የሃሳብ ነፃነት #ሰው #የተፈጠረበት #ዓውራ #ሚስጢር ነው። የእኔ አዲስ ፍልስፍና ነው። #መኖር የሚሰለጥነው በሃሳብ ነፃነት ነው። #የኢትዮጵያ ሳንባ ሙሉለሙሉ ንጹህ አየር ሊተነፍስ ይገባል።
የሃሳብ ነፃነት #ሰው #የተፈጠረበት #ዓውራ #ሚስጢር ነው። የእኔ አዲስ ፍልስፍና ነው። ህሊና ያለው ፍጡር ሲፈጠር እንዲያስብ፤ እንዲመራመር፤ እንዲፈላሰፍ ነው። እንዲያመሰግን፤ ምህረት እንዲሆንም። #መኖር የሚሰለጥነው በሃሳብ ነፃነት ነው። #የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሃሳብ ነፃነትን በአገለለ ቁጥር እየጫጫ፤ ውርጭ እየገረፈው ይኖራታል። #አንጎልማ ዲንቢጥ ወፍም አላት እኮ። ዶሮም አለው አንጎል። #ፍትህ ! #ምንጊዜም #ፍትህ !ፍትህ አልባ ዓውድዓመት #ግንጥል ጌጥነት ነው። #የግንጥል ጌጥ ፈቃደኝነት #ለምን ? #ስለምን ? #የኢትዮጵያ ሳንባ ሙሉለሙሉ ንጹህ አየር ሊተነፍስ ይገባል። "አቤቱ ንጹህ ልቦና ፍጠርልኝ።" አሜን። ምዕራፍ ፲፯ በርከት ያሉ የሚፈታትሹ ኃይለ ቃሎችን አዋህጄ ነው እርዕሱን ያጎለበትኩት። ነጠላ ከሚሆን ሰሞነ ዓውድዓመት አይደል? ዕርእሴ እንደ አባት አደሩ ጃኖም፤ ካባም፤ ካሰኜውም ካሊም ደረብ አድርጎ ቢቀርብ ከውስጥ፤ ለውስጥ የቢሆነን ዓይነት ነው ዕሳቤየ። በተፈጥሮው የእኔ ጹሁፍ ዘለግ ቢልም፤ ዕርዕሶቼ አጫጭር ናቸው። ዛሬ ግን እንደ ሐምሌ አቦ ንብርብር ድርብርብ አደረግኩት። እርግጥ ነው አልፎ አልፎ ከሁለት በላይ ርዕሶችን አስተጋብሬ የማቅረብም ልማድም አለኝ። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ፈላስፊቷ ሙሉ ገፆዋ #ግርዶሽ እንዳያጥልበት የሃሳብ ነፃነት የሚበራባት አገር ትሆን ዘንድ የዘወትር ምኞቴ ነው። መናፈቅ። ሰላም ከዚህ ይፈልቃል። የልብ ሽፍትነትም ይለሞጣል። እርግጥ የከረሩ፤ እንደ ጠፍር የገረዘዙ፤ ህግን የሚጫኑ ብቻ ሳይሆን በዚያች ታላቅ አህጉርም ለሆነች አገር የ...