#የህወሃት #ጃርታዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ለኢትዮጵያ #መቃብር እንጂ #ትፍስህት አይደለም።

 

#የህወሃት #ጃርታዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ለኢትዮጵያ #መቃብር እንጂ #ትፍስህት አይደለም።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 1 person and smiling
 
እሚታዬ ጽግሽ ተናግሮ ካናጋሪ ያድነኝ የዕለት ጸሎቷ ነበር። እኔ በህወሃት ዙሪያ ቅንጣት አቅም ማዋጣት አልሻም። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ቀበጥ ያሉ ዘመናይ ሃሳቦች ሲነሱ የተገባ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።
 
ህወሃት በኢትዮጵያዊነት ላይ ቂም #የቋጠረ ድርጅት ነው። ቂምን እዬዘረዘረ ነው ኢትዮጵያን ሲበቀላት ነው የኖረው። እናት አገር ኢትዮጵያ #መተንፈሻ እንድታጣ ያደረገው እልል እያለ በፌስታ ነበር። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ተፈላጊነት #እንዲከሳ ያደረገው አቅዶ ነው።
ህወሃት ትግሉን መሠረትም ሲጥል ቂም እና በቀልን #ከጥላቻ ጋር አጋብቶ ነው የጀመረው። ለዚህም ነው በሥልጣን ዘመኑ እንኳን "የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት" የሚለውን ሥያሜውን ያለወጠው። ህወሃት ጥንስሱም፤ ውልደቱም፤ እድገቱም፤ አስተምኽሮቱም፤ ፍልስፍናውም #በጸረ ኢትዮጵያዊነት የተጠቀለለ ነው። 
 
በእያንዳንዱ የሥልጣን ዘመን ሂደቱ ነገ ኢትዮጵያ #ሊያሰቃይ ይችላል የሚለውን ክፋ ሃሳብ ሲያፈላ፤ ሲተክል፤ ሲኮተኩት፤ ሲያሳድግ እና ጨካኝ ሃሳብን ሲያሰብል ነው የኖረው። የውጭ ኃይሎች የነደፋትን ካርታ ተግባር ላይ ያዋለው ህውሃት ነው። ኢትዮጵያን ባህር በር እና ወደብ ያሳጣ ህወሃት ነው። የኤርትራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ህብራዊነት #የጎረደው ህወሃት ነው።
 
ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ዒላማው ትምህርት ቤት፤ የህዝብ መገልገያ ክሊኒክ እና መንገድ ማውደም ነበር። ይህን እኔ በስማበለው ሳይሆን በዓይኔ በብሌኑ ያዬሁት ሃቅ ነውና #ቀለጤ ፕሮፖጋንዲስቶች አያስፈልጉኝም። 
 
ህወሃት ኢትዮጵን #አራጦ በገዛበት ዘመኑ ሁሉ ፊት ለፊት የታገለው ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ነው። በኢትዮጵያዊነት ተቋማት ላይ ዘመቻው ሰፊ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊትን፤ የኢትዮጵያ ባህር ኃይልን፤ የኢትዮጵያን አየር ኃይልን የበተነው እሱ ነው። የኢትዮጵያ የሠራዊት አገነባብ #ከፕሮፌሽናልነት ወደ #አማተርነት ቀይሮ ደረጃውን ቁልቁል የለቀቀው ህወሃት ነው። ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተያያዙ አመክንዮች ሁሉ በህወሃት ነደዋል። 
 
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት ለውጭ አገር ባለሃብቶች ቸብችቦታል። እንደ ህወሃት ዘመን የኢትዮጵያ ሙሁራን፤ የሃይማኖት አባቶች አልተሰደዱም ነበር። ህወሃት ፖለቲካው #የጃርት ነው። ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮን ካለ ርህራሄ ያስደረቀው ህወሃት ነው።
 
እኔ ህወሃትን እማከብርለት ፈቅዶ እና ወዶ #ሥልጣኑን ማስረከቡን ነው። ለዚህም ነው ሙሉ ፯ ዓመታት ዝም ብዬ የተቀመጥኩት። የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሰጣቸው መጠንም ልክም ያልነበረው ፍቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የህወሃት #ጭካኔያዊ ፖለቲካ ያንገፈገፈው ስለመሆኑ አሳይቷል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የተሰጣቸውን ወደር የለሽ ፍቅር አቅም አንሷቸው በቅጡ አስተዳድረው፤ ያን ቅንነት እና መታመንን በመምራት ህዝብ የጠበቀውን ተስፋ ሊመግቡ ባይቻላቸውም።
 
ኢትዮጵያ የሚለው ኃይለ ቃል የህወሃትን #በሽታ የሚቀሰቅስ ሰይፈ ሚኬኤል ነበር። በዘመኑ ህወሃት ከጭካኔ ውጭ ርህርህናን ደፍሮ የማያውቅ ጉልበተኛ መንግሥት ነበር። በዘመኑ የሠራቸው ልማት ነክ ጉዳዮች እንዳሉ አዳምጣለሁኝ። ያ ጥሩ ቢሆንም በጦርነቱ ቆርቁሮት የአማራ ክልል ላይ በዘመኑ የተገነቡ የመንግሥት እና የግል ድርጅቶችን አይሆኑ አድርጓቸዋል። አገር የመራ ድርጅት በዚያን ያህል ወርዶ የበቀል ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ውስጥ መዘፈቁ አሳፋሪ ነበር። የግለሰብ ጓዳ ዝርፊያው ሌላው ነውሩ ነው።
 
በጦርነቱ #አፋር#ትግራይ እና #አማራ ተጎድተዋል። ይህም ህወሃትም፥ አብይዝም በገቡት የፋክክር ጦርነት የመጣ ኪሳራ ነው። ህወሃት ሥሙን ለማደስ ባገኜው ጊዜ ፈጽሞ አልተጠቀመበትም። #ማይካድራ#ጭና#ወረባቡ#ኮንበልቻ ንፋስ መውጫ እራስ #ጋይንት#አፋር ትምህርት ቤት ላይ የፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት አልፀፀተውም። የሚገርመው ይህንን የሚያንቆለባብሱለት ሰብዕናወች ማግኜቱ፥ የጭካኔ አውራነቱን ይቀጥልበት ዘንድ አንድ ማፋፊያ እርግማን ይመስለኛል።
 
ህወሃት ቢኖርም፤ ባይኖርም፤ ቢከስምም ቢያልፍም ለኢትዮጵያ #ምንም {} ነው። ምክንያት ኑሮም አላማረበትም እና። በጦርነቱ ባዶ እጁን አጨብጭቦ፤ ነፍሱን ብቻ ይዞ ተሸንፎ ነበር የወጣው። ነፍሱን ያተረፈለት የአሜሪካ መንግሥት እንጂ ህወሃት #ተጠናቆ ነበር። ጉዳትን በሚመለከት በሁለቱም ወገን መጨካከን ነበር። የሰባዕዊ መብት ጥሰት እና የሰው ልጅ ስቃይ ነበር። በዚህ ሂደት አብረን ልናፍር ይገባል።
ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ይጠቅማል? አይጠቅምም አስተዋዩ የትግራይ ህዝብ፤ የትግራይ ተወልጄ ተጋሮወች የሚወስኑት ጉዳይ ነው። ህወሃት በአገራዊነት ጉዳይ እርግማን፤ መቃብር እንጂ ትፍስህት አይደለም። ህወሃት ለኢትዮጵያ ዕዳ፤ መከራ፤ የፈተና እንኮሸሽሌ ነው። አቤቱ ህወሃት ቢዳከምም፦ ቢሰናበትም በለስ ቀንቶት ቢጠናከርም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ፋይዳው እምብዛም ነው።
 
/// የህወሃት ፖለቲካ ከህግ በላይነት ነው። ይህ ደግሞ አናርኪዝም ነው።
/// የህወሃት ፖለቲካ ማፈንገጥ ነው። ይህ ደግሞ ህግ ተላላፊነት ነው።
/// የህወሃት ፖለቲካ መታበይ ነው። ይህ ደግሞ ልክን አለማወቅ ነው።
/// የህወሃት ፖለቲካ ክህደት ነው። ይህ ደግሞ ለትውልድ ዕዳ ከሜዳ ነው።
/// የህወሃት ፖለቲካ የመግለጫ እና የ24 ሰዓት ስብሰባ ነው። ይህ ደግሞ ሰላማዊ መንፈስን ማወክ ነው። ሙሉ ፲ ዓመት!
/// የህወሃት ፖለቲካ ግትር ነው። ይህ ደግሞ ጸረ ዴሞክራሲ ነው።
/// የህወሃት ፖለቲካ በጥባጭ ነው። ይህ ደግሞ የመንፈስ ስርቆት ነው።
ወዘተ። ወዘተ።
 
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከህወሃት እንኩሮ ምኞት ፈጣሪ፤ አላህ ቢገላግላቸው ልዩ ሽልማት ነው። ለአፍሪካ ቀንድ፤ ለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ አገሮችም የቀውስ ማምረቻ ድርጅት ተፈጥሯዊ ሞቱን ቢሞት ልዩ መታደል ነው። ብሄራዊ ቀናቸው በሆነም። ይህን የፃፍኩት ዛሬ ሳይሆን ከ፲ ዓመት በፊት ነው። ለአፍሪካ ጠንቅ መሆኑን። ለህወሃት ፓን አፍሪካኒዝም ምኑ ነው? ምንሙ።
ህወሃት እርካታ ቢስ ነው። ሁሉንም ብታደርግለት በቃኝን አያውቅም። ህልመኛ ነው። ህልሙ ደግሞ ከአቅሙ በላይ የተንጠራራ ነው። በሌላ በኩል ከህወሃት ፖለቲካ ባሻገር ያሉ የሳይለንት ማጆሪቲው ማህበርተኛ ተጋሮወች ልቅና ያላቸው፤ የጨመቱ ብቁወች አሉ። ዕድሉን ቢያገኙ ህወሃትን ያሳዩት በነበረ በተባ ጨዋነት ትንግርትን ፈጽመው። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን፤ አስበን፥ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/05/2025
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?