ልጥፎች

ከኦክቶበር 19, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የሥልጣኔ ድንጋጌ ጥሩ ዜና በበተልሄም ብሥራት ሲሰክን!

ምስል
የማግስት ብሥራት ድንጋጌ ናት የፈጠራ ባለቤቷ ወጣት ቤተልሄም ደሴ። „ሁሉም በመቅደሱ ምስጋና ይላል።“  መዝሙር ፳፰ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 19.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።፡ ማስተዋሏ የበረከተ ነው። ቅኝቷ ለምለማዊ ነው። እረቀቷ እዬራዊ ነው። በዓላማው ውስጥ ከዕድሜዋ በላይ የሚጠይቀውን ትዕግስት ተጎናጽፋ በአማኑኤል ተሰጥቷትም ሐሤትን በተሟላ ተስፋ በገፍ አጋርታናለች። ብርክታዊት! ለኢትዮጵያ አገሬ ሽልማትም ናት። እሷም ደስተኛ ናት። እውነት በማይመስሉ የኮንፒተር ሳይንስ ፍልስፍናዎች እና ውጤቶች ተሰማርታ ስኬታማ ሆናለች። ዕድሜዋን ሳያስቡ ተግባሯን ብቻ ማሰቡ ብቻ ይሻላል። ዕድሜዋን አስበው የህይወት ጊዜዋን ሲያስተውሉ ልበወለድ ስለሚመስል። „ለእግዚአንሄር ግን የሚሳነው የለም“ ማለቱ ለአማንያን ታምራቱን ያይ ዘንድ የሆነው ሁሉ እንዲህም ሆነው። ብሩሕ ቢዥነር ናት። እማጅነሽኗ እርቀቱ ይገርማል። የምትገርም ዕንቡጥ ቀንበጥ ፈላስፋ ወጣት ናት። ለ21ኛው ምዕት የተፈቀደላት ባለመክሊት ናት። እውነትም ቤተልሄም የዬምስራች ዓውደ ምህረት የሥልጣኔም ጥሩ ዜና።   የሚገርመው በዚህ ዕድሜዋ ልዑል እግዚአብሄር እኛን የሰጠበት ሚስጥር ደርሳበታለች። አትጨናነቅም፤ መጨናናቅንም አጀንዳዋ አለደረገችውም። ብሩሁን ጭንቅላቷን ማበከን አትፈቅድም እና። ጊዜዋን ባልባሌ ጉዳያዎች አታሳልፈም። ጌዜ ወርቅ ነው ገቢር ላይ ውሏል። ደስታ ተስጥዖችን ስለመሆኑ እዬኖረችበት ነው። ህይወትን ቀለል ዘና አድርጎ መኖርንም በዚህ ዕድሜዋ ታስተምረናለች። ፍልቅልቅ ያለች፤ ቀለል ያለች ቁጥብ ወጣት ብርሃን ጠገብ ወጣት ናት። የተስፋ ውሃ ልክ ንጥረ ነገር እርጋታዋ የችግር መፍቻ በእጇ ስላለ ብቻ ሳይሆን ኢማጅኔሽኗ