ፍቅርን መቀበልም ማብቀለም ፈተና ነው።
ፍቅርን መቀበልም ማብቀለም ፈተና ነው። ከሥርጉተ ሥላሴ 16.06.2018 ከመነኩሴዋ ሲውዝዬ ነፍሴ። „ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሄርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁኝ።“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፬) · መክፈቻ ። እንዴት ናችሁ የኔወቹ የልቦቹ አባ እና እማ እነ ቅንዬ ? ዛሬ ቀኑ ፈታ ብሏል። ፏ ብላlች ልዕልተይ። አሁን አንድ ጹሑፍ ከብራና ሳተናው አነበብኩኝ። ከማከብራቸው ጸሐፊ አቶ ስዩም ተሾመ ነው። ወቅታዊ ነው ብዬም አላምንም። ጭብጡ ለአብይ መንፈስም ተቀራራቢ አይደለም ብዬ አምናለሁኝ። ተቀራራቢ ያልሆኑ መንፈሶች ሃሳብን ከመክፈል ውጪ ለምናስበው ተስፋ ጠቃሚ አይደለም። ክብሩነታቸው በማህበረ ደራጎን...