የተመስገን ሸጋ ዜና!

ሐሤት!
„እንሆ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፤
 የምትናገሩትን ነገር እስከትመረምሩ
 ድረስ ብልሃታችሁ አዳመጥሁ።“
መጽሐፈ እዮብ ፴፪ ቁጥር ፲፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 
06.12.2018 ከጭምቷ©ሲዊዘርላንድ

         በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን!


                         „ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ናት“
                       (ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፤ 
                           ከጠቅላይ ሚኒስተር አሜኑ)
                                   
 
·       „እንዲህም ሆነ ….“
ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ልሰራው የነበርኩት ጹሑፍ ነው ዛሬ የምጽፈው። የልጅ አቤል ጹሑፍ መነሻ እረፍት ነስቶኝ ስለነበር። ልጅ አቤል የፃፉት እጅግ ስላስደነገጠኝ የግድ ስለማክበራቸው ዶር ለማ መገርሳ ትንሽ ማለት ስለነበረብኝም። የማልደብቀው በውነቱ በዜናው ደንግጬማለሁኝ።

የእሳቸው ከሥልጣን መቆዬት ወይንም መልቀቅ የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ነው። የኦህዴድ ሊቀመንበርነትን ቦታን በፈቃድ መልቀቅ ለዛውም የምልዕት ፍቅር እያለ ገል ስለሆነ፤ አፍሪካን የሚያስተምር ብቻ ሳይሆን በትህትናም የሚገስጽ አርምጃ ነበር የወሰዱት። የመሆን የፊደል ገበታ። 

40 ዓመት ሙሉ እኮ ከሥልጣን ያልወረዱ መሪዎችን ምድራችን እነሆ አሁን እያስተናገደች ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ በሊቀምንበርነት የቆዩ መሪዎችን ባዕታችን አሁንም እያስተናገደች ነው። የሚገርመው አሁንም መጠቅለሉ ቀረበን ነው መታመሱ ሆኖ በህውከት መገማሸሩ። እነሱ በሰሩት መከራ ነው በእረፍት ዘመን አሁንም የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባቸው እዬፈሰሰ ያለው።
  
ከዚህ አንጻር በፍልቁ የዕውነት አንባ ዶር ለማ መገርሳ የወሰዱት እርምጃ የአፍሪካን መከራ ተሻግሮ አፍሪካን ያበራም ነበር ማለት ያስችላል። ይህ የዘመን ልዕልና ተግባራቸው ሁላችንም ባለመብት ያደርጋል እንጂ ከኦነግ ብቻ የሥልጣን ቆይታ ፈቃድ የሚያስጠይቅ አይደለምም፤ ሊሆንም አይችልም። ለማ የእኛ ነው እና። ለማም የሁላችን ነውና።  

እኔ እንዲያውም ጎንደር ቢሄዱልኝ እና መነኩሴቷ እናቴ ብድግ ቁጭ ብላ እንድታስተናግድልኝ እሻለሁኝ። የጎንደር ሥነ - መንግሥት የሥርዓት ድባቡ የውስጥ ነው ተፈጥሯዊም ነው። ዓጤ ንጉሥ አባት ከዚህ ዓለም ሲለይ ልጅን ፈልጎ አጤ በካፋን ከትውልድ ስፍራቸው ሄዶ ይዞ አመጥቶ ያነገሰ ልዩ ፍጹም ልዩ ቦታ ነው ጎንደር፤ ቅዱሱን ያሬድ ሆነ ቅዱሱን ፈላስማ ዘርያአቆብ ከብክቦ ተቋሙ አድርጎ ያሰተናገደ ብልህነት ከማስተዋል ጋር የተሰጠው ብጡል ነው ጎንደር። ሊቀ ሊቃናት ባገብቻ ዝምድና አስሮ እዛው ቤተኛ እንዲሆን የሚፈቅድ ሥልጡን ህዝብ የተፈጠረበት ምድር ነው። 

ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም እንዳለው ጎንደር ከመሬት በላይ በሚታዩት ብቻ ሳይሆን በከርሰ ምድርም ገና ያልተተኮረባቸው ብዙ መንፈሳዊ ሃብታት አሉበት። ስለዚህ አሁን እንዲህ ባፍላው ሂደው ጎንደርን ቢያዩት ዶር ለማ መገርሳ ጥብቅ ምኞቴ ነው።
  
የሆነ ሆኖ እብዬ እናቴ ሽሮ በጎድጓዳ ሳህን ትሰራለች፤ የዛሬን ባለውቅም ዶሮ አርቢ ስለነበረች የእንቁላል ፍርፍሩን በጎድጓዳ ሳህን ሰርታ ጥድፍ ብላ ጓደኞቼን ታስተናግድልኝ ነበር። ቃተኛውም ልዩ ነው። የውሃ ዳቦዋም የተለዬ ነው ያሳሳልም። ጓደኞችም የሚወዱላት ይህን የተለዬ አርቷን ነው።

ሥሟም በሞቴ አፈር ስሆን ነው የምትባለው። እና እኔ እስከዚህ ድረስ ውስጤን ከማገኝበት ቦታ ላያቸው ሁሉ እፈቅዳለሁኝ እንኳንስ እንዲህ ኢትዮጵያን በጥርሳቸው በያዟት በኦነጎች ቸርነት እና ፈቃድ የኢትዮጵያን እናቶች /ሴቶች ዕንባ ማድረቂያ ተስፋን ትተው እንዲሄዱ ቀርቶ። መቼም አያደርጉትም ብዬ አስባለሁኝ። ማንን ደስ ይበላው ብለው? እግዚአብሄርም ይህን ክፉ ቀን አያመጣብንም። የሰይጣን ጆሮም ይደፈን። አሜን!

·       ዘመነ መንፈሳዊ ሐሤት!

ሰንበት ላይ የዘንካታዋ፤ የሃብታት ሁሉ ልዕልቷ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐሴታዊ ዜና ነበራት ። የተመስገን ሸጋ ዜና። በጅጅጋ፤ በደብረማርቆስ እን በስሜን ጎንደር። ግጣም ያልተሰራለት የተፈጥሮ መስኮት በጣምራ ፍሉን በጥሞና እያዘናከት እዬለቀቀ ብሥራታዊ ዜናውን በቅደም ተከተል ተከታትየዋለሁ። ሐሤትም አድርጌያለሁኝ።

የራስ ባለደራ ሥነ - ግጥም። (29.04.2018)


በሦስቱም ቦታ የነበረው የአቅባባል ሥርዓተ የቤተክርስትያን ሂደት ልቤን ነካው። እንኳን ለዚህ አበቃን፤ አባቃችሁ። ይህ ቀን ለእኛ ለኢትዮጵውያን የሰላም ዓዋጅ ቀን ነው። ለዓለም ሆነ ለአህጉራችን በረከቱ ለምለም ነው። ጅጅጋ ላይ ቅንብሩ በኦሮምኛ በተዘጋጀው ዜማ ስለነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር በ ኦሮምኛ የቅድስት እናቴን ቤተክርስትያን ዝማሬ ያዳመጥኩት። እናም ልቤ ተነካ። 

በፍጹም ሁኔታ ተመሰጥኩኝ። ይህ ሁሉ ሃብታት፤ ይህ ሁሉ ጣዕመ ዜማ፤ ይህ ሁሉ ህሊናን የሚገዛ ቃና ያላት አገር ኑራን ፍቅር ነስቶን እንሆ አሁንም እንተራመሳለን። ይህን ለማጥፋት፤ ይህን ለማውደም ሌት ተቀን እንባዝናለን። አለመታደል። ይህ ጸጋ እኮ ገብይ ተሂዶ አይሸመትም። የትምም ዓለምም አይገኝም። በአስመጪ እና ላኪ ህግም አይገዛም። ርቁቅ ቅደመ አያቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተመርተው ያጎናጸፉን ተዝቆ የማያልቅ የመንፈስ ስጦታ ነው። ዋ! ቅድስት ሃይማኖቴ እንዴት ያምርሽ ነሽ?

                              የክፉ ቀናችን አጽናኝ ቅዱሳችን! 


MUST WATCH የሶማሌ ክልል ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብጹዕ

አቡነ መቃርዮስ በኢትዮ ሶማሌ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል   


https://www.youtube.com/watch?v=TYbuJv8BFjo

MUST WATCH የሶማሌ ክልል ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብጹዕ

አቡነ መቃርዮስ በኢትዮ ሶማሌ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል


በኦሮምኝ የቤተ እግዚአብሄርን መዝምሩን ስሰማ የተሰማኝ ስሜት የኤርትራ ልዑክ ቦሌ ሲገቡ የተሰማኝ የማላውቀው ስሜት ያልኳችሁ ዓይነት ነበር። አቤት እንዴት ነፍስን እንደሚገዛ፤ አቤት እንዴት ሩህን እንዲሚያስተዳደር፤ አቤት እንዴት ነፍስን እንዴት እንሚያፍነሸንሽ ልነግራችሁ አልችልም። ቃናው አይጠገብም። ለዛው አይጠገበም። ጣዕሙ ልቀቁኝ አይልም ወደ 10 ጊዜ አዳምጨዋለሁኝ።  

ጅጅጋ የሄዱት አርበኛው መንፈሰ ጠንካራው ጽኑው አባታችን ብጹዕ አቡነ መቃርዮስ ናቸው። በቀደመው ጊዜ የካናዳ እና የእዬሩሳሌም አገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፤ አሁን ደግሞ ለሱማሌ ክልል አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመዋል። 

እኒህ አብነታዊ አባት ለእኔ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ አቡነ ሚኬኤልም ናቸው ማለት ያስችለኛል። ብጹዑ አቡነ አብርሃም እንዲሁ አያነሳቸውም አርበኝነት። የቀደሙት ሰምዕታት አገራችውን በጸሎት ብቻ ሳይሆን እናታቸው እምዬ ኢትዮጵያ የጠየቀቻቸውን ሁሉ ሰጥተው ነፍሳቸውን ገብረው ነው ዛሬን የሰጡን።

የዛሬዎችም ስደት ቢያንገላታቸውም ግን በውጭ ለተበተኑት የቤተክርስትያኗ ልጆች ሳይጎድልባቸው ሙሉ አገልግሎት እና ሐሴት አጎናጽፈው እንሆ ተልዕኳቸውን እሱ አማኑኤል በትቡቡ በመልካም እርካብ አሳረገው።
 ተመስገን።  

ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ቀደም ባለው ጊዜ ነፃነት የራባቸውን አርበኞች ኤርትራ ድርስ ሄደው እንደ አባት አደሩ ልጆቻቸውን ባርከው፤ አጽናንተው፤ አዬተው ነበር። እኒህ አባት አስታዋሽ ያጡትን፤ ከመከራ ጋር የባጁትን፤ ጥቁር ልብስ የለበሱትን የጅጂጋ ምዕመናን እንደ ጸጋቸው፤ እንደ መክሊታቸው ለቦታው መመረጣቸው የሰማይ ተግባር ነው።

የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሰጡፋ ዑመር ለዛ ቦታ መታጨታቸው ታምር እና ዕጹብ ድንቅ እርምጃ እንደ ሆነው ሁሉ አሁንም እኒህ ቅዱስ አባት ለዛ ቦታ መመረጣቸው እዬራዊ ነው። ብዙ ነገር ይሰክናል።  

ስለምን? ፈቃዱ የእግዚእብሄር ነውና። ሁለቱም ስደተኛ የነፃነት አርበኞች ብፁዑ አባታችን አቡነ መቃርዮስ እና አቶ ሙሱጡፋ ዑመር ዕድለኞች ናቸው። ቋንቋ አላቸው። ቋንቋው እራሱ ማህንዲሳቸው ነው። የስደት ኑሮ ቋንቋው በራሱ ጊዜ የመንፈስ ሃዲዱን ያስተዳድረዋል፤ ይመራዋል፤ ይገራዋል። ስደት የጫጉላ ሽርሽር አይደልመና። መገፋትን መገለልን ተጸይፈው ስደትን እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደው ጽጌን በምግባር ያበለጸጉ ጉልላቶች ናቸው።

እኒህ አጽናኝ አባት ለዛ ከ9 በላይ ለተቃጠለ አብያቴ ቤተክርስትያናት፤ እነዛ ለተፈለጡ፤ ለታረዱ፤ ለተቃጠሉ ሰማዕታት ሁሉ የጸጋ ስጦታ ናቸው። ካሳም ናቸው። ትክክለኛ ቦታ ነው። እኔ እንደማስበው እኒህ ቅዱስ አባት ጸጋቸው ማጽናናት ነው። እናም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔም ሰውኛ ነው ብዬም አላስብም፤ በፍጹም። ድስት ግጣሙን እንዲሉ … የመንፈሱ ረቂቅነት ለ ዕድምታ ባለጸጋዎች ልተወው። 

የተጋባውን ሰው ወደ ተገባው ቦታ ለመላክ መወሰኑ ረቂቅ ነው። ይህ እንደ ገሃዱ ዓለም ሳይሆን የሚስጢር ዕድምታ አለበት። ለእኔ ብጹዕ አቡነ መቃርዮስ ጅጅጋ ሲደርሱ ሰማዕቱ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡን ጵጥሮስ ከሞት የተነሱ ያህል፤ የቅኔው ልዑል ብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን „ጵጥሮስ ያችን  ሰዓት“ ጋር ነፍሴ ተዋደደች እና ሌላ ፍጹም ሌላ መንፈሳዊ ዓለም ጋር ውህደት ፈጽሙክኝ። ስባንን ለካንስ ከገዳማዊቷ አገር ሲዊዘርላንድ ነኝ። ሁለመናው ምስባክ ነበር።

https://www.youtube.com/watch?v=fBR8nFNpN6M

Petros Yachin Seat by Laureate Tsegaye Gmedhin

ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት ሎሬት ጸጋዬ /መድኅን


ባጋጣሚው እኒህ ቅዱስ አባት ሲዊዘርላንድ መጥተው ስለነበር አይቻቸዋለሁኝ። የሚገርመው ብዕሬን ያውቋታል። እናም ልባቸው መርቆኝ በአደባባይ አመሰግነውኛል። ችግሩ እኔ ከዚህ እስረኛ ስለሆንኩኝ እኒያን ቅዱስ አባት በውጉ አግኝቼ የውስጤን ልነግራቸው አለመቻሌ ነበር። እንዲያጽናኑኝ እማምክራቸው ብርቱ ጉዳይም ነበረኝ።

እንዲያውም የማን እህት መሆኔን ቢሰሙ ራሱ ይገርማቸው ነበር። ይደንቃቸውም ነበር። ወንድሜ ለዚህች ቤተክርስትያን መከፈል ያለበትን ሁሉ ከፍሏል እና። ብርቀቸውም ድንቃቸውም ነውና። የዝምታው ርቀት፤ የጥሞናው ዝልቀት ራሱ ሲያስቡት ለእነሱ አገልጋይነት እንደ ተፈጠረም መንፈስ ቅዱስ ይነግራቸዋል ብዬም አስባለሁኝ ለመላ ስደት ላይ ለነበሩት ብፁዕን ሁሉ።

ያው ከዚህ ሲዊዘርላንድ ውስጥ ቲያትርም ገንዘብ ተከፍሎ ተገብቶ መንፈስ በካቴና ነው፤ ከበላይ አካል ከመጡት ጋር እንደገናኝ አይፈቀድልኝም ነበር በተለይ እኔ። ምክንያቱም ገመነኞች ስለሆኑ። ድፍረቱ ስለሚያንሳቸው። ከዛ የታሰሩትን እናስፈታለን ተብሎ ከዚህ ደግሞ ሺዎች በካቴና ውስጥ ነበርንና። 

ኑ እና ደግፉን ተብለን ተጠርተንም በካቴና ነው። እበሶ እቴጌ ሥርጉትሻ ከሄድኩኝ በጥበቃ ነው ሰው እንዳያገኜኝ። መሄዴን እራሱ አይወዱትም። እጇን  ከአሁን አሁን አውጥታ ትናገራለች ተብሎ በስጋት ነው የሚታዬው፤ ነገም አገር ቤትም ቀጣይ ነው ይህ መሰል ጉዳይ፤ ብቻ ዕድሜ ለሳተናው ጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈረስ ሥሜን በአደባባይ አንስቶታል፤ ያን ጊዜ በውጩ ቤተ መነግሥት ባለሟሎች ራድ ነው የሚሆነው። ውጪ አገርም አጥሩን ጥሶ ከ እነ ፎቶዬ ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅሰተር ሲለጥፍ የመነበረበትን ጫና ያውቀዋል። 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ እኒህ ቅዱስ አባት አቡነ መቃርዮስም ሥሜን በድንገት እኔም ሳላስበው አጉልተው ስላነሱትም የነገሯቸውን ይንገሯቸዋል። ለዛውም ጥሪው የግንቦት 7 ፍነድ ራይዚንግ ነው የነበረው። ከኢትዮጵያ አርበኞች ጋር ተዋህደናል ባሉ ጊዜ ነበር ዘመኑ። አዘጋጆች እነሱው ናቸው።

ለመጀመሪያ ጊዜ ነበርም ሲዊዘርላንድ በተዘጋጀው የግንቦት 7 ስብሰባ ላይ የተገኘሁት። ዓይነ ጠበብ መንፈስ ካለበት ቦታ ድርሽ ማለትን አልፈቅድም። እዛው ያቡኩት እዛው ይጋግሩት። ያን ጊዜ የተገኘሁት በግራ በቀኝ ግንቦት 7ቶች ይዋከቡ ስለነበር በብዕር ሞጋቾቻቸውን አደባባይ ወጥቼ ካለ አንድ ጥግ እሟገትላቸው ስለነበር፤ እና አካሄዴ አይዛችሁም ለማለት ነበር። ግን ለእነሱ ፋይዳ ቢስ ነው ዋጋ የለሽ ምናምንቴ። አለመታደል።  

ብቻ ልቤ እዬፈለጋቸው ሳልጠግባቸው መስቀላቸውን ተሳልሜ ብቻ ነበር ወደ ቤቴ የተመልስኩት። የተሰማኝ አንዳችም ነገር አልነበረም። ተልምዷለኝ። ከእኔ ጋር የበላይ አካል የሆነ ቁሞ ከታዬ ወይንም ሥሜን ካነሳ ዕዳ ከሜዳ ማፈስ ነውና። እራሱ ኦባንግሽ ሲወዚን ከመርገጡ በፊት በኢሜል በሰልክ እንገናኝ ነበር። እርጅን ብሎ ጠይቆኝ ሁሉ ነበር።„ደወል“ የሚል ርዕሰ አንቀጻቸውን በራዲዮ ፕሮግራሜ በመደበኛ አቀርብላቸው ነበር። ሲዊዝ ደርሶ ከሄደ በኋዋላ ግን ኢሜሉ ራሱ በራሱ ጊዜ ተቋረጠ። አላዘንኩበት የተለመደ ስለሆነ። ክፉዎች ምን እንደሚሏቸው አላውቅም። 

እኔ ሥራቤት ቤተሰብም አላሰደገኝም፤ እኔም አይደለሁም ወይንም ጎርፍ አምጥቶ የከመረኝ ፖለቲከኛ አይደለሁም፤ መደበኛ ቋሚ በሆነ በፖለቲካ ድርጅት ጽ/ቤት የክ/አገር የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት አደራጅ ነኝ። በቃ!

የግራ ፖለቲካ ማዶ ላይ ተቀምጦ ነው ለነፃነት የሚታገለው። ማለት ህዝብን አቅምን እንደ ጦር እዬፈራ። ወይንም ልምድ ያላቸውን ሰዎች አሸሽቶ ብቅ እንዳይሉ ቀብሮ፤ አቅማቸውን እንኩት አድርጎ ስም በማጥፋ ሰባብሮ እያሳደደ ነው ዴሞክራሲ የሚለው። ተረበኛ! አሁን ከሆነ ይልቅ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህችን ነገር እዬነካኳት ነው። ጠለቅ ብለው ቢገቡ ስንት ገማና አለ። እግዚአብሄር ይመስገን አሁን መሬት ላይ መተያዬት ነው። 

እኔ ለለማ ለአብይ ለገዱ ለደመቀ ለአንባቸው ለፍርያት መንፈስ እምነገረው ይህን የመንፈስ ካቴና ከእስር እንዲያስፈቱ ነው። እነሱ በጓዳ የሚሏቸውን እንዳያዳምጡ ነው። አገር የገቡት ከነገመናቸው ነው። አሁንም እነሱው ስለሆኑ ባለሟሎቹ የቅርቦቹ እና አማካሪዎቹ። እነሱም እራሳቸው የለውጥ አራማጆች አይድኑም። ያ በሽታቸውን እንዳያሻግሩት መሬት ላይ ባሊህ ሊሉት ይገባል ባይ ነኝ። ብዙ አቅም ነው የሚበተነው። የተቋሰለ ነው ሁሉም።

ፊት ለፊት ባገኛቸውም አሳሪዎቼን በአደባባይ ለመናገር ግንባሬን አላጥፈውም እኔ የሥላሴ ባሪያ ሥርጉተ ሥላሴ ከፈጣሪዬ በታች ማንንም ምንምም አልፈራምና። ጠፈፍ ክውን ያልኩ ስለሆነም የማፍርበት አንዳችም የታሪክ 
ጉድፍ የሰብዕና ዝበት የለኝም ኑሮኝ አያውቅም። ያጣሁትም ነገር የለም። 

አንገቴን ቀና አድርጌ በሠራሁባቸው ቦታዎች አርሲ ጢቾ እና ጎንደር ስሄድ በሙሉ ሰብዕና ነው። አንገቴን ቀና አድርጌ። የሚያሸማቅቀኝ አንዳችም ነገር የለም። የተቀጣ በፍጹም ሁኔታ የልባለቀ እና የታረመ ስብዕና ነው ያለኝ። ትናንትም ይሁን ዛሬ። በስደትም ልክ በወጣትነቴ የነበሩ ሙሉ ተፈጥሮዬን አክብሬ ነው የምገኘው። ለዚህ ነው እኔ ነፃነት ፍለጋ የሚባለው ስለማይገባኝ
ፊት ለፊትም ነኝ ያለውን ሁሉ ባለው ልክ መሆን መቻሉ እና አለመቻሉን ደፍሬ እምናገረው። ወደፊትም!

የሆነ ሆኖ እኔ ከጎንደር ዓርት ዓይናማ ሊቀ ሊቃውንታት ቤተስብ የተፈጠርኩኝ ነኝ። ለቤተክርስትያን ባይታዋርም አይደለሁም፤ ብርቄም አይደለም። ሊቃናተ ቤተክርስትያን ከሥራቸው ሆኜ ነው ያደግኩት፤ ነዳይን አደግድገው ድንኳን ጥለው ፍሪዳ ጥለው ገናን ከሚያገድፉ ቤተሰብ ነው የተፈጠርኩት። ይህን ደግሞ ጎንደር አሳምሮ ያውቃል። ዛሬ አያቶቼ ባይኖሩም ተውፊቱን የሚናገሩ፤ የሚያውቁ ሊቀ ሊቃናት ጠበብት ግን ይነራሉ። ስለዚህም መንፈሳቸው በአፀደ ነፍስ አብሮኝ ስላለ ሆድ አይብሰኝም። ብታገደም፤ ብገፋም፤ ብገለልም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መረብ በዚራጋም ከዚህ አገር።

 በዚህም ምክንያት ነበር እኔ እኒህን ቅዱስ አባት ብጹዑ አቡነ መቃርዮስን እንዳ አሳቤ እና እንደ ልቤ ላገኛቸው ሳልችል በልቤ እንደቀሩ የቀሩት። „የቴውድሮስ ራዕይ“ ጊዜም አርቲስት አለምጸሐይ ወዳጆን፤ አርቲስት ጌትነት እንዬውን ማግኘት አልቻልኩም፤ ይዤላቸው የሄድኩትን እቃ እራሱ ይዤው ነው የተመለስኩት፤ ከፍለህ ገብተህ በጥበቃ በወታደር ነው። ዓለም እንዲህ ዓይነት ጉዳ ጉድ አስተናግዳ አታውቅም። 

ሥርጉተ ሥላሴ ሥሙን ስለምን እንዲህ እንደ ጣውንት እንደሚያዩት አላውቅም? መደገፍ ሲኖርባቸው እነሱንም ደግፌያለሁኝ፤ ሊወቀሱ ሲገባቸው ደግሞ ይነገራቸዋ፤ል ይህን ከፈሩ ክውን ብሎ መቀመጥ ነው። ነፃነት የምላስ ድርሳን አይደለም ዴሞክራሲም የላንቃ ድንጋጌ አይደለም፤ ነጻ ሆኖ የተወለደውን ተፈጥሮ አለመጫን፤ አለማሰር አለማግለል ተፈጥሮን አለመጻረር ማለት ነው ነፃነት። 

ለዛውም እኔ እኮ ሲበዛ ቁጥብ ነኝ። ሁሉ ሰው ይህን ያውቃል። ድብልቅ ድብልቅ በእኔ ቤት የለም። አንዲህ ዝንቅ ዝንቅ የለም በእኔ ቤት። ሁሉም በልክ እና በፈርጁ ነው። 

የሚገርመው ሌላው ቀርቶ ዜና ለመሥራት እንኳን ለሌላው ተፈቅዶ „የቴወድሮስ ራዕይን“ ፎቶ ማንሳት እንኳን አልተፈቀደልኝም ነበር፤ ያዘጋጀውም ያው አቤቶ ግንቦት 7 ነበር። የተቆለፈ የተከረቸም የተኮረኮደ መከራ ነው ከዚህ የነበረው። በአጥር በክትር በግድብ ነበር ዜግነት። ሁሉንም ቦታ ተቆጣጠሪዎች እነሱ ነበሩ፤ በዬት ሰው ይንቃሳቀስ? በዬት መፈናፈኛ ያግኝ? የተዳፈነ ጉድ።

በመንፈሳዊ ሲኬድ እነሱ ካልመሩት አይሆንም፤  በሥነ ጥበብ ሲመጣ እነሱ ካልደወሩት አይሆንም? በፖለቲካ ሲመጣ እነ አቤቶ ካልፈቀዱት ውገዘ ተርዮስ ነው እገዳ ነው እቀባ ነው፤ ታዲያ ነፍሳችን የት ላይ እራፊ አዬር ታግኝ። በግልም ሲሞከር አይቻልም በስል ገብተው ፍርሰርሱን ያወጡታል። የአኳርዬስ ኮከብ ያለበት ይመስለኛል ግንቦት 7።  

መጸሐፍ ያጽፋል የሆነው ሑሉ። እነሱ ከሚጠሩት ስብሰባ በጓደኛዬ አስገዳጅነት ስገኝ የነበርብኝ ግልምጫ ፍዳ ነበር፤ ንጹሁ ታዳሚው ደግሞ ያደርግልኝ የነበረው ቁልምጫ ደግሞ ልዩ ነበር ከመቀመጫዬ ድረስ እዬመጡ ነው የሚያገኙኝ ወገኖቼ። ሰብዕናዬን ያወቁታል ሙርቅርቅ አለመሆኑን። 

ከእንግዲህ እምየዋ ሲዊዘርላንድ ከእስር ተላቃ ሰው ከሰው የሚገናኝበትን ዘመን እንዲሆንላት እመኛለሁኝ። በብዙ ሁኔታ እስርኛ ነበርኩኝ። ስለምን ሰው ከእኔ ጋር በዬዘመኑ እንዳይገናኝ እንደሚፈለግ እራሱ አይገባኝም። አቤት የሰላዬ ብዛት ብርጌድ ያለኝ ይመስላቸዋለኝ። ብዕርና ወረቀት ብቻ ነው እኔ ያለኝ። ከፈጣሪዬ ትምክህት ውጪ ሌላ ምንም የለኝም። እሱ ግን የፈቀድኩትን የለመንኩት አድርጎልኛል። አሁን ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት። 
   
ብቻ … ያ ፍጡር ጠል የሆነ የግራ ዘመም የምቀኝነት፤ የሸር፤ የስጋት ቋት፤ 
የቡቃያ ጸር፤ የኢጎ የስስታምነት ዘመን እያለፈ እዬጣላቸው እዬሄደ በመሆኑ እጽናናለሁኝ። እኛም ከስደት ውስጥ ሌላ ስደት የነበረነው ሁነኛ ባለቤት ያልነበረን ዜጎች የልባችን መሻት አይቶ ሁሉንም ቁጭ ብለን እያሳዬን ነው።

የሚበልጡ የሚልቁ የሚያቅፉ የሚወዱ የልባችን መሠረት ስላገኘን 
ስላለፈው የጨለማ ዘመን ሳይሆን፤ ስለመጪው ብሩኽ ዘመን ማሰብን 
ለማግኘት ነበር ያለፈው ዓመት የዕጣ ነፍስ ተጋድሎዬ። ተጋድሎዬ እንዲህ አስብሎ ኢትዮጵያዊው ባለቤት ያልነበረው ማለቴ ነው በመንፈስ የታሰረው ሁሉ ከካቴና ጋር እንዲፋታ ነበር ትጋቴ። የሆነውም ይኸው ነው። ሲያብጠለጠሉ፤ አትችሉትም ሲባሉ የነበሩት ሊሂቃንም ዛሬ የት እናግኛችሁ ሆኗል። ምልጃ፤ የሚቀርብ ሰው ፍለጋ ነው አሁን ጥድፊያው። ተመስገን ነው።

እናም የሆነው ሁሉ ነገር የታምር እስኪመስል ድርስ እኔ በተመኘሁት፤ በሻትኩት፤ በፈልግኩት ልክ የልቤ ደርሶልኛል። ኢትዮጵያ አዬሯ፤ ትውፊቷ፤ ቤተ መንግሥቷ የሁሉም እንዲሆን ነበር ምኞቴ አንዳችም ነገር ሳይጓደልበት ከህልሜ እንሆ እንደ ተመጸንኩት ሆነልኝ።

ሁሉ እኩል የሚሆንበት፤ የማይስዳድበት፤ የክት እና የዘወትር የምይለይበት፤ ዜጋ ልጅ እና እንጀራ ልጅ የማይልበት ካሻን ጋር ቁመን ተቀምጠን ሲያስፈልግም ጋዳም ብለን ሳንጨናነቅ የምንወያይበት፤ የምንነጋገርበት፤ የግል ሰላይ አልባ ህይወታችን የምንመራበት ዘመን ነበር የናፈቀኝ ይህን አድርጎልኛል። አንድ ጊዜ ተሜ አዲስ ፊት ናፈቀኝ ሲል ከዚህ ሁኜ እስቅ ነበር። ሥምም ስለሰጠ። ብቻ የልቤ ደርሷል። ሃሳቤም በላቀ ልዕልና አሸንፏል ተወደደም ተጠላም።

ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ልዑሌን አመሰግነዋለሁኝ። የታለፈው ዘመነ ጨቀጨቃማ፤ ጭጋጋማ፤ ዝጋጭ ጨለማማ፤ ቅርጭጭታም ቀዝቃዛ ዘመን ነበር። ይህን እኛ ውጭ አገር የባጀብን መከራ አገር እንዳትሸከም ያደረገው አዶናይም የተመሰገነ ይሁን። ድቅድቅ ነበር። እርሃብን የሚያውቀው የተራበው ብቻ ነው። 

ዲሲ ላይ ተሆኖ የሲዊዝ ስቃይ ለመናገር እኛን ይጠይቁን። ቋያ ነበር። ስንገበገብ ስንታደን ነው የኖርነው። ሥማችን ተቀብሮ እንዲቀር። እኔ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ማህበርተኞቹ ኢንባሲውን ጨምሮ መደበኛ ሥራው ነው ቢያሳድደኝ፤ ለዴሞክራሲ ለነፃነት የሚለው ግን ቃሉን ለመናገር አቅም እንደሌላቸው እነሆ እነግራቸዋለሁኝ። የዛሬዋን እድል ቢያገኙት የመከራ ቀን ይታወጅ ነበር። ቅናት እና ምቅኘነት ቅንነትን ወልደው ትወልድን ከብክነት አያድንም። 

ይልቅ ራስን ማሸነፉ እና ስለምን እንደሚታገሉ፤ ስለምንም ዘመናቸውን እንዲያቃጠሉ አደብ ገዝተው እራሳቸውን ያደምጡት ዘንድ በትህትና አሳስባቸዋለሁኝ። ነጻነትን በማታለል አይገኝም፤ ነፃነት በማዳፍ ላይ ስላለው ነፃነት ለሌላው መስጠትን፤ መፍቀድን ይጠይቃል፤ ሌላውን ስትተች የራሰህንም አቅም መለካት ያስፈልጋል። 

እዚህ ያለገኘሁት ዴሞክራሲ፤ እዚህ ያልተሰጠኝ ነፃነት አገር ቤት ያለውም ዜጋ ያገኘዋል ብዬ አላስብም። መሬት ላይ ነው ሥራ ያለው እንጂ ሞገድ ላይ አይደለም። ሰው ብሎ መነሳት ያስፈልጋል።  

መከራን የደፈሩ የተዳፉሩም ብጹዑ አባት ያን ጊዜ የካናዳ እና የእስራኤል ሊቀ ጳጳስ ነበሩ አቡነ መቃርዮስ ከዚህ ሲዊዘርላንድ መጥተው ጸጋዬን የመሰለ ራዲዩ እያለኝ ለደቂቃ ቃለ ምልልስ ሳለደርግላቸው ቢመለሱም ዓይናቸውን ማዬቴ ግን ትልቅ በረከት ነው። እንዲያውም ጎንደሮች „ወግ  በዓይን ይገባል“ አይደል የሚሉት። እንደዛ። መንፈሳቸውን ልከውልኛል።

ለመንፈሳዊ ሰው መንፈሱ ራሱ በቂ ነው። ሴረኞቹ ያሏቸውን ቢሏቸው በሰተጀርባ ሥሜን መድረኩ ላይ ልክ እንደ ደፋሩ ጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈረስ ስላነሱ፤ እኒያ ብፁዑ አባት በብእሬ ሞገድ ብቻ ሳያዩኝ ያመኑኝን ያህል ዛሬም ያሏቸውን ቢሏቸው በልባቸው ጽላት ውስጥ ቦታ እንደሚኖረኝ አስባለሁኝ፤ አምናለሁኝ።
እና እኒያ የልብ የሆኑ አርበኛ እና ትጉኽ ቅዱስ አባት ናቸው ጅጅጋ የተገኙት። ጥሪውም አዮራዊ ነው። እናም አብዝቼ ሐሤት አደረኩኝ። 

መከራን ችግርን ኮረኮንችን ጠጠራማ ዳገትን የሚፈቅዱ ሰብዕናዎች ክብሬ ናቸው። እኔም ደልዳላው አያሰኘኝም፤ ቆርጮ እምገባበት ሁሉ መከራን የሚጭን ነው። ግን ጥሼ እወጣለሁኝ። ተሸንፌም አላውቅም። በፈተና ሰልጥኝበታለሁኝ ማለትም ያስችለኛል። 

ለዚህም ነው በወያኔ ሃርነት ትግራይ አዋራነት ይመራ በነበረው በቀድሞው ቅርፊቱ ኢህአዴግ ውስጥ እነዛ የዘመን ፈርጦች ያን ያህል ተጋድሎ አድርገው ዕውቅና ሲነፈጋቸው፤ "ከመለሳውያን ወደ ለማውያን" ተብለው ሲብጠለጠሉ የሽግግር መንግሥት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንድነት መንግሥት ይመስረት የሚል የሸር የደቦ ዘመቻ ሲስተጋባ የመመከት ትጋት ላይ የባጀሁት። የፈውሱ ነጋሪት ጎሳሚዎች እነሱ ናቸው ተወደደም ተጠላም። 

የአማራ የህልውና ተጋድሎ መጥራት ጠያፍ በነበረበት ወቅት ዛሬ ዲሲ ላይ
ደግሞ የምናዬውን እያዬን ነው። የብአዴን መሪዎች እንደ ታቦት እየተከበከቡ ነው። ተመስገን ነው! አማራ ነኝ ማለት ወንጀል ነበር። የአማራ ተጋድሎን በሥሙ መጥራት፤ ማንሳት ደፋሩን ጋዜጠኛ ሁሉ የፈተነ ተጠቅልሎ የቀረ መከራ ነበር። አሁን ተመስገን ጊዜ ታሪክን እንሆ ሠራ። መከራውን ጥጥት አድርገው ነው ዛሬን ያበሩት እዛው መሬቱ ላይ የሚገኙ ታጋድሎውን ያደመጡት ጀግኖች ናቸው። ያን አንበሳም ኮ/ ደመቀ ዘውዱ አብሪውን ኮከብ አሳልፈን ለበላህሰብ እንሰጥም ብለው የመይሳውን ክብር ያስከበሩት። ይህ ብቻ ይበቃል። 

ሁሉንም ነፃ ያወጣ ተገድሎ ነው የአማራ የህልውና አብዮት፤ ለመንፈስም
 ምቹ ማሳ የተገኘው በዚህ ረቂቅ እዮራዊ ምርቃት ውስጥ ነው። እናም 
ቅድስት ተዋህዶ እንደ ትውፊቷ፤ እንደ ውብ ለዛዋ፤ እንደ ማራኪ ትሩፋቷ፤
 እንደ ጥልቅ ፍልስፍናዋ፤ እንደ ሙሉዑ ሰማያዊ ክኸሎቷ የድርሻውን 
ትወጣ ዘንድ ....
                                   የዛ የጨለማ ጊዜ ጧፍ!

ብጹዕ አባታችን አቡነ አብርሃምም ዕጣ ነፍሳቸውን በዛ ጭንቅ ጊዜ፤ ለሰይፍ አንገታቸውን ለመስጠት ቆርጠው በአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎ ላይ ያሳዩት ቆራጥ፤ ደፋር፤ እውነትን የወገነ የሰማዕትነት የአርበኝነት ውሎ ዛሬን ልክ እንደ ፈርጣማ ፖለቲከኞቹ ቦግ አደርጎ የልባችን ደርሶ እንሆን አዬን። እንደሰማነው ሆነልን። ተመስገን!


ብጹዑ አባታችን አቡነ ዮሐንስ የስሜን ጎንደር አገር ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው አዲስ የተሾሙት፤ በአቀባባሉ ላይ ለተገኙት ምዕመን እንዳሉት የሆነው ሁሉ „ከትርጉም በላይ ነው“ የሆነው ሁሉ፤ የሚሆነው ሁሉ፤ የምናዬው ሁሉ ልዑል እግዚአብሄር መሬት ወርዶ የሠራው ነው የሚመስለው።

መከራን የደፈሩ ሰማዕታት ብፁዐና አባቶቻችን፤ ቅዱሳን አርበኞቻችን እንደ አውቶብስ ባለክንፉን እደጃቸው ድረስ ልኮ በሙሲያቸው ከብካቢነት በክብር እና በሞገስ ነበር ያችን ቅድስት ምድር የረገጧት። ያችንም እናት ምድር ሲረግጡ መንፈሱ ራሱ የባለቤቱ የመንፈስ ቅዱስ ነበር። እዬባዊነትን ከሰነቅ ሁሉም እረብ ይላል። መጪው ዘመን የዕውነት ነውና።

ይህን ታላቅ የሰማይ ሥጦታ ማቃለል ይሆናል በሆነ ባልሆነ አንዳንድ መረጃዎችን ከዚህ እና ከዚያ የሚራወጡት እንጂ እጅግ ጥልቅ ምጥቅ የሆነ ሽልማት ዘመን ለቅድስት ኦርቶዶክስ የሸለመበት ዘመን ነው። ሁሉም ነገር ግድፈትም ቢፈጠር ከዚህ ባለይ ሊሆን አይገባም። ቁርጡ ጉዳይ አሁን ምዕመኑ አህቲ ነው። 

የተዋህዶ ልጆችም ለዚህ ዘመን አጥር እና ክትር በመሆን፤ ጋሻ እና ዘብአደር በመሆን ሌት ተቀን መትጋት ይጠበቅባቸዋል። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሁን ከልዕልናዋ፤ ከመንበሯ ላይ ነው ያለችው። እባካችሁ ሰውኛ አንሁን? የገሃዱ ዓለም ብልጨልጭ እርምጃ የእዮርን ታምር እንዳይፈትን አብዝተን እንጠንቀቅለት። ምርቃት በወጉ ካልተያዘ ይነሳል። ተመስገን እንበል።  

የብፁዕን ቅዱሳን ሰምዕታት አርበኛ አባቶቻችን አዲሱ የአግልግሎት ቦታ፤

v   ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የሱማሌ ክልል አገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ  ሆነው ተሹመዋል።„የፈረሱትን የእግዚአብሄር ማደሪያዎች እንሠራቸዋለን“
ብጹዕ አቡነ መቃርዮስ በጅጅጋ ከተማ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባባእል
Afaan Oromo
8,522 views
2656SHARESAVE
Published on Dec 3, 2018

v   ብፁዕ አቡነ ዮሖንስ የስሜን ጎንደር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል። „የሆነው ሁሉ ከትርጉም በላይ ነው።“
ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሰሜን ጎንደር ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል

ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሰሜን ጎንደር ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል

Published on Dec 3, 2018
v   ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምሥራቅ ጎጃም አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመዋል።  „እናንተን ለመታዘዝ ከፊታችሁ ዛሬ ተገኘሁ“

ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ - የምስራቅ ጎጃም አዲስ ሊቀ ጳጳስ በደብረ

ማርቆስ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Published on Nov 18, 2018

በስሜን ጎንደሩ እና በምስራቅ ጎጃሙ የአቀባበል ቤተክርስትያናዊ ሥርዓት ላይ ብፁዑ አባታችን አቡነ ባርናባስ አበረው ተገኝተዋል። 
                                        የስብከት እጬጌ!
አብሶ የትውፊቱ ቀጣይነት አስብሎ ስላገኙት ደሰታቸው ወደር የለውም። ብፁዕነታቸው ገበሬው የሐብታችን፤ የትሩፋታችን፤ የትውፊታችን የቅድሰት ቤተክርስትያናችን አንጡራ ባለውለታ ስለመሆኑ አበክረው በአጽህኖት ገለጣዋል። ብፁዕን አባቶቻችን እንኳን ለዚህ አበቃለን አዶናይ። ተመሰገን!

                         "እንሆ ቃላቶችህን በትዕግስት ጠበቅሁ"
 
ተመስገን!

                              ወስብሃት ለእግዚአብሄር።






አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።