ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 28, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለጨለማው ሳጅን በረከት ስምዖን የጋዜጠኛ ፋሲል ልዩ ስጦታ¡ እንዲህ ይሰለቅ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዳ ዋ ። የማጅራት ገጽ። „ከመልካም ሽቱ መልካም ሥም፤ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።“  መጽሐፈ መክብብ ፮ ቁጥር ፩ -፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 28.01.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                                                    የአማራን ብሄርተኝነት ተጋድሎ የወለደው ይህ ቅኔ                                            እንጂ ጨለማው ሳጅን በረከት ስምዖን አይደሉም!     ·        መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=9FVkFDLDj1g ESAT News In Depth The End Of Bereket Simon January 24,2019 ·        እፍታ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? አቶ ወንድም ልጅ ፋሲል የኔአለምስ እንዴት ነህ?    ውዶቼ ዛሬ ልዝ እንጨት የመሰለ ቀን ነበር ዛሬ። ወይ ጨርሶ አል ከ ፋው ወይ ደግሞ ጨርሶ አልቀ ለ ለው። እንዲህ አይነት አየር መንፈስን ሰ ርቅርቅ ስሜትን ስ ርቅርቅ ያደርጋል። ከሰሞናቱ አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም በሳጅን በረከት ዙሪያ አንድ የሀተታ ዝግጅት አቅርቦ ነበር። እኔም ቃል በቃል መጻፍ ስለነበረበኝ ዘገዬሁኝ። እስሩን ምክንያት በማድረግ ሀተታ እንዲቀርብ የገፋፋውን ዋቢ ምክንያት ፈረጥረጥ አድርገን እንመለከተው ዘንድ እንዲህ ወደድኩኝ። ቅርፊቱን የሀተታ ክፍል ሆነ መናጆውን በሚመለከት ከግፍ ጋር አጣጥሞ የቃኘው እሱ ለሐተታው መቋጫ ጉልበት እንዲያገኝለት ብሎ ማቀረቡን ብረዳም አቀራረቡ ግን ወድጄለታለሁኝ። መሰረ