያባጀ፤ እያባጃ … የተዛነፍ ሚዛን አይባል አበጀ፤ ትርፉ መልካምነት ሰውነን ያበጀ። ተጣፈ አሁን 20.46 ስለምን ተጣፈ /// ልብ ለልብ አሰኝቶኝ። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። ውዶቼ ክብረቶቼ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።