ልጥፎች

ከኦክቶበር 17, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እኮሳ!

ምስል
እኮሳ ! ወደ ዬት ? „ከሱም የተነሳ ባንደበቴ ነገር ተነገረ፤ ምድርም ጠፋች ብዬም እጮኽ ነበር።“   መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ 17.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የራስ ተሰማ ናደው ቅኝተኛ ቀኝ ጌታዎቻችን። ·        እኮሳ!  ወደ ዬት ጥሩ ጥያቄ ነው። አሁን በምናዬቸው ምስቅልቅሎች አንዳንድ ጊዜ ድንጋጤ እንዳንድ ጊዜ ብስጨት፤ አንዳንድ ጊዜ ሀዘን ይሰማናል። ስለምን ቢባል አዲስ ሥርዓት ለመፍጠር ያለን ተስፋ እና ጭብጡ የሚነግረን ድብልቅልቅ፤ ውልቅልለቅ ያለ ድንገቴ መረጃ መላ ከማጣቱ የተነሳ ነው። ብዙ ነገሮች ዝንቅ ናቸው። የእነኝህ ቀውሶች መነሻ ያው የራስ ተሰማ ናደው የሴራ ምህዋር ሲሆን ነጠል አድርገን ለማዬት ግን እኔን በሚገባኝ ልክ ትንሽ ልፈትሽው። ለነገሩ እኔ ከሰሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ የሆነው በአባ ዝምታ የሐምሌ ዕድምታ ብዙ ኮልሚያለሁኝ። አማራን በተመለከት ምንግዜም ያው ነው። ብዙም አልጠበቀነም ባልጠበቀነው ልክ የሆነውን ከዕለቱ ጀመርነን ታዝበናል። አንቦ ይናገር! ግን ዛሬም ትንሽ በተያያዘ መልኩ ልበል፤ ቀውሰኞች በጅረታቸው እስኪ ይፈተሽ … ·        ቀድሞውንም የወያኔን ዓላማ ሲያራምዱ የነበሩ ግን ተጋሩ ያልሆኑ በፍጹም ሁኔታ የአብይን መንፈስ የማይፈቅዱ አሉ። እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አይነት እነኝህ ከአኩራፊው ማህበር መዶል እንችላለን።   ·        በፍጹም ሁኔታ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው አሉ ማህበረ ተጋሩ ብቻ ሳይሆን የማህበረ ተጋሩን ስሜት የሚጋሩ። እንደ ሳጅን በረከት ስምዖን አይነት። ·        በዛ በሽግግር ዘመን አብረው ሆነው