ልጥፎች

ከማርች 27, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ወጥ ወረርሽኝ የበታችነት ስሜት ባይረስ ...

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ   ወረርሽኝ።   ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 27.03.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? እሽት ያደረገኝ ጹሑፍ ነው። ዛሬ የተሜን ጹሁፍ ከዘሃበሻ ሳዳምጥ ነበር። እና ከሥር አስተያዬነት ሳነብ የተጸፈ አገኘሁኝ ከልቤ ከትክት ብዬ ነው የሳቅኩት ጉዳዬም ይኸው ስለሆነ እንደ እኔ ሳቁ … "ሽንት ቤት   ትሄድና ሰው አለ ትላለህ ? በኦሮሚኛ   ካልመለሰልህ ጥለኸው ትሄዳለህ ፤ እንደገና አሁንም ተመልሰህ በኦሮሚኛ ሰው   አለ ? ትላለህ ሰዉዬውም አይመልስም # በመጨረሻ ላይ እንቢ ብሎ ካልመለሰልህ   ሰውዬው # ሱሪህ ላይ # ትለቀዋለህ 😂😂😂😂😂 like በቀለ ገርባ“  „Tikdem Tikdem 1 hour ago ·        ወረርሽኝ ተህግ ጥሰት አንጻር። ወረርሽኙ ከህግ ጥሰት አንጻር ሲባል ከሃይማኖታዊው፤ ከብሄራዊው፤ ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጋር እንደማለት ነው። ሌላም ይተበሃል አለን፤ የህግ ባለሙያዎች ላይስማሙት ቢችሉም ሁሉጊዜም አዘውትሬም እንደምለው ኢትዮጵያ በተጻፈ ህገ መንግሥት እንደሚተዳደሩት አገሮች የተጻፈ ህገ መንግሥት አላት፤ ባልተጻፈ እንደሚተዳደሩትም ያልተጻፈውንም ይሁነኝ ብላ በህሊናዋ መስጥራ ትኖርበታለች። ምን ማለት ነው ይኼ ሁለቱንም አጣምራ የያዘች አገር ናት ለማለት ነው። እንዲያውም ከተጻፈው ይልቅ ያልተጻፈው የበለጠ ተግባራዊ ይሆናል። ህዝቡ ፈቅዶ ስለሚወሰነው። እንዳሁኑ የ ኦዴፓ አውራነት በ ገዳ ተዳደሩ ተብለን አቅጣጫ የለሽ ወጀብ እንደምንናጠው ግን አይደለም። አሁን ከሆነ የሚታዬው ደግሞ ያልተጻፈውንም የተጻፈውንም ሲጣስ ነው።