ልጥፎች

ከጃንዋሪ 19, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጉራጅ ዘመን የአማራ እናትን ከመኖር እርስት ነቀሏታል።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላምመጡልኝ። የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጉራጅ ዘመን የአማራ እናትን ከመኖር እርስት ነቀሏታል። የአማራ ወጣት ተስፋውም ባሩድ እና ካቴና ሆኗል። „እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎች ግን በቃል ጠሩት፤ ባልንጀራም አደረጉት፣ በዚህም ጠፉ።“ (መጽሐፈ ጥበብ ቁጥር 1 ቁጥር 16)      ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 18.01.2020 ·        መነ ሻ! „ሴቶች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ከወንዶች የሚስተካከሉበትን መንገድ ለመፍጠር ብልጽግና አበክሮ ይሠራል “ {ዶር አብይ አህመድ}።  ስላቅ! ነው ለእኔ። ዘለግ ብሎም ይፈተሽ፤ ይሞገትም። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሁልጊዜ የታይታ ስለሆነ ነገራቸው ዓለም በዚህ እሳቸው በሌሉበት ሁኔታ የተሳሰተ መንገዳቸውን ሃቅ መስሎት ዕውቅና እንዲሰጥ በእንግሊዘኛም ከሥር ይጽፋሉ። ከቶ አገር ስንት ዓይነት ሰው ይሆን ዬምታበቅለው?ከዬትኛው ዩንቨርስቲ ይሆን የተማሩት ይህን መሰል አረንዛዊ ጉዳይ ? ከዬትኛውስ ፕላኔት ይሆንስ የመጡት? ኢትዮጵያዊው ምድር አስተናግዶት የማያውቅ የአሟሟት ዓይነት በልጇቿ ላይ ይፈጸም ዘንድ የአማራ እናት በዘመነ አብይዝም ተቀጥታበታለች። ዶር አብይ አህመድ የአማራ ሴት ተቆርቋሪ እንዳልሆኑ የአማራ ሴት ጠንቅቃ ታውቀዋለች።  አስተርጓሚም ባለቅኔም፤ ፕሮፖጋንዲስትም አትሻም፤ እንዲሁም የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ካድሬም አያስፈልጋትም። ምድሪቱም፤ ጋራ ሸንተረሩም ያነባሉ - ይመስክራሉም አይደለም ተጠቂዋ የአማራ እናት // የአማራ አንስት። ዬዬትኛው ብሄረሰብ...