እኮሳ!

እኮሳ!ወደ ዬት?

„ከሱም የተነሳ ባንደበቴ ነገር ተነገረ፤
ምድርም ጠፋች ብዬም እጮኽ ነበር።“
 መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፳፱ ቁጥር

ከሥርጉተ© ሥላሴ
17.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
የራስ ተሰማ ናደው ቅኝተኛ ቀኝ ጌታዎቻችን።




·       እኮሳ! 
ወደ ዬት ጥሩ ጥያቄ ነው። አሁን በምናዬቸው ምስቅልቅሎች አንዳንድ ጊዜ ድንጋጤ እንዳንድ ጊዜ ብስጨት፤ አንዳንድ ጊዜ ሀዘን ይሰማናል። ስለምን ቢባል አዲስ ሥርዓት ለመፍጠር ያለን ተስፋ እና ጭብጡ የሚነግረን ድብልቅልቅ፤ ውልቅልለቅ ያለ ድንገቴ መረጃ መላ ከማጣቱ የተነሳ ነው። ብዙ ነገሮች ዝንቅ ናቸው። የእነኝህ ቀውሶች መነሻ ያው የራስ ተሰማ ናደው የሴራ ምህዋር ሲሆን ነጠል አድርገን ለማዬት ግን እኔን በሚገባኝ ልክ ትንሽ ልፈትሽው።

ለነገሩ እኔ ከሰሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ የሆነው በአባ ዝምታ የሐምሌ ዕድምታ ብዙ ኮልሚያለሁኝ። አማራን በተመለከት ምንግዜም ያው ነው። ብዙም አልጠበቀነም ባልጠበቀነው ልክ የሆነውን ከዕለቱ ጀመርነን ታዝበናል። አንቦ ይናገር! ግን ዛሬም ትንሽ በተያያዘ መልኩ ልበል፤ ቀውሰኞች በጅረታቸው እስኪ ይፈተሽ …

·       ቀድሞውንም የወያኔን ዓላማ ሲያራምዱ የነበሩ ግን ተጋሩ ያልሆኑ በፍጹም ሁኔታ የአብይን መንፈስ የማይፈቅዱ አሉ። እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አይነት እነኝህ ከአኩራፊው ማህበር መዶል እንችላለን።  

·       በፍጹም ሁኔታ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጪ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው አሉ ማህበረ ተጋሩ ብቻ ሳይሆን የማህበረ ተጋሩን ስሜት የሚጋሩ። እንደ ሳጅን በረከት ስምዖን አይነት።

·       በዛ በሽግግር ዘመን አብረው ሆነው አሻራቸውን ያሳረፉ ህገ- መንግሥት ፌድራል ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚሉም አሉ። እንደ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ አይነት። የአሁኑ የኦፌኮን ዕድምታም ይኸው ነው።

·       ተስፈኞች ሥልጣኑ ይገባናል የሚሉ ህልመኞች የኢጎ አርበኞች ራዕዬ ወንበር ትልመኞችም አሉ እንደ …?

·       በሁለቱ የአማራ እና የኦሮሞ ተጋድሎ መንፈስ ለውጥ ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑ በጠ/ ሚር አብይ አህመድ አመራር በፍጹም ሁኔታ የሚያምኑ አሉ። እንደ ዶር አንባቸው መኮነን አይነት ኪዳን ጠባቂ ሰው። አሁን ደግሞ ተንሳፋፊ የሆኑ።  

·       ለውጡን የሚፈልጉ ግን የጠ/ ሚር አብይ አህመድን መንፈስ ጭራሽ ሊያስጠጉ የማይፈልጉ ደግሞ አሉ ለምሳሌ እንደ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አይነት ሰው። ይህ ሃይል ዶር አብይ አህመድ ባይኖሩ ይመርጣል፤ ከኖሩ ግን በሌላ ሃይል መንፈስ እዬተማራ ለውጡ አለ እዬተባለ አቅም እንዲዝል እና የራሱን ተልዕኮ ለማሳካት የሚጥር ሲሆን እጅግ አደገኛው እና ትጥቅ አስፈችም ነው። 

    በሌላ አነጋገር ይህ የጃውርውያንን መንፈስ አዘለ ነው እንደ አርሲና ባሌኛም ያደርገዋል። አሁን ሙሉ አቅም ያለው መንፈስ፤ አሁን ሙሉ ጉልበት አግኝቶ በሚፈልገው መልክ እዬተንቃሰቀሰ የሚገኝ፤ ለኢትዮጵያ እና ለአማራ እጅግ ረግረጉ በእሹህ የተከለለ ጃርታዊ የምህንድስና ጎራ ነው።  

·       በፍጹም ሁኔታ ለውጡ ምንም ሊያመጣ አይችልም፤ ለውጥም የለም የሚሉም አሉ። ዶር አብይ አህመድ አቅም ብቃት ክህሎት ፈጽሞ የማይቀበበሉ እንደ ኢንጂነር ይልቃል፤ እንደ ዶር አበባ ፈቃዴ፤ እንደ ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ አይነት ደግሞ አሉ። እነኝህ ለኢትዮጵያም የተሻለ ለውጥ አለን ባዮች ናቸው። ጥገናዊ ለውጥ አያስፈልግም ባዮች ናቸው።   
·       ለውጡን ብናግዘው ብንደግፈው የተሻለ ሥርዓት መፍጠር እንችላለን ብለው የሚያምኑ ደግሞ አሉ እንደ ኮ/ ጎሹ ወልዴ፤ እንደ ዶር ነገዴ ጎበዜ፤ እንደ ልዑል አስፋው ወሰን አስራተ ካሳ እንደ ዶር ደረሰ ጌታቸው፤ እንደ ፕ/ አለማርያም አይነት። 

   እነዚህ ቅኖች ዶር አብይ አህመድ በ100 ቀናት ባሳዩት ጥንካሬ ልክ አሁንም በህገ መንግሥቱ በተሰጣቸው ሥልጣን ልክ የማድረግ አቅም አላቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው። ግን ያ ተስፋ በምን አይነት ውጋት ውስጥ ስለመሆኑ ጠንቁ የት ላይ እንደ ተፈጠረ በጥልቀት የሄዱበት አይመሰለኝም።  

·       ምን አልባት እኔ ብቻ ልሆን እችል ይሆናል ከሐምሌ ዝምታ በኋዋላ ከስሜን አሜሪካ መልስ ዶር አብይ አህመድ በሙሉ አቅማቸው፤ በሙሉ ክህሎታቸው፤ በሙሉ ጸጋቸው እንዳይሰሩ እንቅፋት የመንፈስ ኩዴታ ተደርጎባቸዋል ብዬ አምናለሁኝ - እኔው። ይህ የተሸፈነ ዱራኛዊ ቅዬሳ እነ ከይሲው ተስፋዬ ገ/ አብ መንፈስን አክሎ ያለ ነው።

·       ሌሎች አማራጮችን እስኪ እንይ ጊዜም ይሰጣቸው የሚሉም አሉ። አማራጭ ስለሚባለው የትኛው አማራጭ እራሱን ችሎ መቆም የማይችል የተፎካካሪ ፓርቲ ነው ያለው። የኢትዮጵያን ዝቀሽ ችግርም እያስተዋለነው ነው። እናም፤ እናማ ይህን ተሸከሞ ሊያሻጋር የሚችል በሁሉም ዘንድ ተቀባይ የሆነ መንፈስ የለንም ነው የእኔ ዕሳቤ።

አሁን የሚመራው በውጭ ድጋፍ በውጭ ሃይል አይዟችሁ ባይነት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በታሰበው መልክ እንደ ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው፤ ወይንም እንደ ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ማሰወገድ ስላልተቻለ የሥልጣን ሽግግሩን ቁንጮ አስገድዶ በሃይለ ለማሰወገድ ስለጨነቀው በቀስታ በዝግታ እዬተራመደ ነው ብዬ አምናለሁኝ።

በአንድ በኩል ህውከት በመፍጠር የነበረውን የዶር አብይ አህመድ የአመራር አቅም እና ሙሉ ተቀባይነት በመሸርሸር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወንጀሎችን ራሱ በመፍጠር እና በመስራት በወንጀሎች አፈጻጻም የተሳተፉትን ሳይሆን የተጎዱትን በማንገላታት አቅም ቢስ አመራሩን አድርጎ በማሳዬት ሥልጣኑን ወደ ሚቀጥለው አካል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ማሻገር ነው የሚሹት።

ይህ ሃይል ዶር ለማ መገርሳ ጠ/ ሚር ቢሆኑ ምርጫው ነው። ገና ያልጨረሰውም የቤት ሥራ አለው። ዶር ለማ መገርሳ የኦህዴድ ቦታውን ከለቀቀ ጠ/ ሚሩ ዙሪያ አንድ ነገር ቢከሰት ቀጣይ ተወዳዳሪ መሆን አይችልም ብሎ ስለሚያስብም ቦታው በሌላ እንዲያዝ አይሻም። ለነገሩስ ማንስ አለ ከሁለቱ ውጪ?

ጠ/ሚር አብይ አህመድን ማስወገድ ካልተቻለ በቀጭን ትእዛዝ የሚፈልጉትን ማስፈጸም ነው። ይህን ደግሞ መሬት ላይ እያዬን ነው። አሁን እሰቡት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ተቀምጠው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ወደ ኤርትራ የሄዱበትን አግባብ፤ እሰቡት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአውራው ፓርቲ ብቸኛው ተመራጭ ሆነው ወደ ኦዴፓ ጉባኤ የሄዱበትን አግባብ፤ እሰቡት አቶ ንጉሡ ጥላሁን የኢህአዴግን ጉባኤ መግለጫ አንባቢ ሆነው የቀረቡበትን አግባብ፤ እሰቡት ሌላ ቦታ አልተደረገም የጠ/ ሚር አብይን ወደ ሥልጣን ሲመጡ OBN ልዩ ቃለ ምልልስ ያደረጉት እሳቸው ነበሩ። 

ቃለ ምልልሱ ራሱ ይጨንቃችዋል ስታዳምጡት። ቃለ ምልለሱ የሞት ዓዋጅ ነው የሚመስለው። ‚ በአገሪቱ ተጀምሮ በአገሪቱ ተጠናቀቀ‘ አሁን እሳቸው የፌድራሉ አፈ ጉባኤ ሊሆኑ ይችላሉ እረግጥ ነው አማራንስ ማን ሰቅዞ ይይዛላቸዋል? የሆነ ሆኖ አፈ ጉባኤው ያ ቢቀርባቸው የጠ/ ሚሩ ቃል አቀባይ ይሆናሉ። ይህም ቢሆን አማራ መሬት ጃዋርውያን አለኝ የሚለው መንፈስ ይህ ብቻ ስለሆነ ሌላ ራስ ምታት ነው የሚሆነው። 

ዶር አብይ አህመድ አኮ አይደለም ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም የበቃ ብቃት ያላቸው ሰው ናቸው። ይህን የማይቀበሉ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁኝ። ይህን ግን እኔ ደፍሬ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁኝ። እኔ እንዲያውም ግዕዝ ቢያጠኑ ኖረ ከዚህም  ይልቅ ነበር እላለሁኝ። ሁሉም አላቸው ሰብዕናቸው ልዩ ነው። 

ከስሜን አሜሪካ መልስ እንደ ሰው ለከፋቸው ዜጎች ተስፋ በመሆን ስልክ ደውለው ማናገር ሁሉ እንዲያቆሙ ተደርጓል። ጳጉሜ ላያ የሆነው ለማዘናገት ነው አብዩ አለ እንድንል፤ ቀዳሚወት እመቤትም ትንሽ ለቀቀለ እንዲሉ ተደርጓል ያን ሰሞናት። አልተጠለፉም እንዲባል ቅኑ ፕ/አለማርያም "አክ ወሬ" ብለው የጻፉት ትክክል እንዲመስል። ይህንን እዬተሠራ ያለውን የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሴራ ላይ ምንጩን፤ ፍሰቱን አጥንቶ በግንዛቤ ደረጃ ለመቀበል እንኳን አልተቻለም። ለዚህ ነው ፕ/ አለማርያም ‚አክ“ ወሬ ማለት ብቻ ሳይሆን ሌላ ማጠናከሪያም ጨምረው የጻፉት።

·       ቢገባን፤ ብንስማማ የጋራ አጀንዳችን እና ትጋት ሊሆን የሚገባው ጉዳይ …

እረፍት ይቀርብኝ 7 ሰዓት እኔ ልስራ እናንተ 61/2 ሥሩ እና ይህችን መከረኛ እናት አገር አንታደጋት የሚለውን፤ ያ የምናውቀው ትንታጉ አብይ ስለጠፋብን ይህን ማፈላለግ በሆነ ነበር። ማስኩን አጋልጦ መንፈሱን ነጻ ማውጣት ነበር። እውነቱን ብናገር ከእንግዲህ አንዲት ነፍስ ኢትዮጵያ እንድትጠፋ፤ አንዲት ነፍስ እንድትንገለታ የአብይ መንፈስ አይፈቅድም። እዬሆነ ያለው ግን አብይ በሌላ መንፈስ አምሳል ሆኖ ከህዝብ ተስፋ ውጪ እንዲንቀሳቀስ እዬተደረገ ነው። ማስካዊ ትዕይንት ነው እያዬን አለውን። ውስጡ ጃዋር ማስኩ የአብይ ፎቶ።

ታስታውሱ ከሆነ አቶ ጃዋር እና መሰሎቹ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ብቃት ዓለምን ሲያካልል ምን ያህል አብደው እንደ ነበር። የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጥተው ነበር። አሁን ዕዴሜ ለአቶ አዲሱ አረጋ እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተሳክቶላቸዋል። ሌላም የውጭ አገር መንግሥትም አለ ብዬ አምናለሁኝ። 

ተናግሯል እኮ አቶ ጃዋር መሃመድ ካልኩሌተሩን እኛ ነው የሠራነው ብሎናል። አሁን በአዲሱ ሚኒስተር እኮ አርሲኛ ነው፤ በኦሮምያ ጸጥታም በኩል መሰሉ ነው እዬታዬ ያለው። 
  • ሴቶች

ሌላው እንዴት ሥርጉተ ሴቶች ሲበዙ ምነው ወይ ተብያለሁኝ። እኔ እኮ ዘመኔን ሁሉ የታገልኩለት ዓላማ ነው። እኔ እኮ በሴቶች አደራጅነት ነበር በፖለቲካ ተግባር አህዱ ያልኩት፤ ከዛም በቀጠለው በሠራተኛ እና በገበሬም አደራጅነቴ ሴቶች ነበሩ ሴቶችን ነበር ወደፊት አማመጣው በዚህም ነው እምታወቀው፤ በህዝባዊ ድርጅቶች እና በሙያ ማህበራት አደራጅነቴም በዚህ ጽኑ ዕምነት ስላለኝ ብቁ ሴቶችን ወደ ፊት ለዬትኛውም ድርጅት አባቃለሁኝ፤ አቀርባለሁኝ።

ሴቶች ቦታ እንዲይዙ መፍቀድ ማለት ግን ሴት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ሴቶች ቦታ እንዲይዙ የምፈልገው ብቃታቸው ሰብዕናቸው የማድረግ አቅማቸው ሁሉ እኩል ከወንዶች ጋር መመጣጠን መቻል አለባቸው ብቻ ሳይሆን ሴቶች አይመጥኑም ተብለው ተገፍተው የኖሩበትን ዘመን የሚክስ የድርጊት አቅም አመንጭተው ሆነው ሲገኙ ነው የሚያስፎክረው ነው የእኔ ቁምነገር። 

ለዛውም ፈርሶ ሲገነባ ተገንብቶ በሚውለው የ ኢትዮጵያ ካቢኔ የሚያስደልቅ ነገር የለውም፤ እስከ ምርጫው አይቆይም ማህል ላይ ጠ/ ሚሩ ሊለቁ ሁሉ ይችላሉ። ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል የመጀመሪያዋ አፈ ጉባኤ በተባሉ ማግስት የመጀመሪያዊያዋ የሰላም ሚ/ር ተብለዋል፤ ሌላዋ ክብርትም የመጀመሪያዋ የመከላከያ ሚር ተብለዋል፤ እንዲያውም የሳቸው ድንገቴ ነው የሚመስለው ምክንያቱም ቀደም ብሎ የታሰበው ሌላ ሰው ነበር። 

ከዚህም ሌላ እኔ ከአንዲት ገዳይ ሴት አንዳችም ውጤት አልጠብቅም። ሰብዕና ገዳይነትን ብቁ ካደረገ ለውጥን በተጻራሪ ሲታገል የኖረን ብቁነት ከሆነ ይህን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያውቁታል። ከዚህ ቀደምም አብይ ሆይ በሚለው በዝርዝር ሠርቸዋለሁኝ። ነገረ ፈትለወርቅን ተሸክመህ 50% ሴቶችን መሪ አደረኩኝ ለእኔ ከእቃ እቃ አያልፍም። ለጊዚው የሚዲያ ሰነድ መገኘቱ አይደለም ለእኔ ቁም ነገሬ ለ እኔ ዕውነት ፈልቆ ማዬት ነው። ስሜት ሳይሆን ፋክት እንዲገዛኝ የወሰንኩኝ ሴት ነኝ። 

በሌላ በኩል ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያትን በሥም አጉልተህ ግን አንተ የምትቆጣጠረውን ሃዲድ ዘርግተህ ሴት አመጣሁ አይጥመኝም። በአቅማቸው ልክ ራሰቸውን ችለው ካለምንም ተጫኝ በክሎህሎታቸው እንዳሳቸው በነጸፃነት የሚሠሩበት አፈ ጉባኤነት ከበቂ በላይ ነበር።

ያን ሁሉ ሃላፊነት አራሱ በ እርግጠኝነት የምናገረው ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት አይወጡትም፤ ሃላፊነቱን ዝርዝሩን ለማንበብም እጅግ ይከብዳል። ይልቅ ምክትል ጠ/ ሚር አደርገው ቢሾሟቸው መልካም በሆነ ነበር። ኦሮምያ እኮ ሦስት ፕሬዚዳንት ሹሞ የለንም? አሁን ሲቸግራቸው ደግሞ ዶር አንባቸውን ጨምሮ ም/ እያሉ መለሰን ነው ምን ሲቸግር ላልጠፋ ቃላት። እኔ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚልን ቦታ እንደ ፕ/ ሙላቱ ተሾመ ነው የማዬው ወይንም እንደ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ። የሚመራው በቀጥታ በዶር ለማ መገርሳ መንፈስ ነው። 

ሌላው የኦሮሞ አኒፓዬርን መሰረት ለማስያዝ ሲባል በተሻለ ብቃት አዲስ አባባን ልተመራ የምትችለውን ሴት ምንም ለማይፈዬድበት ከበከተ ድርጅት ውስጥ ከተህ ሴት ሾምኩኝ አይዋጥልኝም። ሴት ከመንገድ ሥራ ይልቅ ሌላ ክህሎት አላት። ባለቤት አልባ ከ100 ሺሕ በላይ ለሆኑ አዲስ አባባ ታዳጊዎች ትልቅ ፋይዳ ነባራት።

 ልስማማ እምችለው በወ/ሮ አዳነች አበቤ ሹመት ብቻ ነው። እሳቸው በብአዴን /አዴፓ ጉባኤ ላይም ተገኝተው ማንፌሰቶ ሊሆን የሚችል ቁም ነገር ልብ ላላቸው ተናግረዋለው። የራሳችሁን የቤት ሥራ ሥሩ ብለዋል። በቀደመው ጊዜም ጥረታቸውን እከታተል ስለነበር ጥሩ ነው ሹመቱ። ይወጡታልም ብዬ አስባለሁኝ። ነጻነቱም አላቸው በላይም በታችም ሥነ - ልቦና አቅማቸውን ገንቢ ትልቅ ሃይል አላቸው ጀዋርውያንን አክሎ። 

ምደባው ባጠቃላይ ነገም ይናዳል ብዬ ነው የማስበው። ፊርማው ሳይደርቅ ይፍረከረካል፤ አሁን እራሱ በሃሳብ ደረጃ ተንዷል። በዬጊዜው በአዳዲስ ካቢኔ ሥም ሲለጠፍ እና ሲነሳ፤ ሲፍርስ እና ሲሰራ አብሶ ከዛ ትንታግ የአብይ መንፈስ እኔ አልጠብቅም ነበር ለነገሩ አብዩ እኮ ምስሉ ብቻ ነው ያለው። 

የሚገርመው ቢሮውን ጠንቅቀው ሳያውቁት ደግሞ፤ ገና ሳይለምዱት ሃላፊነቱን እንደተቀበሉ ይነሳሉ። ከዛ በላይ በጀት ለመቆጠብ ተብሎ የታጨቀ ነው። አዬር የሌለው እምቅ ነው ራሱ መጠሪያው። ጭንቅንቅ ጭቁንቁን ያለ እፍን ያለ ጉድ ነው። 

እኔ ሥርጉተ ስተረጉመው ነገረ ኦሮምያ ሥልጣንን የማማከል ተልዕኮ ነው ያለው። ጥናቱን ያደረጉት እነማን እንደሆኑም አናውቀውም። በማናውቀው ውስጥ ነው አቅም እያፈሰስን ያለነው።

እርግጥ ነው እኔ ብቻዬን በአብይ ላይ መፍንቅል ተደርጓል ብዬ ስለማስብ ጦሱ የእሱ እንዳልሆነ አስባለሁኝ። እንዲተችም መንፈሱ ይፈለጋል። እንዲቃለልም ይፈለጋል። አመጽ እንዲካሄድበትም ይፈለጋል። 

ግርም የሚለኝ ደግሞ- ሰው ስለምርጫ ያወጋል እኔ አገር አለን ብለው የሄዱ ወገኖች እንዳይታፈኑ ነው እምሰጋው፤ እሚያስስበኝ ያ ነው፤ እንጂ አሁን አርሲኛ እና አድዋኛ አረብኛ ስለመሆኑ ዛሬ ሰው ባይገባውም ነገ ይገባዋል። የ ብጹዕን አባቶቼ ነገር እጅግ አድርጎ ያሳስበኛል። የበዬሁለት ሳምንቱ ደህንነታቸውን እርግጥ ነው እሰማለሁኝ ግን ለበለሃሳብ እንደተሰጡ ያህል ይሰማኛል። የጃዋርውያንም መንፈስ ክፉ እና ጨካኝ ነው።  

እጬጌው አማራ መሰረዙን ቁጭ ብሎ አይቷል። አፋር መከላከያ ሚ/ር ሲሆን፤ አገር ምድሩ በሰላም ስም ደቡብ ሲኮፈስ፤  ይህ ከሥር ያለው ለብአዴን ተሰጠ የሚባለው ደህንነት ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚባለው አንዱን ሳጅን አዲሱ ለገሰ ልባቸውን የገጠሙላቸው ነው የሚመሩት ሌላውም ከዛ አይወጣም፤ ከአማራ ክልል መንፈሰ አለ የሚባለው ቧልት ነው፤ ጭቆናውን ለመግለጽ ውሃ ያዘለ ተራራ ልበለው መሰል። እልህን አመንጭቶ ቆርጦ በሰላም ይታገል ዘንድ አቅም ያፈልቃል። ትናት በወያነተ ሃርነት ሳሬ ደግሞ በጃዋርዋያን ... 

ለውጥ የሚመስሉ ነገሮች ቀስ በቀስ እንደ ሻማ ብርሃን እዬከሰሙ መሄዳቸው እዬታዬ ነው። አሁን ጭልጭል የምትለውም ከሆነም አትሰነብትም። ችግሩ አሁንም ተስፋ ተቀምቶ ለባለማስኩ ለውጥ አቅም መፍሰሱ ነው። አብይን እንደግፍ ሲባል አብይ በህይወቱ እስከ ቤተሰቡ ከዚህ ረግረግ የሚወጣበትን ስልት እና ጥበብ ፈቃደ እግዚአብሄር እንዲከውን መማጸን ዋናው ነገር ነው።

አማራ ክልል የታቀደው አቶ ደመቀ መኮነን እና ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ለመንቀል ነበር የብአዴን ጉባኤው አሻም ብሎ ስለ አፈረሰው የጃዋርውያኑን መንፈስ አሁን ብወዛ ላይ ናቸው።

ጥርት ባለ መለኩ ለውጥ የምንለው የደከምንለት የታተርለንት የጠበቅነው ተስፋ ተቀምቷል። ለውጥ የነበረው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 እስከ ሐምሌ 19.2010 ድርስ ባሉት ቀናት ብቻ ነው። ለውጡ ከሽፏል፤ ተስፋውም ተነጥቋል። ሁልጊዜም የሞኞቹ ማህበር መቀማታችን የምናውቀው ከተሸንፍን በኋዋላ ነው።

ወያኔ ሃርነት ግልጥልጥ ብሎ የታወቀው እኮ 600 ንጹሃናን ሬቻ ባዕል ላይ ሲጨርስ ነበር። እሰከዛች ማዕልት ድረስ ወያኔ ቅዱስ ነው ይሉ ነበር አብሶ  ኦሮሞዎች። ልማታዊ መንግስት ነው። 

ሌሎችም ሆኖ መወስን በማይችሉበት የበይ ተመልካች ሆነው የነሩበትን መራራ ዘመን ጃንጥላ ተሸካሚ ሆኖ 79 ብሄር ብሄረሰብ በቃ የብሄረሰቦች መብት ተከበረ፤ ህዝብ ራሱን ማስተዳደር ቻለ ተብሎ አብሮ ድለቃ ነበር።

በደርግ ጊዜም ፌደራሊዝም ነበር ያውም ተፈጥሯዊና ጆግራፊያዊ፤ በደርግ ጊዜም ነበር የብሄረሰቦች ኢንስቲቲዩት። እንዲያውም በኢሠፓ ከጫፍ እስከጫፍ እኩል ነበር ተዋፆኦ። አሁን እኮ አፋር፤ ቤንሻንጉል፤ ሱማሌ፤ ሀረሬ እኮ 27 ዓመት ተሰርዘው ነው የኖሩት። ዘንቢል ያዥ ሆነው ነው የኖሩት። 

ጃንጥላ ተሻካሚ ሆነው ነው የኖሩት። የተፈቀደው ለማዬት ብቻ ነበር፤ ታያለህ የማትበለው ህብስት። የማትጠጋው ተስፋ። እነዚህ ክልሎች 27 ዓመት ሙሉ ከፖለቲካ ተሰርዘው ነው የኖሩት። የአማራ ግልት በስልት ነው። ይህንንን ርትህ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የአፋርን የጠ/ ሚር ጉዞ አስመልከቶ ከምዕራፍ አንድ አስከ ሰባት ባለው ውስጥ ብቻም ሳይሆን አብይ ሆይ አቤቱታ ላይ ጽፌዋለሁኝ።

አሁን ያለው ሁኔታ መፍንቅለ መንፈስ በተካሄደበት መንፈስ ውስጥ አብሮ ታድሞ ለመፍንቅል አድራጊዎች ሴራ እና ሸር ሽፋን መስጠት ነው። 

አማራ አንጋሎ የሚያርደውን አቶ ንጉሡ ጥላሁንን እኮ መርጧል የአማራ ጉባኤ። ይህን ማድረግ ከቻለ የአማራ ጉባኤ ስለምን ሳጅን በረከት ስምዖንን አባረረ? በአዲስ ስልት፤ በአዲስ ዘዴ፤ በአዲስ አቅም ተቀብሮ ለመቀረት? ለነገሩ አሁን እራሱ አትረዱትም አዴፓዎች። ሥሙን እራሱ ኦሮምያ የሰጣችሁን መቀበል አልነበረባችሁም። ይህንም ጽፌው ነበር። ነገ ፈጥራናችዋል መምጣቱን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባ ነበር። ለ አማራ የመታገያ ሥም አማራ አንሰን? ተርፎም ይናኛል። የሆነ ሆኗል አዴፓ በጥንቃቄ መራመድ ይኖርበታል።

ለእኔ ያ አራት ዓይናማው አንበሳ አሜኑ አብዩ የለም። በህልሜም ያየሁት ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው። በሌላው ህልሜ ግን ልጽናና፤ እህቴ እንደፈታችልኝ ከሆነ ስትፈጠር አንድ ጡት ያላት ሴት እንዳዬሁን ነግሬያችሁ ነበር፤ እሷ እንደምትለኝ ከሆነ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች ነው። እኔም እንደ አፍሽ ያድርግልን ብያለሁኝ።

ዶር አብይ አህመድ እኮ መንፈሳቸው ገናና፤ ተወዳጅ፤ ሳቢ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ እኮ ናቸው። ሥርዓት በተፈጠረበት ዘመን ቢሆን ኖሮ እኮ ዘመኑን ሁሉ በመላ ዓለም ተከብሮ ተወዶ በመንፈስ ጽላት ሆኖ ይኖር ነበር ልቅናቸው። 

ግን ምን ይሆናል አቶ ጃዋርን አህመድን የመሰለ ክፉ ጠላት፤ የመለስ ዜናዊ አምልኮት መንፈሳቸውን የገዛው ሰዎች ባሉበት ሆነና ሁሉንም አከሱት። ተስፋም ቆዘመ። የሚገርመው አፈናቃዮቹ ራሳቸው ተመራጭ ሆነው አብረው ጉብ ማለታቸው ነው። የሚሊተሪው አመጥ ደግሞ የፈንቃይ ፈንቃይ ነበር ተሳክቶለት  በሆን ኖሮ ደግሞ ሌላ አቅጣጫ አህዱ እንል ነበር። ቢሳካ የንጉሱ ጃዋርም ህልምም አብሮ ያከትም ነበር።

·       ደንጋጣነት።

ሌላው ቀድሞውን ቢሆን በኢህአዴግ ሥር ለውጡ መመራቱ መዘንጋቱ ነው አሁን እዬሆነ ያለው ሲታይ ድንጋጤ የበረከተው። እርግጥ ነው የ100 ቀናቱ እርምጃዎች ቀንጣ ያሉ ፍላጎቶችን እንዲኖሩን አድርጎናል እኔ እራሴ አቤቱታ ጽፌያለሁኝ። የሆነ ሆኖ ጥገናዊ ለውጡ የህዝብን ጥያቄ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ክብር በማይነካ መልኩ የተወሰነ እርምጃ ለመራመድ የተሄደበት መንገድ ሥር ነቀል የሚያስብሉ ወሳኝ ጉዳዮችን አስተውለናል።

አብሶ የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር መለቀቅ እና ከጠ/ ሚር ጋር የነበራቸው ቆይታ ጠቅላላ የለውጡን መንፈስ ወደ ሥር ነቀል መንፈስ አዘል አሸጋግሮታል ማለት ይችላል። ይህ ያሰጋቸው ሃይሎች ደግሞ ራሳቸውን ከቀደሙት ሴረኞች ጋር ሆነው ጊዜያዊ የመንፈስ ቢሮ በቅጽበቱ ከፈቱ።

ጃዋርውያንን እና የአድዋ መሳፍንታትን ያነቃነቀው ጉዳይ ይህ ነው። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ቀድሞውንም ቢሆን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ምርጫቸው አይደሉም። በላይ እንደ ዘነበ ሙላት ነው አብረው የተቀላቀሉት። በሌላ በኩል ያልተገባቸውን የተንጠራራ አቅም በመስጠት እሳቸውንም አቶ ጃዋር መሃመድ እንዲያብጡ አድርጓቸዋል። ወደፊት መምጣት ይገባቸዋል ከአቶ ለማ ጋር ያለው እሳቸው እና አቶ አዲሱ አረጋ ነው። አሁን የምናዬው ይህንኑ ነው እንግዲህ አቶ አረከበ እንቁባዕይም ተመራጭ ይመስላሉ ለዚህ ቡድን።

አሁን ፍዳቸውን እዬከፈሉ ያሉት ዶር ለማ መገርሳ ይመስሉኛል። ጠ/ሚር አብይ አህመድን የማይደገፍው የኦሮሞ ሊሂቃን አቶ ለማ መገርሳ እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ፤ አቶ ለማ መገርሳ ደግሞ እሳቸው ሪኮምንዴሽን ለሰጡበት ታማኝነት ህዝብ ያለው አክብሮት እና ፍቅር ያውቁታል። መንታ መንገድ እንዲዋልሉ አደርገዋቸዋል ብዬም አስባለሁኝ። አሁን ከጎልጉል መረጃ ስንነሳ ይህ ምን ማለት ነው? ወደዬት ነው አስብሎኛል። OMN ወደ OBN መቀዬሩን አይተናል።

የለማ መገርሣኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
ሰው በአገሩ ሁሉም እኩል ተሳታፊ እንዲሆን አለመደረጉ ነበር ለረጅም ጊዜ የታግልንበት አቋም፤ ቢሆንም ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን እዬሰበሰበ ኦዴፓ የኢትዮጵያ አውራ ፓርቲ፤ ብሄራዊ አገራዊ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ያለው ተስፋ ያው ሻሸመኔ፤ ቡራዩ፤ አዲስ አባባ እንዳሳዬን ይችል ይሆናል በጠመንጃ ለመግዛት። በበቀል ህዝብን እያቆሰለ። ነገር ግን በዛ በገፍ በተሰጠው ፍቅር ልክ ግን መከራን ለማሻገር? 

ክብሩን ይዞ መቀጠል ግን የሚችል አይመስለኝም። የመንፈስ ሃብቱ ተንዷል። ወርቅ ሰዎች እኮ አሉ ውጭ ለምሳሌ የቦርድ አባል እንደሆኑ ሰምቻለሁኝ ግን ሰብሳቢ መሆን የሚገባቸው ሰው ነበሩ ጋዜጠኛ ደረጀ ገረፉ እኔ እንዲያውም ይህ ዴሞክራሲ ምንትሶ የሚባለው ሚ/ር መ/ቤት ውስጥ ቢገቡ ሁሉ ምርጫዬ ነበር በፌድራል ደረጃ። መንፈሳቸው ጤነኛ የሆነ ስለሆነ።

በሌላ በኩል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ቢሆንም አማራን በሚመለከት፤ ጠ/ሚር ከሆኑ በኋዋላ ባዬኋዋቸው ጉዳዮች ሞግቻቸዋለሁኝ። የቀደመውን በአማራ ላይ የነበራቸውን ቀናዊ አቋማቸውን ባለማዬቴም በተደጋጋሚም ጽፌያለሁኝ።

ይህ ማለት እንደ ዜጋ ግን ሰው ሰው ነውና ሁሉንም ማሟላት፤ ሁሉንም መጠበቅ ስለማያስፈልግ፤ እቀምን በአግባቡ መያዝ ይገባ ስለነበር በሙሉ አቅሜ ደግፌያቸዋለሁኝ። አማራ ግን በተጋድሎው ልክ አቅሙን አጎልብቶ አባቶቹ ባበጇት አገሩ የእኩል ተጠቃሚነት መብቱን ማስከበር ግድ ይለዋል። 

እኔ እንዲያውም ዓለም ዓቀፍ ንቅናቄ ማድረግ ሁሉ አማራ ያለበት ይመስለኛል፤ እንደ ፍልስጤም ህዝብ አገር አልባ እንዲሆን ተዶልቶበታል እና። ከበፊቱ በባሰ በከፋ ሁኔታ የሚገኘው አማራ ነው። አማራ የተዘዘለትን የሚያውቀው አንድዬ ብቻ ነው። 
  • ·       አንቤ ከሰማኝ!

በአሁኑ ሹመት ዶር አንባቸው መኮነን ገበርዲን እና ከረባት በመግዛት ድንጋይ ጠባቂ እሆናለሁ ብሎ የፕሪዚዳንት ቦታውን ከተቀበለ መይሳው ካሳ ደግሞ እንደሞተ እቆጥረዋለሁኝ።

አቶ ጀዋር መሃመድ እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን በጥርሱ የያዙት ዶር አንባቸው መኮነን ጥቃቱን መመለስ የሚችለው የሚሰጠውን ሹመት አልቀበልም ብሎ ግልጽ አቋሙን ሲወስድ ብቻ ይሆናል።  በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሪኮመንዴሽን፤ በአቶ ጃዋር መህመድ ምህዳን የሚሰጠውን ሹመት ከተቀበለ ዶር አንባቸው መኮነን አማራን 10 ጊዜ ይገድለዋል።

አማራ ለእንሱ ዘበኝነት፤ ለእነሱ ግርባነት፤ ለእንሱ ህንጻ ጠባቂነት አልተፈጠረም። ካልጎሼ አይጠራም። ትምክህተኛነት፤ ነፍጠኝነት መባልን አይፈርበት አዎን እኔ ነፍጠኛ ነኝ! ይበለው፤ አዎን እኔ ትምክህተኛ ነኝ! ይበለው። ለማንም ለምንም የማላደገድግ፤ የማልንበረከከ እኔ አማራ ነኝ! ይበለው - ይነገረው። ዶር አንባቸው መኮነን ሆኑ ዶር አብይ አህመድ እኮ እኩል ሚ/ር የነበሩ ናቸው።

ከአንግዲህ ይበቃል። ቅንነትን ላልፈለገ መራረነትን መጋት ያስፈልጋል። አማራ ጥቃት ተሸክሞ ከሚኖር ቢሞት ይሻለዋል። እንዲያውም ሹመት ተብዬውን የተቀበሉ አማራዎች ሁሉ ሹመቱን ቢያስረክቡ ምርጫዬ ነው። ምን ሲያደርግላቸው?

 እቃ ለቅላቂ ነው ያደረጓቸው እኮ። ልክ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣኑን ካጠበቀ በኋዋላ ኦነግን እንደገፋው፤ ብአዴንም ኦህዴድን ብቻውን ታግሎ ለመንበር አበቃ፤ ኦህዴድ እስከ ሊሂቃኑ ጎለበቱ ጊዜም ሰጣቸው፤ አሁን በ176 ድምጽ አውራ ሲሆን አማራ አገርህን ለቀህ ውጣ ተባለ።

የዚህ ሁሉ መሰሪ ጉዳይ ፈጻሚ እና አስፈጻሚ የጭቃ እሾሁ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው። አቶ ደመቀ መኮነን መፈንቀል ፈለጉ ሳይችሉ ሲቀሩ እነ ዶር አሚን አማን አስቀጠለው ዶር አንባቸው መኮነን ተንሳፋፊ አደረጉት። ነገ እንግዲህ ግንብ ቁጭ ብሎ ሲጠበቅ ዝንብ እሺ ሲል ውሎ ሲያደር እናያለን … ፕሬዚዳንት ማለት ያ ነው … ህንጻ ጠባቂነት 

የኔዎቹ በአቶ ደመቀ መኮነን ጉዳይ ስቸከችክ የባጀሁት ነገር አሁንስ ግልጽ ሆነላችሁን? ምህንድስናውን ፉርሽ ያደረገው የአማራ ጉባኤ ነበር። የአማራ ጉባኤ አዴፓ  የወሰነውን የኢህአዴግ ጉባኤ ስለሻረው ደግሞ አንባቢው አቶ ነጉሡ ጥላሁን ነበሩ። የልባቸው ስለደረሰ። የአዴፓ ውሳኔ ስለተሻረላቸው። 

 የነገው የፓርላማው አፈ ጉባኤ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ሊሆኑ ይችላሉ የሳቸውን መንፈስ አማራ መሬት ላይ ተረካቢ ካገኙ፤ ፌድራል ላይ ከመጡ አዲስ መርዝ ኢትዮጵያ ትሸከማለች። የፈረደባት። በኢህአዴግ ጉባኤ አዋሳ ላይ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እዬተቆረጡ ነበር ቪዲዮው የሚመጣው። ዶር ለማ መገርሳ ደግሞ ከጠ/ ሚሩ በላይ በጉልህ ሲመጡ ተስተውሏል። ጥሎ ማለፍ ይሏችኋዋል ይሄ ነው።

ግን አማራ ቅን እና የዋህ ስለሆነ ታምራቱን ያይበታል። የትም የሚኖር የአማራ ህዝብ እና ወዳጆቹ አማርኛ ቋኝቋ ታናጋሪዎች ሁሉ ቀጣዩን ጊዜም በተደሞ፤ በአርምሞ፤ በስክነት ነገሮችን ከራሱ ሊሂቃን መሪዎቹ ጎን በመቆም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከታተል ይኖርበታል። አንድ ቀን ሆስዕና ይሆናል።

አማራ መደራጀት የለበትም የሚሉት ሊሂቃኑ ደግሞ ቁጭ አድርጎ ፈጣሪ እያሳያቸው ነው። መቼውንም ቢሆን የአማራ ሊሂቅ ካልጠነከረ በኢትዮጵያ ተሰረዞ የመኖር ዕድምታው የሁሉም ነው።

ሁሉን የሚችል አምላክ ቅኖችን ቀን ስጣቸው! አሜን።

የኔዎቹ ኑሩልኝ። ውዶቼ ፌስ ቡክ ያላችሁ አደራ ሸር እንድታደርጉልኝ። ስለ ቅንነታችሁ ደግሞ ለጥ ብዬ አመሰግናችሁላሁ - መወደድም ይታከላል። ሥርጉትሻ ስትወድ ከልብ ከንጡህ በድንግልና ነው እሺ! ኑሩልኝ።  

መሸቢያ ጊዜ!



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።