ቢያፍሩ ምን አለ አባ ቆስቁስ?

አባ ቆስስቁስ አቤቶ 
አቶ በረከት ስምዖን 
ሥልጣናዊ ቅርፊት 
ፍርክርክ ብትክትክ።
„ምናምንቴ ሰው የበደለኛም ልጅ በጠማማ አፍ ይሄዳል፤ በዓይኑ ይጠቅሳል፤ በእግሩ ይናገራል፤
በጣቱ ያስተምራል፤ ጠማማነት ብልቡ አለ፤ ሁልጊዜም ክፋትን ያስባል፤ ጠብንም ይዘራል።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፲፪ እስከ ፲፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 30.08.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

የሳጅን በረከት ሥጦታ - ለአማራ። 

  • ·       ዛዜ።

ቀድመው የተናዘዙት አቦይ ስብሃት ነጋ ነበሩ። የሰሞናቱ  የኑዛዜ ሁለተኛው ነው ። ባለ ኑዛዜው አቶ በረከት ስምዖን እና ማህበረ ኔትወርካቸው ነው። በጣም የሚያስደስተው እና ተስፋ የሚሰጠው ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን በብአዴን ላይ ስሞታ አቅራቢ ሆነው መገኘታቸው ነው። ብትክትክ አሉ። አሁን ነው እኔ እርግጥም ብአዴን ራሱን ችሎ መቆም መጀመሩን የተደስትኩበት። ብራቦ! ብአዴን ብለናል ተዚህ ተኮሽ አይሏ ሲዊዚሻ።

በሌላ በኩልም አባ ቆስቁስቁስ አቶ በረከት ስምዖን በአቶ ደመቀ መኮነን ያቀረቡት ክስም ቢሆን አቶ ደመቀ መኮነን ጥሩ ሰው መሆናቸውን ማወቅ አስችሎለኛል። ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን የሚጠሉት ወይንም የሚያገሉት ወይንም የሚያሳድሙበት፤ ወይንም የሚያሳድዱት ሰው ጥሩ እና ቀና ሰውን ብቻ ነው። የሚበልጣቸውን ወይንም ሴራቸውን የሚያጋልጣቸውን። 

ስለሆነም በጣም ለድጋፍ ዳታ ያበዛሁበት የአቶ ደመቀ መኮነን ነገር አቋሜን ጥርት ባለ መልኩ ደጋፊያቸው ሆኜ እንድቆም አስችሎኛል የሰሞናቱ የአቶ በረከት ስምዖን ኑዛዜ፤ ወቃሳ እና በዛቸው ላይ እንደለመደባቸው የከፈቱት ዘመቻ። ስለሆነም ከዛሬዋ ዕለት  ከእለተ ሃሙስ የቀን ቅዱስ 30.08.2018 ጀምሮ የአቶ ደመቀ መኮነን ደጋፊ ነኝ።

ሌላው አቶ በረከት ስምዖን በተቃርኖ መንፈስ ውስጥ እዬዳከሩ ስለመሆኑ ደግሞ ተመልክቻለሁኝ። መቼም መልካም ነገር ሲያፈራ እኔ እኔ ማለት እና የኮፒ ራይት ሽሚያ የተለመደ ግራኛ ፓለቲካ ነው። ሳጅን በረከት ስምዖንም አይቅርብኝ ብለው „የለውጥ ሃሳብ አቅራቢው እኔ ነኝ፤ ያለው ለውጥ ባላንባራሱ እኔ ነኝ ይሉና ይህ ለውጥ ተብዬው ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ይሉናል። እሳቸው ያመጡት፤ የነደፉት፤ የቀዬሱት ለውጥ ከሆነ ስለምን በድጋፍ ሰጪነት ለሞቆም ተሳናቸው ነው ሊነሳ የሚጋበው ጥያቄ። ስለምንስ አደጋ ብሎ ሊያሰጋቸው ቻለ ነው ጉዳዩ? 

እንደገናስ አሳቸው ለኢትዮጵያ ሰላም እና ደህነነት አሳቢ ከሆኑ እሳቸው የለውጡ አመንጪ ከሆኑ ስለምን ደጋፊ አይሆንም። ስለምን አልተደመርኩም ይሉናል? አራሳቸው ላመጡት ለውጥ ስለምን ተቀናሽ ይሆናሉ¡

 በሌላ በኩል ደግሞ ህግ እና ሥርዓት ፈርሷል፤ ሥርዓተ አልበኝነት ነግሷል አሁን ያለው ብአዴን ለኢትዮጵያ አደጋ ነው ሲሉም ይደመጣሉ። እሳቸው በመሩበት፤ በዘወሩበት፤ በንግሥናቸው  የ27 ዘመን ስለምን የህግ የበላይነት መጠበቅ መንግሥታቸው ተሳናው ለሚለው መልስ የለሽ ናቸው። ብቻ ነደዋል - ቆስለዋል - ተነገርግባዋል መላ ቅጥ አተጥተዋል። ያልሳቱት ግን የጎንደር የአማራ የማንነት አብዮት አደጋው ከዚህ ሊያደርስ እንደሚችል ሰግተው እንደነበር እና መነሻም መድረሻም እንደሆነም አልደበቁምም። ይህን ደግሞ መስካሪ አያሳጣ ብለናል። ቀድሞውንም ጎንደር ምን አለ ብሂላችን ነው። 

ብቻ ሳጅኑ እሚይዙትን እሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል። ከሁሉ የሳቸው እንዲህ መሆን የሚረዳው ደግሞ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ነው። እጅግ ምቹ ሁኔታ አላቸው ማለት ይቻላል። ይህን የ ኢትዮጵያን ፖለቲካ በሃርድ እና በሶፍ ዌር አማራችነት የማምስ እና የማተራመስ ጉራሯቸው ስለተዘጋ ነው አሁን ኑዛዜው በመጠነ ሰፊ እዬተካሄደ ያለው። እንኳን ድንኳን ጥለው ለማልቀስ አባቃል ብለናልም ... ደመሩ ደግሞ ከጉባኤው በሆዋላ ይሆናል። 

ታስተዋሱ ከሆነ ውዶቼ ዶር አብይ አህመድ ለጠ/ ሚር ሲወዳደሩ ፊት ለፊት ወጥተው በሚዲያ የሞገቱ፤ ብቃት የለውም ብለው ስንት ነገር ያደረጉ ስለመሆናቸው ይታወቃል። እኔም በስፋት ሞግቻቸዋለሁኝ። አሁን ደግሞ አቶ ደመቀ መኮነን እንዳልደገፉ እና  ከኦህዴድ ብቁ ሰው እንዳለም እንደተጋሉም ዓይነት ነው የሚናዘዙት። በዚህ ዕድሜ ምን ዓይነት እስስትነት እንደሆነ መቼም የሚያሳፍር ነው። ይብላኝ ለቤተሶቦቻቸው የእኛም ትርፍ ነው።

ለዛውም ዕድሚያቸውን ሙሉ በሴራ ፖለቲካ ለበሰሉት ለሳቸው ፈጽሞ የማይመጥን ሙግት ነው እያቀረቡ ያሉት። በዬአንዳንዱ አረፍተ ነገር እራሳቸውን እያፈረሱ ነው የሚሞግትቱት፤ ራሳቸውን እዬዋሹት ነው የሚፋለሙት፤ ራሳቸውን ፈተና ውስጥ አስቀምጠው ነው ሌላውን የሚኮንኑት። ጠፍጣፋ ሙግት።

በሌላ በኩል የአማራ ወጣቶችን ተስፋ ቀብረው የኖሩት እሳቸው ሆነው ሳለ፤ በዛ የቅበር መንፈስ የሰጠሁትን ንድፍ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አልተጠቀመበትም፤ ሊጠቀምበትም አይፍቅድም ባይ ናቸው። ይህም እልል የሚያሰኝ ነገር ነው። 

የተቃጠለው ካርቦን የሳጀን በረከት ጭንቅላት የቀመረውን  የአማራ የወጣቶች የቅበር ንድፍ ከእንግዲህ በኋዋላ እርሙን ማውጣት አለበት ብዬ አምናለሁኝ። ይህን በማድረጋቸው ደግሞ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እንደ ወትሮው ሁሉ ሊመሰገኑ፤ ሊከበሩም ይገባቸዋል።

የአቶ በረከት ስምዖን አስቃኙ የተስፋ መቁረጥ ትርኢት ደግሞ የኤርትራዊነታቸው አጀንዳ አንድ ቆስቋሽ ስልት አድርገው ማቅረባቸው እና የኤርትራን መንግሥት ከዜግነታቸው ጋር ነጥለው ያቀረቡበት ስልታዊ መንገድም ሌላው በኤርትራ መንግስት ላይ ዜጎቹን  በአሉታዊነት ያስነሳልኛል ብለው የሳቡት ሌላው የጦርነት ቀጠና ነው።

እኔ ኤርትራዊ ሆኜ ሳለ፤ የኤርትራ መንግሥት ግን እኔ በኢትዮጵያ መንግሥት እንድገለል እዬሠራ ነው ማለታቸው ሆን ብለው የፈጠሩት አንዲስ የቀወስ ቀጠና ነው። አጋጣሚ ካገኙ እሳቸው ለማንም እና ለምንም ሊተኙ የማይችሉ፤ ተለዋዋጭ ባህሪ ያላቸው አባ ቆስቁስ መሆናቸውን ያሳያል።

ትልሙ--- የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ኤርትራውያን በተፃራሪ የቆመ ነው ለማስባልም ጭምር ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ኤርትራውያን ታገላላች እንዲባል የኢትዮ ኤርትራን ሰላማዊ ግንኙነት ከአቅቃማቸው በላይ ስለሆነ ለዚህ አዲስ የክፈተት ማገዶ ያቀረቡበት ዘይቤያቸው ነው። ከሴራ ቸረቸራ የሚጠበቅ ስለሆነ አይደንቅም    >>>

ይህን መሰል ነገር በሌላም ሊሂቅ ቀርቦ ነበር። አጀንዳቸው ያለቀባቸው ሰዎች ሌላ ሥራ የላቸውም። ሥራ ፈትነታቸውን ብቻ ሳይሆን 21ኛው ምዕተ ዓመት አመክንዮም የሾለከባቸው ናቸው እንዲህ ዓይነት ፍጥረቶች። ምክንያቱም ዓለም የሚሻው ዛሬ ሰላምን ነው። ከጦርነት ትርፉ አመደ ብቻ ነው። 

ሌላው "ትምክህተኛ፤ ነፍጠኛ" ሲሉት ለኖሩት፤ እያደኑ ሲያሳድኑት፤ እዬቀበሩ ሲያስቀብሩት፤ እያበለዙት ሲሰላስሉት፤ እያወዬቡት ሲያስነቅሉት ለኖሩት አማራ ደግሞ ብቸኛው ተቆርቋሪ ሆነው ለመቅረብ የሄዱበት መንገድ „ለማያውቅሽ ታጠኝ“ እንዲሉ መሆኑን እሳቸውም ያውቁታል እኛም አሳመረን እናውቀዋለን። ይባረኩ እንጂ አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ሆነ አቶ ምግባሩ ደህና አድርገው የመልስ ምቱን በፋክት ላይ ተመስርተው ሰጥተዋቸዋል። 

ከሁሉ በላይ ግን አንድም የአማራ ልጅ አባ ቆስቁስ አቶ በረከት ስምዖን ነፍሴ እንደማይላቸው ልባቸው ያውቀዋል። እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሪሞሪካቸውን፤ ጋንታቸውን፤ ኔታቸውን፤ የሴራ ስካዶቻቸው ሁሉ ዘመን ያለፈባቸው የተነፈሰ ጎማ መሆናቸውን ልብ ሊሉት ይገባል።

እንዴት የአማራ ልጅ አንቅሮ እንደተፋቸው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ሲሞቱም እንደ እኔ እንዳሻቸው ሲጫወቱበት የኖሩት የኢትዮጵያ አምላክ መቃብራቸው እንጦርጦስ ሆኖ ሰው እዬሰማው ጓ ጓ ጓ እያለ ሳጥናቸው ሲወርዱ ይታያል ብዬ ነው እማስበው። ይህንን አንድ ጊዜም ጽፌ ነበር።  

ስንት አድራሻው የማይታወቅ ዜጋ እንደወጣ ተውጦ ቀርቷል። ስንት እናት እንዳነባች አልፋለች፤ ስንት ሚስት እንዳለቀሰች ቀርታለች፤ ስንት ልጆች ወላጅ አልባ ሆነው ተበትነው ቀርተዋል። የዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠሪ አሳቸው ናቸው። ጠረናቸው አድማ እና ሴራ ነው። 

አላዛሯ ኢትዮጵያ እኮ የሳቸው የመሞከሪያ ጣቢያ ነው የነበረችው። ሙሶሎኒ ከሰራው ግፍ በላይ ኢትዮጵያን አልመው እንድትጠፋ ያደረጉ እርኩም ሰው ናቸው። ይህን ራሳቸውም የተፈጠሩበት ስለመሆኑ አሳምረው ያውቁታል። አሁንስ ምን ሲሰሩ ነው የባጁት? ምሾ ዋይታ - ስሞታ እንዲበራከት ማነው አቃጁ እና አስፈጻሚው፤ ንገሩኝ ባይ።
  • እገዳና ጥንዝሉ ተስፋቸው።  

ከማዕከላዊ ኮሜቴ መታገዳቸው ጉባኤው እስኪሰበስብ ድረስ ነው። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሲናገሩ ጉባኤው ይሁን ይቀጥል ካለ ይቀጥላለሉ ካለም ይሰናበታሉ ብለዋል። አዎን ሥልጣኑ የብአዴን ጉባኤ ነው። የአባላቱ ጠቅላላ ጉባኤ ነው ማዕከላዊ ምክርቤቱን የመረጠው። በዚህ የ አደረጃጀት ሂደት በአንድ ወቅት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ስለሰጠሁበት አልሄድበትም። ታስታውሱ እንደሆን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲታገዱ ሂደቱን በሚመለከት አቶ ኤርመያስ ለገሰ ያቀረበው ትንተና ስለነበር ያን ሞግቼ አቅርቤ ነበር ያልኩትም አልቀረም እንደታገዱ አሉ። 

በጥቅሉ ማዕከላዊ ምክር ቤቱም ተጠሪነቱም ለብአዴን ጉባኤ ነው። እኔ እንጃ ደመነፍስ ካልሆነ በስተቀር አንድም ቀንጣ ነፍስ መርገምትን ይቀጥልልኝ፤ መቃብር እሸከማለሁኝ፤ መርዶ ጥሞኛል ብሎ እንዲቀጥሉ እንዳማያደርግ እኔ በእርግጠኝነት መናገር እችላላሁኝ። አቶ በረከት ስምዖን እና ጓዶቻቸው ኤክስፓዬርድ ያደረጉ እኮ ናቸው። ያለቀ ብቻ ሳይሆን የዛጋም ባትሪ ናቸው።

ርግጥ ነው ከዛ በፊት መረባቸውውን ዘርግተው የሞት ሽረት ትግል ሊያደርጉ ይችላሉ። እስከ ህልፈታቸው ከሴራ ፖለቲካ ይድናሉ ተብሎ መቼም አይታሰብም። ያው የተፈጠሩ ለአድማ ነውና፤ ነገር ግን እኔ 100% እርግጠኛ ነኝ አቶ በረከት ስምዖንን የብአዴን ጉባኤ የማዕካዊ ምክር ቤት አባልነት ይቀጥሉ ብሎ እንደማይወስን። በጣም እርግጠኛ ነኝ።

 27 ዓመት ተቀብሮ የኖረው የብአዴን ጉባኤ የመጀመሪያ ትንሳኤው ዕለት የሚሆነው ይህን ሲፈጽም ብቻ ይሆናል። እሳቸውን ብቻ ሳይሆን የጃርት ጉባኤ ማህበርተኞችን በሙሉ አግልሎ ጥርት ባለ አቋም እና መርህ አዲሱን ዘመን በአዲስ ብቃት እና በነጠረ መስመር ይቀጥላል ብዬ አስባለሁኝ ብአዴን። ይህም ብቻ ሳይሆን ይህን ከንቱ እወድድ የሚለውን ባርኔጣውን ብአዴን አውልቆ ክልሉን እንደ ሥሙ የሚወክሉትን መሪዎችን ይመርጣል ብዬ አስባለሁኝ። 

ለፌድራልም ውክልናው በዛ መስመር ይሆናል ብዬም አስባለሁኝ። ይሄ  በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ጨዋታ መቆም አለበት። ትግራይ የራሷን ልጆች ነው ተወካይ አድርጋ የምትልከው ብአዴን ደግሞ ተጨማሪውን ኮታዋን ሲሸፍንላት የቆዬውን ከንቱነቱን በዚህ ጉባኤ የማያዳግም እርምት መውስድ አለበት። ባህርዳርም ወካዮዋን በትክክል መወከል ግድ ይላታል። ወይ ብአዴን  አውነተኛው ብአዴን ወይ ደግሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን አንዱን መምረጥ ነው ያለበት ባህርዳር ...በስተቀር ብአዴን የ አማራ አብዮትን ጥያቄ መመለስ አይችልም። ድምጽ መስጠት ማለት ወስኙ የመሸነፍ አዋጅ ነው።  

በሌላ በኩል ግን አሁን አቶ ደመቀ መኮነን እንዲቀጥሉ መደረግ አለባቸው ባይ ነኝ። ሳጅን በረከት ስምዖን ሃሳብ ተፃራሪ ሆኖ የቀረበ ሰው፤ ያ ሰው እጅግ ንጹህ እና ቅን ከሴራ - ከአድማ ጋር የተፋታ ነው ብዬ አስባለሁኝ።

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አንድ የማልወድላቸው ባህሪ አለ። እኔ ወድጀዋለሁና እናንተም ያን ሰው ውደዱልኝ የሚሉት ነገር። አሁን አቶ ደመቀ መኮነን ሁልጊዜ ያነሷቸዋል። እኔ ደግሞ ጊዜ ያስፈልገኛል ብዬ በዝምታ ነው የቆዬሁት እስከ አለፈው የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ቤት እስካዬኋዋቸው ድረስ፤ ከዛ ሳያቸው ግን በሥራ ብዛት ሰውነታቸው እንደዛለ ነበር የተመለከትኩት።

እናም ከልቤ ገቡ የአሁን የሳጅን በረከት ስምዖን የሰሞኑ ዘመቻ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ አቋሜን ቀይሬ ከአቶ ደመቀ መኮነን ጎን እንደቆም አድርጎኛል። ምክንያቱም የአባ ቆስቁስ አቶ በረከት ስምዖን ንፈስ የጨለማው የሳጥናኤል ስለሆነ።
  • ·       ሳስበው

ሳስበው አቶ በረከት ስምዖን ለጠ/ ሚኒስተርነት እራሳቸውን አጭተው ነበር። ችግራቸው ይሄው ነው። ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እንደሞቱ እሳቸው ይህች ቦታ የእኔ ናት ብለው ተደላድለው ተቀምጠው ነበር። ያ አልሆነም። 

አሁን ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ ሁኔታዎች ሲለዋወጡም ይህ ቦታ ከእኔ ሌላ የሚሸፍነው የለውም ብለው አስበው ስለነበር ነው ዶር አብይ አህመድን በቀጥታ ወጥተው ታች ሁሉ ወርደው ባልተገባ እና ባልተለመደ ሁነታ ያን ያህል ዘመቻ የከፈቱት። በዚህ አጀንዳ ወደ አምስት የሚሆኑ ሰዎች አብደው ነበር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለጠ/ ሚር እጩነት ሲወዳደሩ። ሌሎቹ ደግሞ በስውር ፍላጎት ይናጡ ነበር።

ቅብዕ የፈጣሪ ሆነና ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ሆኑ። መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ ስኬታቸው ብዙ ሰዎች ከገመቱትም፤ ከጠብቁትም በላይ ነው። እኔ እንደሆን ብዙ ነገር የማይደንቀኝ የምጠብቀው ሰለሆነ ነው።

ስለ እሳቸው ስሞግትም እርግጠኛ ሆኜ ነበር። መንፈሳቸው ቅርቤ ነበር። ሰውኛ ነው ተፈጥሮኛም ነው። አሳታፊም አቀራራቢም ነው። ፈገግተኛም ነው ሳቅ የናፈቀውም። ሃሳብ አፍላቂም ነው ከዋኝም ነው። ታጋሽም ነው አታጋሽም ነው።  

ኢትዮጵያ የዓለም ሚዲያ አምድ የሆነችው በዚህ ዘመን በስፋት ነው። እንኳንስ ኢትዮጵያ ኤርትራ ራሷ። ይህ የጭንቅላት ቁርጥማት የሆነባቸው ደግሞ ሴራ አደራጅተው ብዙ መከራ አውጀዋል። ይህም ሆኖ አዲሱ ለውጥ እዬገሰገሰ ነው። 

ብቻ ሳጅን በረከት ስምዖን ከሴራም፤ ከደባም፤ ከአድማም ስለማይታቀቡ ባሊህ ሊባሉ ይገባቸዋል። ሹልክ ብለው ደግሞ ሌላ መከራ ሳያሳውጁ በጅ ቢባሉ መልካም ነው።
ሥልጣን በሽታ ነው። ሥልጣን እንዲህ ያሳብዳል። 

የዕድሜ ልክ የጠ/ ሚር ወይንም የፕሬዚዳንትን ምኞት ያለበት ሰው ሁልጊዜም ግጭት ሸማው እና ሚዜው ነው የሚሆነው። ከሁሉ ጋር፤ ብቅ ካለው ባለ አቅም እና ክህሎት ጋር መጋጨት እና ማተራመስ ምኞቱን ያሳካለት ይመስለዋል። ይህ የጠ/ ሚር ህልመኛ ባናኝ ወላዊ ባህሬ ነው። አቅም በወጣ ቁጥር እረሳለሁ ወይንም ሾልኬ እቀራለሁ በማለት በቃ ይርበተበታል።

የዚህ ሁሉ ጉግስ ድምር ሲጠቃለል አማራን ወክለው ጠ/ ሚር ለመሆን እራሳቸውን አጭተው ስለነበር ነው አቤቶ አቶ በረከት ስምዖን። ጠቁሙኝ - አቅርቡኝ ብለው ድርጅታዊ ሥራ አለመሥራታቸውም አሳቸው ሆነው ነው። ይህም ቢቀር የአቶ ፍጹም አረጋን ቦታ ሳያስቧት፤ ሳይሰልሏት አይቀሩም ነበር ... ቢቻል ... 

ወደፊትም ትርምሱ እንዲቀጥል ስጋቱ እንዲጨመር ለዛም ተግተው ይሠራሉ። አቶ በረከት ስምዖን ጠ/ ሚር በረከት ስምዖን የመባል ህልም ነው ያላቸው፤ እስከ መቃብር ድረስ ነውና። ምኞት እስከ መቃብር ይባልላቸው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች አሉ … በህልማቸው ዙፋን ደፍተው የሚኖሩ …. ቢያልፉ እንኳን ምኞታቸው አብሮ ነው ተሰኔሉ ተቹቻው ላይ ይጣፍልኝ ነው የሚሉት … ባለገኘውም ጠ/ ሚር እገሌ ልባል ዓይነት ... 

የሆነ ሆኖ ቃለ ምልልሳቸው እና ምኞታቸው እና ተስፋቸው ቃሬዛ ላይ ውሏል። አብሶ አዲስ አበባ ላይ ጠ/ ሚሩን ደግፎ የወጣው ወደ 5 ሚሊዮን የተገመተው ህዝብ፤ ባህርዳርን ጨምሮ በዬከተሞች የታዬው የድጋፍ ትዕይንት፤ ውጪ አገር በመላ አውሮፓ እና በስሜን አሜሪካ ለሳቸው የተደረገው አቀባባል እና ድጋፍ፤ በአረብ አገር የሚኖሩ ወገኖቻችን የሰጡት ፍቅር እንደ አሳጅን በረከት ላለ ቅን ለማያስብ ቀናተኛ ማህበረ ሳዖል አለማበዳቸውም እሳቸው ሆነው ነው።

ከመነሻው ጀምሮ የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ወደ ፊት መምጣት በጠላትነት ስሜት የሞገቱ ክፉ ሰው ናቸውና። አብሶ የኤርትራ ህዝብ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ የሰጠው ፍቅር እና አክብሮት እርቃናቸውን አስቀርቷቸዋል።

በፖለቲካ ልምድና ተመክሮ ማዕካላዊ ግንዛቤ ሲታይም ይህ ክስረት ነው። አንድን ሰው ሌላው ተመክሮ አለኝ የሚለው ሲገመግም ብቃቱን ከጥላቻ፤ ከምቅኝነት፤ ከማናህሎኝት በጸዳ መልኩ ማዬት መመዘን ሲገባ እሳቸውና መሰሎቻቸው ግን የሰጡት ኢባሎሺን አቅመ ቢስ ፖለቲከኛ ሆነው ነበር የቀረቡት። ስለሆነም ልምዱ፤ ክህሎቱ ለዚህ ካልበቃ የባከነ ጊዜ ነው ለእኔ አለፍኩ ለሚሉት የፖለቲካ ህይወት።

አንድን ሰብዕና አይመቸኝም ልትለው ትችላለህ፤ ግን ብቃቱም ለመመዘን ለመስፈር ተመክሮህ ሥራ ላይ መዋል ካልቻለ የአንተ ፖለቲከኛነትን ወና ነው ማለት ነው። መቼም በዚህ ዘመን እኔ ብዙውን ሰው በፖለቲካ አቅሙ እርቃኑን ቁሞ ነው የሚታዬኝ። ፖለቲካ የአገር ችግር መፍቻነቱ ከብቃት እና ከፋክት መነሳት ሲገባ ከሥልጣን ይገባኛል ሆነና ሁሉም ከፎቅ እዬወረደ ሲፈጠፈጥ ማዬት የ2018 ትዕይነት ሆኖ አረፈው።
  
የሆነ ሆኖ አደባባይ ወጥተው አቶ በረከት ስምዖን ዶር አብይ አህመድን ሲቃወሙ እጅግ በርካታ ጹሁፎችን ጽፌያለሁኝ። መቼም እሳቸውን የሚነካ ሰው ሁሉ አንስት ካለሆነ ሁሉንም ማለት ይቻላል ሞግቻለሁኝ። ምክንያቱም እንዲህ አይነት ቅንነትን ስንቁ ያደረገ የፖለቲካ ሊሂቅ ማግኘት የሰማይ ያህል እሩቄ ነበርና ነው።

ስለዚህም ትህትናቸውን፤ አቅማቸውን፤ የማይጠገብ ጥረታቸውን አላዛሯ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን እሻ ስለነበር የቀረ አለነበረም። አንቴናዬ ረጅም ነበር።  አቶ በረከትንማ ምንም ሳላስተርፍ ነው እስኪበቃቸው ነበር የሰለቅኳቸው። አሁን ደግሞ ይገላበጣሉ እንደ ሽንበራ ቂጣ …

ብቻ ህልም እልም /// ህልም እልም ብለው አረፈው ቢቀመጡ ጥሩ ነው። ከእንግዲህ እሳቸው የሚዘወሩት የአማራ ነፍስ ምድር አታፈራም። የተፋውን የሚልስ ውሻ ብቻ ነው። ኢትዮጵያም በቃት ከአድመኞች ጋር ፍቺ መፈጸም አለባት። 

መከረኛ ናት መቼም እናት አገር ኢትዮጵያ ከህዝብ ፍቅር ተወጥቶ ዘነዘናውን ተቀርቶም አሁንም አለማረፍ ነው እንደ ለመደብን በአድማ በሴራ እንረስሽ ማለቱ የእርግማን ነው … ቢያፍሩ ምን አለ አባ ቆስቁስቁስ አቶ በረከት? እኔ እኮ ሲናገሩት ተቆርቆሪ ነኝ ሲሉ አራሱ ቃሉን ሲደፈሩት ምን ዓይነት ሰው ቢሆኑ እላለሁኝ። መጠለት እኮ ከባድ ነገር ነው። ምን አለ ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡ …

አቶ በረከት ስምዖን ማመስና ማተራመስ፤ ህውከት እና ሴራ አድማ እና አፍራሽነትን በቃኝን የማያውቁ የፖለቲካ ሰው ናቸው። አሁንም ሥልጣን ቀረብኝ ብለው በዬቦታው ማይክ ፍላጋ ይማስናሉ፤ መፈለገም፤ መመኘትም መብት ቢሆንም በቃህን ሲባል ደግሞ ትንሽ ህሊናን ማሰራት ይጠይቅ ነበር … 
  
Ethiopia: አቶ ንጉሱ ጥላሁን ሰይፉ ላይ ቀርበው ለበረከት ስምዖን ምላሽ ሰጡ

Ethiopia: ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገ ልዩ ቆይታ Exclusive Interview With Bereket Simon

 

·       ሲጠቃለል።

ኢትዮጵያ ከአባ ቆስቁስ አቶ በረከት ስምዖን ሙሉ ለሙሉ የተገላገለች እለት ስለ ነፃነት ፊደል መቁጠር ጀምራለች ማለት እችላለሁኝ።

 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 


የኔዎቹ ማለፊያ ጊዜ ኑሩልኝ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።