ልጥፎች

ከዲሴምበር 6, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አንድ ጥበብ የጨለመበት።

ምስል
አንድ ጥብብ  የጨለመበት። Eine Art Dunkelheit . „አንተ ረዳቴ እና መድህኒቴ ነህ አምላኬ ሆይ አትዘገይ።“ መዝሙረ ዳዊት ፴፱ ቁጥር ፩፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ(Sergut © Selassie)                                      የሥነ ጹሁፍ እና የመጋዚን ዝግጅት ት/ቤት ውዶቼ ይህን ጹሑፍ የጻፍኩት በ2006 ነበር በፈረንጆች። ያን ጊዜ ሳኡ ከሚባል የስደተኛ መጋዚን ዝግጅት ቡድን ጋር እሳተፍ ነበር። ያን ጊዜ የተጻፈ ነበር። ያን ጊዜ ብዙ እርማት ቢያስፈልገውም በጀርመንኛ ብርቱ ጸሐፊ ነበርኩኝ።ታዳሚም አርቱን ዘይቤውን ይወደው ነበር። ለመጽሄቱ ግጥም የጀመርኩት እኔ ነበርኩኝ። ዛሬ ሳቆመው ቆመ ይባላል። ዛሬ በጣም ደካማ ነኝ። ወደ ቁልቁል ልበለው። ወደ ሦስት ዓመት ሊሆነኝ ነው ስለላውም ስለበዛብኝ ትምህርቱም የማታው ቆመ ጽፌም አላውቅም በጀርመንኛ።   ታሪኩ ዕውነተኛ ነው። ቀን አልፎለት በ2016 ደግሞ የቲያትር ሥልጣና ነበረኝ። እና ለኮርሱ የፍጻሜ ዕለት ለህዝብ በቀረበው ቲያትር ላይ ደግሞ በድጋሚ በአማርኛ እና በጀርመንኛ በድምጽ ቀርቧል። ከሥርጉተ ቁጥር ሁለት ዩቱብ ላይ በድምጽ የተሠራው ለጥፌዋለሁኝ፤ ወደ ፊልም የመቀዬር ሃሳቡ ነበረኝ።  እዚህ ሲዊዝ ውስጥ ስትጀመሩት አየር ላይ ነው ትልሙ እንኩት የሚለው፤ ከሃበሻ ጋር ከሆነ። ኢፍትሃዊነት // እናትን ከሠራሁ በኋዋላ ወደ 10 የተዘጋጁ ፊልም ነበሩኝ ግን እንዴት? አያንቀሳቅሳችሁም። መፈናፈኛ የለም ሁለማናችሁ የታሠረ ነው። ምንም አይቀርባቸውም፤ ከእነሱም የሚደርስ የለም ግን ፍዳ ነበር።  የሆነ ሆኖ ይህን ዕቅድ ላይ ተንጠልጥሎ የቀረ አጭር ፊልም ከአንዲት ጀርመናዊ ሲዊዝ ትኖር ከነበረች የራዲዮ ጋዜጠኛ ጋር ነው የሠራነው። የእ

ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።

ምስል
ጥልፍ „ አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን “ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute© Selassie 06.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                                                 በርን ቤተመጻህፍት ባዘጋጀው የሥነ ጥበብ መሰናዶ።  **           ጠብታ! ዘለላ-                የመንፈስ ወለላ                       መዳፈ-ጥልፍ                            ጠፈፍ!                  አልቦሽ ጠረፍ          ብራና ላይ ሲንጠፈጠፍ               ዛላው ሲርገፈገፍ     ጊዜ አይሽረው አይነጥፍ              አይሆን ጠፍ                   ጥልፍ!   ብዕረ ምጥ -የቁርጥ     የቀለም ሰርጥ         ንጥር የምናብ መረቅ ነበልባላዊ መንፈስ አቅልጥ                  ጥልፍ!               የቅመም ውቅጥ             የተግባር ነቁጥ         ወልጋዳን ቆንጥጥ፣ ተባደግን አፍርጥ-ደፍጥጥ            ጥልፍ!    ነው ጥልፍ የኮፒ እንፋሎት፣ ፍ ላ ሎ ----------- ት ሮ ኆ ቦ ------------ ት               ጥልፍ!     ዘይቢያዊ ንቅሳት ነቀል - ተከል፣ የሌለበት                   ቀድሞ የሚያልፍ፣                አይደለም ግርድፍ         ማገሩ አለው ውብ ዘርፍ                  የሚያዘርፍ፤                     ጥልፍ!          ገለባን የሚቀርፍ

የተመስገን ሸጋ ዜና!

ምስል
ሐሤት! „እንሆ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፤  የምትናገሩትን ነገር እስከትመረምሩ  ድረስ ብልሃታችሁ አዳመጥሁ።“ መጽሐፈ እዮብ ፴፪ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie  06.12.2018 ከጭምቷ © ሲዊዘርላንድ          በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!                          „ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናት“                        (ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፤                             ከጠቅላይ ሚኒስተር አሜኑ)                                       ·        „እንዲህም ሆነ ….“ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ልሰራው የነበርኩት ጹሑፍ ነው ዛሬ የምጽፈው። የልጅ አቤል ጹሑፍ መነሻ እረፍት ነስቶኝ ስለነበር። ልጅ አቤል የፃፉት እጅግ ስላስደነገጠኝ የግድ ስለማክበራቸው ዶር ለማ መገርሳ ትንሽ ማለት ስለነበረብኝም። የማልደብቀው በውነቱ በዜናው ደንግጬማለሁኝ። የእሳቸው ከሥልጣን መቆዬት ወይንም መልቀቅ የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ነው። የኦህዴድ ሊቀመንበርነትን ቦታን በፈቃድ መልቀቅ ለዛውም የምልዕት ፍቅር እያለ ገ ድ ል ስለሆነ፤ አፍሪካን የሚያስተምር ብቻ ሳይሆን በትህትናም የሚገስጽ አርምጃ ነበር የወሰዱት። የመሆን የፊደል ገበታ።  40 ዓመት ሙሉ እኮ ከሥልጣን ያልወረዱ መሪዎችን ምድራችን እነሆ አሁን እያስተናገደች ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ በሊቀምንበርነት የቆዩ መሪዎችን ባዕታችን አሁንም እያስተናገደች ነው። የሚገርመው አሁንም መጠቅለሉ ቀረበን ነው መታመሱ ሆኖ በህውከት መገማሸሩ። እነሱ በሰሩት መከራ ነው በእረፍት ዘመን