ልጥፎች

ከኦክቶበር 10, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአቶ ዳውድ ኢብሳ "የእንትን" ፍልስፍና።

ምስል
ልብ። „አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ፤ በመ ዓትህ አትገስጸኝ።“ መዝሙር ፮ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·        መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=hwus5MSdFiA ሰበር መግለጫ ኦነግ ትጥቅ ፈቶ ለመግባት ነው የተስመማው https://www.youtube.com/watch?v=hwus5MSdFiA&t=3s ጤና ይስጥልኝ  እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ ክብረቶቼ። ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦነግን በሚመለከት ግልጽ አቋሙን አሳውቋል። እጅግም ዘግይቷል። ቢሆንም ግን እኔ በገባኝ እና በጻፍኩት ልክ በሁሉም መስክ በተበራራ መልኩ በመንግሥትም ተገልጧል። ቆፍጠን ኮስተር ያለ መግለጫ ይመስላል መሬት ላይ ድፍረቱ ከኖረው። በዚህ እኔ ደስ ብሎኛል ደስ ያለኝ ግን እኔ የተረዳሁትን ያህል ስለገለጸው ነው። መግለጫውን የሰጡት አቶ ካሳሁን ጎፌ መ/ጉ/ኮ/ጽ/ቤት ም/ዴኤታ ናቸው። እኔ ብዙ ጊዜ በአዎንታዊነት ሥማቸውን አነሳዋለሁኝ። ለዬትኛውም ጥያቄ ግልጽና ጭብጥ ነክ ምላሽ ለመስጠት አቅማቸውን ያዬሁት አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦነግ መሪነት ኤርትራ ላይ እያሉ ፤ ዶር መራራ ጉዲና በኦፌኮ መሪነት፤ አቶ ካሳሁን ጎፌ ኦህዴድን ኦደፓን ወክለው በዶቼቨሌ ዲቤት ሲያደርጉ በተመስጦ ነበር የተከታተልኩት። ያን ጊዜ እጅግ ነው የተደነቅኩት።  ዲቤቱ ለእኔ 70% በአቶ ካሳሁን ጎፌ አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው። ያን ጊዜም አቶ ዳውድ ኢብሳ 30 ሺህ እስረኛን መፈታትን በሚመለከት እምነታቸው ስስ ነበር ሰራን የምትሉትም በቂ አይደለም ብለው ነበር ያቃለሉት፤ ያበጨሉት። ያው ኦፌኮንም „ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አይጠፋጥም“ አቋም ነው የነበረው።   ሌላ ጊዜም በዶር አብይ አህመድ ወ