ጎንደሮች ምከሩ። ማስተዋልን ዘክሩ።
ጎንደሮች ምከሩ። ማስተዋልን ዘክሩ። "አቤቱ በመመስገኛህ ቦታ በጽርሐ አርያም ሆነህ እኛን በዓይነ ምህረትህ ተመልከት።" (መጽሐፈ ባሮክ ምዕራፍ ፪ ቁጥር፭) የእኔ ክብር ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ? ሰንበት እንደምን አለፈ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። እናንተም ደህና ሁኑልኝ። አሜን። በጣም ዘለግ ያለ ጹሁፍ ነው። ……… እንሆ ዛሬ ……… በእቴጌ ጎንደር ዙሪያ ትንሽ እል ዘንድ ፈቀድኩኝ። በ2014 እአአ በደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው የጎንደርን ተሳትፎ በሙሉ ልባቸው በተቀበሉ ድህረ ገጾች በ፬ ክፍል ስለ ጎንደር ጽፌ ነበር። የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይንም አንድ ቀን ሊፈነዳ የሚችል የተዳፈነ ቦንብ እንደሆነ ኮልሜ ነበር። ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ በኽረ ብሄራዊ ዓለም ዓቀፋዊ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል። ምን ለማለት ነው ይሄ? አስፈላጊ ሲሆን እቴጌ ጎንደርን በሚመለከት ይጣፋል ለማለት ነው። ስለ ጎንደር ሲፃፍ፤ መልካም ሲነገር የሚከፋቸው እንዳሉ አውቃለሁኝ። እነሱም ፕሮ - ህወሃቶች ናቸው። አንድ ግለሰብ፤ አንድ ተቋም፤ አንድ ሚዲያ ተግቶ በፀረ ጎንደርነት ከሠራ ያ አካል ፕሮ - ህወሃት መሆኑ አስተርጓሚ አያስፈልጋችሁም። ፕሮ - ህወሃት ሆነው ኢትዮጵያኒዝም መለያችን የሚሉትም፦ ጎንደርን ከልባቸው ፈግፍገው፦ ፍቀው ስለመሆኑ ልብ ልትሉት ይገባል። ስለምን? ጎንደር ትቀደምልኝ የሚለው ኢትዮጵያን ስለሆነ፤ የኢትዮጵያ ምልክት ነኝ የሚል ሁሉ ከጎንደር መንፈስ ጋር ግብግብ ፈጽሞ አይገባም እና። #የቅኔው የጎጃም ህዝብን በሚመለከት። ጎንደሬ ነኝ የሚል ሁሉ በማስተዋል ሊራመድ የሚገባው የጉዞ ቅያሴ፦ የቅኔው ጎጃምን ማገዶነት ስለጎንደር ከውስጡ በዶግማነት ሊቀበል ይ...