ልጥፎች

ናፍቆትን መገደብ ለነፍስ ራህብተኞች ሃጢያት ነው ...

ምስል
ሳቅን፤ ናፍቆትን ለመገደብ የታደመው ዕሳቤ ወቅታዊነት ይጎድለዋል። „ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።“ ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.09.2018 ከጭምቷ ሰዊዘርላንድ። ·         የጭብጥ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=en5MiO0Tq1w #EBC   አድማ የመቱ የሲቪል አቪየሽን ሰራተኞችን በመተካት ለሰሩ ሰራተኞች እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው፤   ·        መቅድመ ነገር። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ትናንትም ዛሬም ደምኗል። ትናንትም ዛሬም ልዕልተይ የለችም። ትናንትም ዛሬም ብትጠራ ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብላ፤ ጠላታችሁ እልም ይበል እልም ብላለች። ትውር አላችም። እናም እኛ ምናችን ሞኝ ነው ደረትረት ብለን ጉብ ብለናል። ግን ያው እንደ ዳሽን ተራራ ከንፈራችን በልዕልተይ ላይ ነፋ አድርገናል።  ያካፋል፤ ያበራል፤ እንገናም ያካፋል እንደ ገናም ይባራል በቃ እንደ ወርህ ሚያዚያ ቅጥ አንባሩ ጥፍት ያለበት ቀን ነው ዛሬ። ብቻ በዚህ ዓመት የተሻለ የበጋ ጊዜ ስለነበር እንዳሻት ሙቀቷን አክስክሳናለችና አሁን ብትመጣም ብትቀርም እንደ ፍጥርጠሯ ብለናል ስለ አውሮፓዊቷ እሜቴዋ ጠሐይ። ·        የወ ግ ገበታዬን እስቲ ዘለግ አድርጌ ላስኪደው… እንዲህ … የአብዬሽን ሰራተኞች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቀም አድማ ለመምታት አቅደው ነበር። መቼም ዜናው ሲሰማ ጎሽ፤ ደግ አደረጉ ልላቻው እልቻልኩም። ምክንያቱም ወቅታዊነቱ የሴራ ይመስል ስለነበር። ስለምን ዓውዳመትን ታክኮ አድማን ለመከወን ታሰበ? እኔ የሠራተኛ ማህበር አደራጅ ነበርኩኝ።

ነፃነት ከኖረ ድል ከሃሳብ አቅም ይመነጫል።

ምስል
ሃሳብ የማያቋርጥ ጅረት ወይንም ፏፏቴ እንጂ የታቆረ የኩሬ ውሃ አይደለም! „እሱን እግዚአብሄር ስለመረጠው ጌትነቱ እንደ እጁ ሥራ ነውና ባለመድኃኒትን አክብረው።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 31.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                                   ትውልድ በፍቅር ማዋህድ የአብይ ሌጋሲ ነው!  ስለዚህም ሊከበርም- ለወደድም ደሊደነቅም ይገባል።  ነገን በፍቅር ማሰብ፤  በእዮባዊነት መቀመር መክሊቱ የእዮር ነው። ተመስገን!  43 ዓመት የተባከነበትም የተተረፈበትም፤ የተጎዳንበትም የተጠቀመንበትም ዘመን ታይቷል - ተፈትሿል። እግዚአብሄር በቃችሁ ሲለን ይህን ዘመን አመጣልን። በዚህ ዘመን ያኮረፉ እንዳሉ ይታወቃል። በዚህ ዘመን ምንም ለውጥ አልመጠም የሚሉ ወገኖችም እንዳሉ ይታወቃል። በዚህ ዘመን የተሻለ ዘመን መጥቷል የሚሉም አሉ።  በርከት ያለነው ደግሞ የተሻለ ሳይሆን የ43 ዓመቱን ዘመን የሚያስንቅ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው የምንል ደግሞ አለን። ሰዎች እንደመሆናችን ስለምን ሬድ ሜድ ሃሳብ አልኖረንም ሊባል ግን አይገባም። በሌላ በኩል መልካም ነው በርቱ የምንል አለን፤ መልካም አይደለም የነበረው ይሻል ነበር የሚሉም አሉም። ከነበረውም ከአሁንም ያልሆኑ ወገኖችም አሉ። ወለሌ ገበታ ላይ ያሉም አሉ። ይህም ቢሆን የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ስለመሆኑ ስለሚያጠይቅ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም።  በሌላ በኩል ደግሞ ፍጽና የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ፍጹም የሆነ የተባረከ መንገድ ነው የሚሉም አሉ፤ ጥቂት የማይባሉም ፍጹም ነውም አይደለም የማይሉ አባ እና እማ ዝማታዎችም አሉ። ማዕዶታችን ሰፊ ስለሆነች ሁሉንም የማስተናገድ አቅም አላትና እንደ እ

የአዲሱ ለውጥ ትሩፋት።

ምስል
መንትዮሾቹ የተግባር ልዕልቶች በደግነት      ማዕዶት! „የፃድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉቀን እስኪሆን ድረስ እዬተጨመረ ይበራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አዲሱ ለውጡ አደጋ ያመጣል የሚሉት የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከትን የኑዛዜ መስቃ እንዲህ መናነቱን ተግባር ቁሞ ይመሰክራል። የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከት ስምዖን ሙገት ቁሞቀርም መሆኑ እንዲህ ይታያል። ይህ ተግባር አላዛሯ ኢትዮጵያ የተፈጠረችበትን የደግነትን፤ የቸርነት ትውፊቷን አህዱ ብላ መጀመሯን ያሳያል። ሲጀመር ጀምሮ ለውጡ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ነው በማለት ነበር ስሞግት የባጀሁት። አዲሱ የኢትዮጵያ መንገድ ይሄውና ዛሬም የበጎ ምግባርን ተግባር ተስፋን ሰንቆልናል ... ይህ ድርጀት መቄዶኒያ በራስ አነሳሽነት ከመንገድ ላይ የወደቁ አቅመ ደካሞችን በራስ ጊዜ፤ ጉልበት እና አቅም የተጀመረ ነው። መስራቹ ቅዱስ ብቻቸውን የጀመሩት ተቋም ዛሬ እንዲህ አፍርቶ ለወግ ለማዕረግ በቅቶ ለዚህ ቀን በቅቷል።  ቤተ መንግሥትም እንዲህ እንሆ ታደመበት። ወይ ጊዜ እንዲህ ትክሳለህ! ሁለት ዳጋጋውያን አንስቶች እራሳቸው ደካሞችን በማስተናገድ የተሰለፉበት ይህ የቸርነት መንገድ አዲሱ የለውጥ መንፈስ እንዲህ ቅንድስና፤ ብጽዕና ያለው መሆኑን ያመላክታል። ይህ የቸርነት ጉዞ ትንሽ ራቅ አድርጌ የዛሬ አምስት ዓመት የት ትደረስ ይሆን ብዬ ስጠይቀው „አይተሽ ፍረጂ ብሎኛል።“ እናንተም አይታችሁ ፍረዱት ልበል በተሰጠኝ መልስ መሰረትነት።  የኔ ውዶች የጹሁፌ ታዳሚዎች ትንሽ ገፋ አድርገሽ ወደ 10 ዓመትስ ስለምን አለወሰድሽውም ትሉኝ ይሆናል። 10 ዓመቱ ረዘመብኝ እና ነው በእኩሌታው

ቢያፍሩ ምን አለ አባ ቆስቁስ?

ምስል
አባ ቆስስቁስ አቤቶ  አቶ በረከት ስምዖን  ሥልጣናዊ ቅርፊት  ፍርክርክ ብትክትክ። „ምናምንቴ ሰው የበደለኛም ልጅ በጠማማ አፍ ይሄዳል፤ በዓይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ይናገራል፤ በጣቱ ያስተምራል፤ ጠማማነት ብልቡ አለ፤ ሁልጊዜም ክፋትን ያስባል፤ ጠብንም ይዘራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፲፪ እስከ ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  30.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሳጅን በረከት ሥጦታ - ለአማራ።   ·        ኑ ዛዜ። ቀድመው የተናዘዙት አቦይ ስብሃት ነጋ ነበሩ። የሰሞናቱ  የኑዛዜ ሁለተኛው ነው ። ባለ ኑዛዜው አቶ በረከት ስምዖን እና ማህበረ ኔትወርካቸው ነው። በጣም የሚያስደስተው እና ተስፋ የሚሰጠው ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን በብአዴን ላይ ስሞታ አቅራቢ ሆነው መገኘታቸው ነው። ብትክትክ አሉ። አሁን ነው እኔ እርግጥም ብአዴን ራሱን ችሎ መቆም መጀመሩን የተደስትኩበት። ብራቦ! ብአዴን ብለናል ተዚህ ተኮሽ አይሏ ሲዊዚሻ። በሌላ በኩልም አባ ቆስቁስቁስ አቶ በረከት ስምዖን በአቶ ደመቀ መኮነን ያቀረቡት ክስም ቢሆን አቶ ደመቀ መኮነን ጥሩ ሰው መሆናቸውን ማወቅ አስችሎለኛል። ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን የሚጠሉት ወይንም የሚያገሉት ወይንም የሚያሳድሙበት፤ ወይንም የሚያሳድዱት ሰው ጥሩ እና ቀና ሰውን ብቻ ነው። የሚበልጣቸውን ወይንም ሴራቸውን የሚያጋልጣቸውን።  ስለሆነም በጣም ለድጋፍ ዳታ ያበዛሁበት የአቶ ደመቀ መኮነን ነገር አቋሜን ጥርት ባለ መልኩ ደጋፊያቸው ሆኜ እንድቆም አስችሎኛል የሰሞናቱ የአቶ በረከት ስምዖን ኑዛዜ፤ ወቃሳ እና በዛቸው ላይ እንደለመደባቸው የከፈቱት ዘመቻ። ስለሆነም ከዛሬዋ ዕለት  ከእለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ 30.08.2018 ጀምሮ የአቶ ደመቀ መኮነን ደጋፊ