ክፉዎች የተፈጠሩበትን ነው የሚሠሩት- እኛሥ ሥማችን ማን ይባል?

                   ክፉዎች የተፈጠሩበትን ነው የሚሠሩት።
                             አሳዛኙ ነገር እኛ ማዳበሪያ መሆነችን ነው።
                                 ሥንሠራው የባጀነው ይሄንኑ ነው።

                                               ከሥርጉተ ሥላሴ 16.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)

                              „መዳህኒቴ ሆይ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ።" (መጽሐፈ ሳሙኤል ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፫)

ያለን ወገን ኑሮው ይህን ይመስላል። አብይ የተረከበው


ክፉዎች ክፉ ናቸው። የተፈጠሩበትን ነው የሚሠሩት። አሳዛኙ ነገር ለመልካም ነገር እንተጋለን የሚሉት የነፃነት ታጋዮች ይህን መሰል የመከራ ዜና የሚናፍቃቸው መሆኑን ነው። ለዚህ BBN ለናሙና መውሰድ ይቻላል። ይህ ሚዲያ ከጅምሩ ኦቦ ለማ መግርሳን ኮንኖ የተነሳ መሆኑ የታወቀ ነው። ከዚያ ቀጥሎ በዶር አብይ ዙሪያ እጅግም ከሰው በወረደ ሁኔታ ደፍሮ የተወያዬ ሚዲያ ነው።

News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa
BBN Presents Jawar Mohammed | Lemma Megersa | Oromo | Amhara | EPRDF
አንድ ሰው ጊዜውንም ፍቅሩንም ውስጡንም የሰጠው ሚዲያ እንዲህ ሲሆን እጅግ ያሳዝናል።

ሌሎቹ እንደ ኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ያሉት የፖለቲካ ተፎካካሪዎች ስለሆኑ የተሻለ አቅም በመጣ ቁጥር ዳጥ እና ምጥ ስለሚይዛቸው ምኞታቸው ተንጠልጥሎ አዬር ላይ ስለቀረ በዚያው ምክንያት ነው። ሌላም የውል ቋጠሮ ስላለ የሚከብዱ ነገሮች ይኖራሉ። ይህ ደግሞ ብቸኛ ተወዳዳሪ አልባ ከነበረ የፖቲካ ድርጀት እና ሚዲያ የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱም ፉክክር ነው። ፉክክሩን መሬት ማስረገጥ ሳይሆን አዬር ላይ ተንጠልጥሎ መሬት ላይ ያለውን የህዝብ ሳቅ በትኖ ስጋት እና ውጥረት በመጨመር፤ ጫና አይሎ ኢትዮጵያ ውደ አልታወቀ አቅጣጫ ከምትጓዝ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ከሚል መደምደሚያ ላይ እንዲደረስ በስልት እና በዘዴ ወጋ ጠቀም ያለ በደጋፊ እና በተቃዋሚ ሃሳቦች ዙሪያ እሰጣ ገባውን በማስጨነቅ የተፈጠረቀ አቅጣጫን ከመመኜት የመነጬ ነው። በዛ ላይ እትጌ ኤርትራም የዘመናት ህልሟ ከስም ሲል የወለሌ ገበታ በመሆኑ ባለ በሌላ ሃይል ናደ መልቀቅ አዬር ላይ የሚጠበቅ ነው።

እትጌ ኤርትራ ከሰበቸው ባጠረ ጊዜ ነው በውጪው ዓለም ሳይቀር የአብይ ካቢኔ ተደማጭነቱ ጎልቶ የወጣው። ኢትዮጵያም ወደ ነበረችበት ክብር መመለስ ያስቻለችው። ይህ ለ እትጌ ኤርትራ የአንጀት ካንሰሯ ነው። ስለሆነም አዬር ላይ ገረጭራጫ ንፋስ መልቀቋ በቧንቧ አማካኝነት የሚጠበቅ ነው። እርምጃው እኮ የአብይ ካቢኔ ለኢትዮጵያ ጠላታዊ መንፈሱ መብረቅ ነው ... ለዚህ ነው እኔ ሲጀመር ጀምሮ ዶር አብይ አህመድን ለህይወታቸው የስጋት ምንጭ ሻብያም ሊሆን እንደሚችል ሁሉ ስጽፍ የነበረው። ለዶር አብይ አህመድ ብቻ ሳይሆን ለኦቦ ለማ መግርሳም፤ ለአቶ ገዱ አንድርጋቸውም በቅርብ ላሉት ቅናዊ መንፈስ ላላቸውም ቢሆን አይተኛም ሻብያ። ሥራው ምን ሆነ እና። ምክንያቱም የአሁኑ አብዮት ተተኪዎችን ያሰናዳ በመሆኑ ከሥሩ ነቅሎ ማደረቅ በቀላሉ አይቻለም። ሰማዕትነቱ ተከታታይ ሰለሚሆን አቅሙም በተከታታይ የሚቀጥል እና መሠረት ያለው ስለሆነ በቀላሉ ገጭ ገው በማድረግ አንዱን አስገድሎ ክፍት ማድረግ የማይቻል ነው።
  • ወዳጅነት በጥያቄ ምልክት ሲሆን ይጨንቃል? 

እኔ የሚገርመኝ የBBN ጉዳይ ብቻ ነው። ይህ ሚዲያ አዘውትሬ እና ወድጄው የማደምጠው ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ የእስልምና ጨዋነት የተላበሰ ስለነበር፤ መረጃዎቹ ወቅታዊ ስለነበር፤ የማይደጋጋሙ መረጃዎችን በፍጥነት ባጫጭር ዜናዎች ስለሚያቀርብ በተለዬ ሁኔታ እኔ „ድምፃችን ይሰማ ነኝ“ ብዬ የወጣሁበትም አምክንዮ ስለነበረ የራሴ አድርጌ ነበር የማዳምጠው።

የለማን መንፈስ ቀድሞ ተጻሮ የወጣ ሲሆን፤ ዶር አብይ አህመድ ከተመረጡበት ቅጽበት ጀምሮ ማለትም ከመጋቢት 10 ቀን 2010 ጀምሮ ደግሞ ጽኑ የሆነ ጥላቻ በጠ/ ሚር አብይ ካቢኔ እንዳለው ተመልክቻለሁኝ።

News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa
BBN Presents Jawar Mohammed | Lemma Megersa | Oromo | Amhara | EPRDF
አንድ ሰው ጊዜውንም ፍቅሩንም ውስጡንም የሰጠው ሚዲያ እንዲህ ሲሆን እጅግ ያሳዝናል።

ምንጩ ምን ሊሆን ይችላል ብዬ ሳስበው ዶር አብይ አህመድ ከእስልምና ክርስትናን ከመምረጣቸው ውጪ ምንም ሳንክ ሊያገኝባቸው ፈጽሞ አይችልም። አሁን በተወካዮች ምክር ቤት እና በፌድሬሽኑ ምክር ቤት ከፍተኛው ሹም ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች የእስልምና እምነት ተከታይ ለዛውም ሴቶች ናቸው። ኦሮምያ ውስጥ ምክትል ፕሬዚዳንቷ የእስልምና ዕምነት ተካታይ ሴት ወጣት ናቸው።

በዬትኛውም የሃላፊነት ቦታ ጎልተው የሚታዩት፤ ቀልፍ ቦታ ላይ ያሉት በፌድራል ደረጃ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ BBN ከተደመጫነት ወደ መርዶ ዘጋቢነት የተሻገረበት ሚስጢር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። አሁን ላሜ ወለደች ሁኖለታል። አዋሳ ላይ የተፈጠረው ችግር እና ግጭት የሚመኘው እና የሚናፍቀው ስለሆነ ስለት የሚያስገባ ይመስለኛል። እጅግ ፈንድቋል።

እኔ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ፋሽስታዊ ሥነ - ልቦና መወራጨት የሚደንቀኝም የሚገርመኝም አንዳችም ነገር የለም። ዛሬ ግሎባሉ ዓለም ሁሉም መረጃ ስላለው ሊደበቅ ስለማይችል ነው እንጂ ስልጣን ከመያዙ በፊት በትግራይ ታሪክ አዋቂዎች አዛውንታት፤ በወልቃይት እና በጠገዴ ህዝብ፤ በምርኮኞች የፈጸመው በደል ከዚህም በላይ ነበር። 

አንድ ሰው ጨካኝ የሚሆነው የሥነ - ልቦና ችግር ሲኖርበት ብቻ እና ብቻ ነው። ይህ ችግር ደግሞ ያው ወደ እንሰሳነት የሚቀይር ነው። ሰው ከሰውነት ተለይቶ ጨካኝ ከሆነ አውሪያዊ ሆኗል ማለት ነው። ግማሽ ሰው ግማሽ አውሬ። ቁመናው ሰው ድርጊቱ አውሬ። ስለዚህ ከዚህም የባሰ እና የከፋ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መጠበቅ ግድ ይላል።

ነገር ግን ለሰላም ለእስልምና ሃይማኖት እኩልነት የተፈጠረ አንደበት እንዴት ጠቅላላ የኢትዮጵያን ጮራ ተፃራሪ፤ አውጋዥ፤ አሳዳጅ ሆነ መቅረብ ግን ተልዕኮውን በጽሞና እንድንመረምረው ግድ ይላል። የቅርቡን ትቼ የቀደመውን ሊንኩን ከታች ለጥፌዋለሁኝ። ምን ያህል መንፈስ ሲንድ እና ሲያተራምስ BBN እንደ ከረመ።

ሌላው እጅግ ያዘንኩበት የቆሰልኩበትም በህብር ራዲዮ ነው። ህብር ብሄራዊ አማራጭ ራዲዮ እንዲሆን ምኞቴም ስለቴም ነበር። ሁለቱም አዘጋጆች በቅንነት እስከ ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ባዕለ ሹመት አገልግለው ችግር የተፈጠረው የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሊታመን የማይችል አቅም እና ትህትና እዬጎላ ሲመጣ በተቃራኒወ ነው የተቆመው። ስለምን ብዬ ልመረምር አስብኩኝ? አንዳንድ ፍንጮችን ባገኝም ግን እርግጠኛ ለመሆን ተጨማሪ ሁኔታዎችን ማጥናት ግድ ይላል።

ይህ ህብር ራዲዮ ደፋር፤ ለእውነት ዘብ የቆመ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ የማይደራደር ሆኖ ስለምን ኢትዮጵያ አቧራዋ ተራግፎ እንደ አገር በሁለት እግሯ እንድትቆም ጥረት ሲደረግ ትችት እና የሚያጣጥሉ ሰዎችን እያፈላለገ እንደሚጠይቅ እና እንደሚያወያይ ራሱ ይገርመኛል። እኔ የተለወጥኩ ያህል ይሰማኛል። ምክንያቱም ህብርንም የእኔ ብዬ ነበር የማዳምጥው ዜናዎችን እና ትንተናዎች።

እኔ የራዲዮ ፕሮግራም ታዳሚ አይደለሁኝም። ብዙ ማንበብ ነው የምወደው። የህብር እና የቢቢኤን እና በተጨማሪም አዋዜን ግን እከታተላለሁኝ። አጫጭር ሆነው የሚያወጡትን ዜና ነክ ጉዳዮችን ብቻ። አሁን ከህብርም ከቢቢኤን ጋር መፋታት ግድ ይላል። ስለምን? ጤናዬ ስለሚያስፈልገኝ።

አንድ የሰማይ ጸጋ ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ ዓይነት እናት የሆነ መሪ ለዘመኑ በሁሉም መስክ የሚመጥን ሥልጡን ንቁ ብርቱ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ሙሴ እናት አገር ኢትዮጵያ አልማው አታውቅም። በቀን ሦስት አራት መልካም ዜና ማድመጥ ቅብጠቱንም ቅልጣኑንም ጨምሮ ሁሉም ጠ/ ሚር ለመሆን ተመኜ። ቀደም ባለው ጊዜ በዚህ ምኞት ዙሪያ በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ አሁን አገር ምድሩ ይሄው ነው ነፍሱ ... የተንተለጠለችበት። 

መመኘት መልካም ቢሆን አንደኛ ካለ ቅብዕ አይሆንም፤ ሁለተኛ ከአብይ አቅም በላይ ለመገኘት የዛሬ 50 ዓመት ዕድለኛ ከተሆነ ብቻ የሚሳካ ህልም ነው። ቀረህም፤ ይጎድልሃልም፤ ያነስሃል የሚባል አንዳችም ነገር በዚህ የፍቅር ፍቅር፤ የደግነት ደግ፤ የርህርህና ርህርህና፤ የትህትና ትህትና የሊቅ ሊቅ፤ የልቅና ሊሂቅ አይገኝም። ፈጽሞ ፈጽሞ የማይደክም ቀን ከሌት በዬዘመኑ የተቆለለውን ችግር ለማስወገድ የሚተጋ ትሁት - ታታሪ - ትንታግ ሳተና ራሱን ዝቅ ያደረገ ችግርን ለማድመጥ የፈቀደ በእኛ ምድር ያለ ነው ወይ ለማለት እስከሚያዳግት ድርስ ፍጽምናው አሟልቶ የተገኘ የሁለመና ሐዋርያ የሙሴዎች ሙሴ ነው የአብይ ቸር መንፈስ።

ይህ ያልተመቻቸው ክፉዎች በግል እና በወል ተደራጅተው ያምሱታል፤ ሰላሙን አውከው፤ ለማደናቀፍ ይታትራሉ። የኢትዮጵያን ህዝብ መሳቅ አቃጣላቸው፤ ብጥብጥ ናፈቃቸው፤ ሁሉ እዬተነሳ ሲዘነጥል እና ሲያዋክብ እኔ ብሆን ይህን እችለዋለሁኝ ብሎ ማሰብ ተስኖታለኝ። አንድ ቀበሌ ማህበር በአግባቡ ማስተዳደር ቀርቶ ስብሰባ መምራት የማይችለው ሁሉ ተራራ ላይ ሆኖ የፍርሻ ቦንብ ሲጥል ውሎ ያደራል። ከቅልጣንም፤ ከዘመናይነትም በላይ የናጠጠ ነው የፍላጎታችን ጣሪያ።

በዛች ደሃ አገር ውስጥ ሁልጊዜ ሙሽርነት መመኘት። እንኳንስ ኢትዮጵያ ለዛውም ሽግግር ላይ ያለች፤ ከሚከስሙት አገሮች ተርታ የነበረች፤ መንግሥት ያልነበራት አገር ቀርቶ በትረ ሥልጣናቸው ከተደላደሉት ከሰለጡኑት፤ ዲታ ከበለጸጉት አገሮች ብዙ ዓይነት ችግር እና ፈተና ነው ያለባቸው። በዬዕለቱ ዲሞ አለ። በዬዕለቱ ግጭት አለ። ስለዚህ ማህበረ ደራጎን ያህል አውሬ ጋር የሚታገል መንፈስን ሌላው ተደራቢ ማዳበሪ ሆኖ በግራ በቀኝ ወጥሮ አፍንድቶ ለማዬት ይራወጣል። ሁሉም ዕድሉ ተሰጥቶት እኮ ታይቷል አንሰም በዛ። በዛው በተከዘነ በታቆረ ሃሳብ ተወጥሮ ነው የኖረው።

ለዚህም ነው በስልት እና በዘዴ ይህን ቅናዊ የሰማይ ስጦታ ቀልብሶ ተልዕኮውም ሆነ፤ መንገዱም እንዲሁም አቅጣጫው ሁሉም ነገር ውል የለሽ ሆኖ የተጀመረው መልካም ነገረ ባክኖ፤ ሌላ አዲስ የማናውቀው መንገድ እንዲፈጠር ነው ትጋቱ …. ታሪክ ያሾለከው ሁሉ የዚህ የመከራ ቀጣይነት ህልመኛ ነው።

በቴሌቪዥንም አልበቃ ብሎ በጹሑፍ የጠ/ሚሩ መንፈስ በማወክ እና ተረጋግተው እንዳይሰሩ ጫና በመፍጠር ህዝብን በማቆሳቆስ አትርፈናል ይሉ ይሆናል እነኝህ የክፉዎች ማህበርተኞች። ነገ ግን ታሪክ እና ሂደት ምስክር ነው እና በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀሬ ነው …

  • ·        ምሾ ደርዳሪ ሚዲያ የክከተት ጥሪ … አዋጅ ነጋሪ!
ይሄ ጥቂቱ ነው ከተወሰነ ጊዜ በኋዋላ አቅለሸለሸኝ እና ተውኩት … 
ለዚህ ለምሾ አውራጅ ሚዲያ ጊዜ ማቃጠል ስለማይገባ። ከተመሠረተብት ተልዕኮው ውጪ ነው እዬተራመደ ያለው። 

አጋዚ በኦሮሚያ ክልል አራት ሰዎችን መግደሉ ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል በኮማንድ ፖስቱ የተያዙ ተጠርጣሪዎች በቂ ምግብና ህክምና እያገኙ አለመሆኑ ታወቀ

የጠ/ሚው የመቀሌ ጉዞ የፈጠረው ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው 16.04.2018

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89711

// አብይ አህመድ የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ግጭትአንገታችንን አስደፍቶናልአሉapril

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89462

ለተተኪው ጠቅላይ ሚንስትር የመልካም ምኞት መግለጫ እና አገራዊ የለውጥ ጥያቄ!” – የሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ

http://www.satenaw.com/amharic/archives/54920

በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ አሁንም ውጥረት መኖሩ ተጠቆመ

ከለማ በስተጀርባ

https://www.youtube.com/watch?v=S-lj2dB32gs

EXPOSED: TPLF False Flag

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/90098

የአሜሪካ ኤምባሲ ለአህመዲን ጀበልና አንዱአለም አራጌ ቪዛ አለመስጠቱ ታወቀ

የጌዴኦ ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው
BBN Daily Ethiopian News April 25, 2018
  • ክውና።
ስለዚህ አሁን ከዚህ የባሰ ቢመጣም ዲል ያለ ሠርግ እና መልስ አዘጋጅቶ አስረሽ ምቺው ማለት ነው በወበራ በክፉ ዜና እና ትንተና ልቡ ውልቅ ሲል ውሎ የሚያድረው ሚደያ እና ተንታኙ ሁሉ። በቃ ይሄው ነው የተፈለገው። በዚህ ውስጥ ምን ያህል የወያኔ ሃርነት ትግራይ እጅ እንዳለበት እና ምን ያህል ባልሆነ የአዬር ላይ ፕሮፖጋንዳ በውስጥ ለውስጥ የማደራጀት ተግባር እንደ ተከወነ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። አሁን ቀጣይ የህዝብ ስብሰባ እንዳለ አዳመቻለሁኝ በክብሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ልዩ መግለጫ ላይ። ሰዎችን አሰናድነተው በድርጀታዊ ሥራ እንደሚጠብቋቸው ልብ ልክ ነው። ሌላ ሥራማ ምን አለ ... ራስን ማደረጃት የተሰነው ሁሉ ያለፈበትን መልቀም የተለመደ ነው ... 

ብቻ ለኢትዮጵያ እናቶ ዕንባ ዘመን መቀጠል ሁሉም ዬየድርሻውን በመወጣት ላይ መሆኑ መታወቅ አለበት። ይህ ዲያቢሎሳዊ፣ ቅናታዊ፣ ምቀኛዊ ጉዞ የት ሊያደርስ እንደሚችል መጠበቅ ነው።

የኔዎቹ ቅኖቹ ክብረቶቼ ከተወዛወዘው ጋር በመወዛወዝ፤ ከሚንጨቧረቀው ጋር በመንጨባረቅ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም። አቋምን ሚናን ለይቶ ከንጹሁ አብይ መንፈስ ጋር እራስን አጣምሮ በውስጥነት ከመልካምነት፤ ከቅንነት፤ ከርህርህና፤ ከሳቅ፤ ከተስፋ ጋር አብሮ መራመድ ሰዋዊነት ተፈጥራዊነትም ነው። ከሁሉ በላይ የ ኢትዮጵያ እናቶችን የዕንባ ዘመን ያደርቃል። የጽድቅም ጉዞ ነው። 

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ 
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።