ልጥፎች

ባልደራስ ለኢትዮጵያ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። ባልደራስ ለኢትዮጵያ እንደ አባት አደሩ ሰንበት ቅኔ ዘረፈለት። „አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ካፌ ቃል አትራቁ።“   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 5 ቁጥር 7) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 15.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·         እፍታ። እንዲህ በአጭር ጊዜ በ ባልደራስ ለኢትዮጵያ ጉዳይ እመለሳለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር። ዘለግ ያለ ሃሳቤን ስለገለጽኩኝ። ብቻ አዎን ብቻ በኽረ አጀንዳችን ይሆን ዘንድ አቅሙን በበለጠ፤ በመሰመረ ሁኔታ ገንቡለት ተባልን፤ ጥበብ ያነሳቸው ፍጥረቶች እነ ማህበረ - ኦነጋውያን። ስለሆነም ደግመህ ናብኝ ማንጠግቦህ ተበላ! እና ብራና እና ቀለም ተመሳጠሩ።  የህልውና ተጋድሎ እንዲህም መራራ ነው። እንዲህም በዬፌርማታው ቀጠሮ የሚሰጥበት አይደለም። ተግ! እስኪ በል ማለት አይቻልም። ቆራጥ ውሳኔ የሚሰጠው እረኛ ያስፈልገዋል። አዲስ አበቤ ሆይ! እንደ ተመኘሁልህ ቀንቶኃ። አይዞህ ባይ ማግኘትህ ን ዕሴትህ አድርገው። ·         በር።    እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ ተዋጥን እኮ በኦነጋውያን የድንገቴ ዝብርቅ ተውኔት። ድብልቅልቅ ያደርጉታል ሁለመናውን። የሰከነውን አዬር እራሱ ይቀኑበታል። ቀናተኛ ናቸው። የረጋውን አውደ ምህረት ቀይጠው ቀወጡት። ሱናሜ ነው የኦነጋውያን ቅይጡ ቅንጡ ንጠት ። ከቶ ተግባባን ይሆን? እኔ ለረጅም ጊዜ ስጽፍበት የባጀሁትን በቅርቡ ለዘሃበሻ ልኬለት አውጥቶት ነበር። ሊንኩን ከሥር እለጥፋለሁኝ። ጉዳዩ የፈረቃም፤ የተረኝነትም አይደለም ከዛ ያለፈ ነው ብዬ ነበር። አምቀው፤ አሽገው አጥረው ይዛዋታል ልዕልት ኢትዮጵያን በቃላት ጅዶ ከሽነው። የችግሩን የውሃ ልኩን ሳታውቅ ትግል

የኔታዋ የደወል ምህላን፤ ብትደፍረው፤ የአርሲ ነገሌ መስቀል ጉዞ ወደ ቀራንዮ

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የኔታዋ የደወል ምህላን ፤ የደወል አቤቱታን ብትደፍረው ታተርፍበታለች። የአርሲ ነገሌ መስቀል ጉዞ ወደ ቀራንዮ። „አንተ ታካች እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሳለህ?“ {መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 6 ቁጥር 9} ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 13.01.2020 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን። ይድረስ ለብፁዓን ወቅዱሳን አባቶቼ በሙሉ። በያሉበት ።                                                 ሰማዕት ሱራፌል ሰለሞን።                         ·        እፍታ። ጤና ይስጥልኝ የአገሬ ቅኔዎች እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ በረጋ ጸጥታ - በአርምሞ ዝምታ - ዘመንን በቀስታ ከምታስናግደው ከእመቤት ሲዊዝሻ ጋር ደህና ነኝ። እህቴ ከወደ አሜሪካ ጎራ ባለችበት ወቅት የገዳም ከተማ ስትል የምኖርበትን ቀዬ መሰጠረችው። ለእኔም ግጥሜ የሆነው በዚህ ስሌት ይመስለኛል አብረን ገደምን። ስከነት የሰፈነበት። ዛሬ ሁለት ዕርዕሰ ጉዳዮችን በአንድ አጣምሬ ነው እማቀርበው። „ የኔታዋ የደወል ምህላን፤ የደወል አቤቱታን  ብትደፍረው ታተርፍበታለች“ „የአርሲ ነገሌ ጉዞ ወደ ቀራንዮ።“ ሁለቱም የዕንባ ቤተኝነታቸው ከአንድ ማህጸን ይቀዳል። ·        ምልሰት። በመስከረም እና በጥቅምት ወር በፌስቡኬ ላይ የኔታዋ የደወል አብዮትን ብትደፈረው ታተርፍበታለች የሚል አጫጭር ማስተዋሻዎችን ጽፌ ነበር። እስከ አሁን ለብጹዓን ወቅዱሳን አባቶቼ መልዕክቱ አልደረሰም መስል ወይንም ፈቃደ እግዚአብሄር አላ