ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 17, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሙሽራ ዜና ከሙሽሪት ተዋናይት ሃና የሖንስ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ሙሽራ ዜና ከሙሽሪት ተዋናይት ሃና የሖንስ። „አቤቱ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።“ (መዝሙር 15 ቁጥር 1) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·         እ ፍታ። ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አንድ ያልተለመደ ድንገቴ ብሥራት ገጠመኝ እና ዜና ቢጤ ላቀርብ ፈልግኩኝ። ባልደራስ ለኢትዮጵያ ሙሽራም ቤተኛው ሆነለት። ታድሎ! በጥልቀቱ ሲታይ ጣና ዘገሊላ - አስተርዬ አይታያችሁምን? ድንቅነት በህብርነት! ·         ባ ልደራስ ለኢትዮጵያ ሙሽራዊ ረድኤት ቀረበው። „ጥበብ ቤቷን ሰራች፤ ሰባት ምሰሶም አቆመች።“ ሙሽርነት እንዲህ የህዝብ ወገንትኝነት ሲታከልበት ያማራል ይሰምራል። ያበራል ያስተምራል። ቅኔያዊነት ያፈካል። እኛዊነት ያሰብላል። እንዲህ ዓይነት ህብሬነት ትውልድን ከብክነት ያተርፋል። በዚህ ውሳኔ እናታዊነትን አይቸበታለሁኝ። እናትነት እንዲህ ነው ይራራል። እናትነት እንዲህ ነው መከራን ይደፍራል። እናትነት እንዲህ ነው መስቀልን ይሸከማል። እናትነት እንዲህ ነው በመሆን ያምርበታል። እናት እንዲህ ናት ለቸገራቸው ፈጥና ደራሽ። ፈውስ! ውድ እህቴ ተዋናይት እና „የእንተዋወቃለን ወይ?“ የቴልቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ወ/ሮ ሃና የሖንስ ጋብቻውን የአብርኃምና የሳራ ይሆንላችሁ ዘንድ ከዚህ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ አንዲት ባተሌ እህትሽ ተስፋዋን እንሆ ላከችልሽ። ውሳኔሽ ከአእምሮዬ በላይ ሆነ።   እንደምን አድርጌስ ልተርጉምሽ? እንደምንስ አድርጌ ላመሳጥርሽ? የዕውነት ከበደኝ። ተስፋ ባጣንበት ወቅት አዲስ የፈካ ቀን ፈቀድሽልን። አንቺም፤ ትዳርሽም፤ ቤተሰቦችሽም የተባ