ልጥፎች

ከጁላይ 31, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የማህበረ አብይ ጉባኤ ... መሪ እና ፕሮቶኮል ሹም።

ምስል
አንጄትን ቅቤ ያጠጣው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አገላለጽ ነው! „ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 31.07.2018 (ከገደማዋቷ ሲዊዘርላንድ) በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰሞናቱ የማህበረ አብይ ጉባኤ የመድረክ አመራር በርካታ ዕይታዎችን አነበብኩኝ። የፕሮተኮል ሹመነትም ተደማሪነትም አለበት። የሆነ ሆኖ ያው በእሱ ዙሪያ እጅግ በርካታ ውዝግቦችን ብራና አስተናግዳለች። እሱን በሚመለከት የተፈለገው ቢባል እኔ በራሴ ውስጥ ነበርኩኝ።  የወጣሁት ከእሱ ሰብዕና አልፎ ትዳሩ ላይ ወቀሳ ሲሰነዘር ግን በህግ አምላክ ብያለሁኝ። ጽፌማለሁኝ። በጣም መጠን አልፎ መሄድ አያስፈልግም። ትዳር ላይ የሚወሰድ ምንም ነገር የለም።  ትዳር ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም። የሰውም የእጅ ሥራ አይደለም የጣና ዘገሊላ ጉዳይ። እንዲያውም የሚስጢሩን ልቅናውን ብናወቀው ሌላ ዘሃ መጎተት ባላስለፈገን ነበር። አገርም በአህቲ መንፈስ ትጸድቅ ነበር። „ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ፤ ቢያንስ ይህ የህይወት ቃል አብሶ የተዋህዶ ልጆች ሊያከብሩት ይገባል። ወቃሽ ጸሐፊው የተዋህዶ ልጅ ስለነበሩ።  ከዚህ በመለስ አሁን ትልቅ ቦታ ስለተሰጠውም ነው ሊያሰኝ አይችልም 7ኛ መጸሐፌ "ርግብ በር" ላይ መልካም ነገር ስላገኘሁ ሃሳቡን ለማስረጃነት ተጠቅሚያለሁኝ። እኔ ቅንነት ባለበት ቦታ ሁሉ ዳር ደንበር የለኝም። ወደ ጉዳዬ እንብርት ስገባ መቼም ፈታኝ ነው፤ አደባባይ ላይ የተሳታፊን ጥያቄ ማስተናገድ። እኔ አይቼ አላወቅም በሰለጠነው ዓለም። አሁን የሆነው እንደዛ ነበር። ኢትዮጵያ ግን በዛ ሰሞን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው የደሴን

መሻገር እና መሸጋገር የአምክንዮ ልዩነት አላቸው።

ምስል
ስንፈጠር  መቻልም መቻቻልም ተሰጥቶናል። „በግዞትም ቤት አደባባይ ታሥሮ ሳለ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ሲል  ወደ ኤርምያስ መጣ፣--- ሂድ ለኢትዮጵያዊው አበሜሌክ እንዲህ በለው፣-  የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣--- እንሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያን ቀን በፊትህ ይፈጸማል። በዚያ ቀን አድንሃለሁ ይላል፤ እግዚአብሄርም በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች አንጂ በሰይፍ አትወደቅም፣ በእኔ ታምነሃልና ፣ ይላል እግዚአብሄር። (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፴፱ ከቁጥር ፲፭ እስከ ፲፰) ከሥርጉተ ሥላሴ 31.07.2018 (ከገዳማዊቷ የደም ገንቦዋ ሲዊዝሻ።) ·        እፍታ። አሁን ያለው ሁኔታ መሻገሪ እንጂ መሻገር አድርገው የሚመለከቱት ወገኖቼ አሉ።  ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ስለደከመኝ አሳደርኩትኝ። በፈለገ ሁኔታ ቢሆን የሚኒያፖሊስን የስብሰባ ድባብ ሳላዳምጥ አልተኛም ብዬ እሰከ እኩለ ሌሊት ቆዬሁኝ። ቅድመ መሰናዶው መስፍኔ ፈይሳ እንደ ዲሲዊ ሲያስቃኘኝ ቆዬ። ያዘንኩት ግን ለታታሪው የእርቅ ጌታ ለመስፍኔ ፈይሳ ቅድሚያ አለመሰጠቱ ነበር። የሚገርመው ትንሳኤዋን ልዕልት ልጁን ይዞ ነበር ሲንገላታ ያዬሁት። ልጅ የያዙ፤ ጤናቸው የጎደለ ደካሞች፤ ነፍሰጡሮችን በሚመለከት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር፤ በዚህ ዘርፍ የዲሲውን አድንቄያለሁኝ። አዛጋጆች ከOMN ጋር የቅድምያ ቃለ ምልልስ በኦሮምኛ እና በአማርኛ አድርገው ነበር። ምቾት የሚሰጥ አልነበርም። በበዛ ሁኔታ የመነጠል ተደሞ ነበረበት። በዚህ በመነጠል መንፈስ ዘመናት ተቆጠሩ የተረፈ የለም። ጀርመን የአውሮፓ ህሊና የሆነው የበርሊን ግንብ በማፈረ