ለጨለማው ሳጅን በረከት ስምዖን የጋዜጠኛ ፋሲል ልዩ ስጦታ¡ እንዲህ ይሰለቅ!
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ዳዋ።
የማጅራት ገጽ።
„ከመልካም ሽቱ መልካም ሥም፤
ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።“
መጽሐፈ መክብብ ፮ ቁጥር ፩ -፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28.01.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
የአማራን ብሄርተኝነት ተጋድሎ የወለደው ይህ ቅኔ
እንጂ ጨለማው ሳጅን በረከት ስምዖን አይደሉም!
· መነሻ።
ESAT News In Depth The End Of Bereket Simon January 24,2019
· እፍታ።
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? አቶ ወንድም ልጅ ፋሲል የኔአለምስ እንዴት ነህ?
ውዶቼ ዛሬ ልዝ እንጨት የመሰለ ቀን ነበር ዛሬ። ወይ ጨርሶ አልከፋው ወይ ደግሞ ጨርሶ አልቀለለው። እንዲህ አይነት አየር መንፈስን ሰርቅርቅ ስሜትን ስርቅርቅ ያደርጋል።
ከሰሞናቱ አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም በሳጅን በረከት ዙሪያ አንድ የሀተታ ዝግጅት አቅርቦ ነበር። እኔም ቃል በቃል መጻፍ ስለነበረበኝ ዘገዬሁኝ። እስሩን ምክንያት በማድረግ ሀተታ እንዲቀርብ የገፋፋውን ዋቢ ምክንያት ፈረጥረጥ አድርገን እንመለከተው ዘንድ እንዲህ ወደድኩኝ።
ቅርፊቱን የሀተታ ክፍል ሆነ መናጆውን በሚመለከት ከግፍ ጋር አጣጥሞ የቃኘው እሱ ለሐተታው መቋጫ ጉልበት እንዲያገኝለት ብሎ ማቀረቡን ብረዳም አቀራረቡ ግን ወድጄለታለሁኝ። መሰረታዊ ምክንያቱ ግን መንፈስን ክፉኛ እዬናጠ ያለው የአማራ ብሄርተኝነት ጉዳይን ቅስም ለመሰበር ታስቦ፤ ታልሞ፤ በተደራጀ እና በተቀነባበረ ሁኔታ ነው እንደተለመደው በዘመቻ እዬተሠራበት ያለው። ተው የሚል ባለግራጫም የለበትም።
ይህ የተለመደ ነው አቅም ብቅ ሲል በደቦ ማሳደድ። በመኢህአድ፤ በአንድነት፤ በሸንጎ፤ በአማራ ታገድሎ፤ በዛሬው ኦህዴድ በአሁኑ አዴፓ አሁን ደግሞ ተረኛው አብን ደርሶታል። ዘመን ፊደል የማያስቆጥረው ቀናተኛ መንፈስ። ይግርማል እስከ ወዲያኛው።
አቅም ገንብቶ በልጦ፤ ተግቶ አሸንፎ መውጣት ሳይሆን አቅም አለው የተባለውን ከተቻለ መጠቅለል፤ ከጠቀለሉም በሆዋላ ታሪክን ማክሰም ልክ እንደ ኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር፤ ካልተቻለ ደግሞ በደቦ ቅስም ለመስበር ሠራዊት ማሰለፍ የተለመደ ነው የተኖረበት።
እነሱም አይደክማቸውም እኛም አይደክምንም ባቀረቡት ልክ መሞገት ይገባል።
የጀግኖች ቀንዲል!
የአማራ ብሄርተኝነትን በዚህ መልክ እንዲቀርብ የሆነበት ምክንያት መላ የኢትዮጵያ ህዝብ በሳጅን በረከት መታሰር ደስታውን ሲገልጽ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የአማራ መደራጀትን ከዚህ ጋር በማነካካት ቁጫኑን፤ ቁጭቱን ለመወጣት የተጠቀመበት መንገዱ ነው የልጅ ፋሲሉ አዲስ የምህንድስና ቃ የለው መንገዱ። ሲያሳዝን? ለነገሩ አለቀ ምን በልቶ ይደር ማይኩ?
ህልም እንደ ፈቺው እንደሚተረጎም የታወቀ ቢሆንም በእሱ የርጋታ አቅም ጋር ሊመጥን ያልቻለ አቅዶ እና ተልሞ የተነሳበት ዓላማ ውስጥ የአማራውን መደራጀት ተፃሮ እንደ የሰማይ መርገምት አድርጎ ያው እንደ ቤተኞቹ ያቀረበበት ሁኔታ ድንቅ እያለኝ ወደ ሦስት ጊዜ አዳምጨዋለሁኝ።
የዚህ አዲስ ትውልድ ቤተኛ ሆኖ በዚህ መሰል መሰሪ መንገድ ለመሄድ ማሰቡ ዕድሜውን የተላለፈ፤ ዕድሉንም የተላለፈ ይመስላል ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም። ማጣበቂያ ፈለገ ቁርሾውን ለማውጣት። ይህ የሚበጀው ለማሌ አራማጆች ነበር። ያው የበቀለ ነገር ማዬት ሃራማቸው ስለሆነ። ወይ አያድጉ ወይ አይከስሙ ዘመን ተዘመን ህውከት ብቻ። የትውልድ ብክነት ናፍቆተኞች።
እሱ በመሰለው ተደራጅቷል ሌላውም በመሰለው የመደራጀት መብት ነው። ሌላው ግን ሳጅን በረከት የአማራ ብሄርተኝነት መስራች አይደሉም። ምኔ ብለው? አማራ እኮ አይደሉም። አማራን ለማፍረስ የተበጁ የሄሮድስ መለስ እጀታ ናቸው። ምንም የእሱ ድርጀት እንኳን መፍረሱ እንደ መልካም ዜና እዬተደመጠ ቢሆንም አሁንም ቅርጥምታሚ ቢገኝ ብሎ ነው የሚነሳ የሚወድቀው። የሆነ ሆኖ ሳጅን በረከት ስምዖን የአማራ ብሄርተኝነት አማጭ አድርጎ ማቅረቡ ይህ ቁልጭ ያለ የፍልስፍና ድህነት ነው።
ምን አልባት ሌላው አድማጭ አሁን ባለው ሙቀት ተነሳስቶ ላያስተውለውም ወይንም ምንም ሳይመስለው፤ እንዲሁ ሊያልፈው የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላል። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ግን አላልፈውም። የፍልስፍና ፍልሰትም ፍድሰትም ስላለበት። ያታሪክም ብክነት ስለሆነ።
የጎንደር የአማራ የማንነት ታጋድሎ „የነፃነት ሃይሉ ተብሎ“ ለአንድ ሰሞናት የፕሮፓጋንዳ ዛቢያ መሆኑ አከተመና ዛሬ ደግሞ ይህን ጠራጣሮ ሃሳብ ይዞ ብቅ ብሏል።
ከሁሉ በፊት ግን … „በኢትዮጵያ የብሄር ብሄራሰቦች መብት እስከመገንጠል“ የማን ፍልስፍና መሆኑን ለማወቅ መጣር ትንሽ ዝበትን ያስተካክል ነበር፤ በስሜት ዘመን ይዞ እስተዘመን ጠላት እዬፈጠሩ የግጭት አውራ ከመሆን።
በማሌ ፍልስፋናው በኢትዮጵያ ጨቋኙ ብሄረስብ ማን እንደሆነ የታወቀ ነው ቅኑ የአማራ ማህበረሰብ ነው። አማራ ደግሞ አይደለም የእነሳጅን በረከት አምልኮተ የህውሃት ማንፌስቶ አማራ ጨቆነ እዬተባለ፤ ከዚህም ባለፈ አማራ በዬለም ቁልጭ ያለ ዲስክርምኔሽን የተፈጸመበት ማህበረሰብ መሆኑን ከእኛም አልፎ ሉላዊው አለም ከቀዩ ድረስ ሄደው ውስጡን እንዲያዳምጡት ተገደውበታል። ያ የብርሐን ቀን ከመሬት የታፈስ አይደለም። ሊቀ ትጉሃኑ የአማራ ልጆች የተጉበት ሰብል ነው።
ውዴቼ አንድ የቤት ሥራ ልስታችሁ በማጅራት ዓይን አፍንጫ ጥርስ እና ከናፍርን እሰቡት። ማጅራትን እንደ ፊት ገጽ ሲሆን ማለት ነው። የጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ፍልስፍናም ይኸው ነው። ማጅራት ላይ ዓይን ሲሰካ፤ አፋንጫ ሲለጠፍ፤ ጥርስን ካነፍር ሲተከል? አቶ በረከት ስምዖን "ለአማራ ብሄርተኝነት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ" ይለናል። ምን ዓይነት ጠቀራ ሆነ ፍልስፍና ነው።
ውስጡን እኮ ነው ገፋ እያደረገ ወደ ሌላ የሚያጠጋጋው „ አሉ፤ ይላሉ፤ ተባለ እያለ“ የሚያስነብበን። ከሱ በቀደመ ሁኔታ እኛም ይህን ዘዴ እንጠቀምበት ነበር። በዚኸው የሙያ ዘርፍ „ሲሉ ይደመጣሉ“ እያልን ጉዳዩን ለሌላ ባለቤት ገፋ እያደርግን ሠርተንበታል።
· ልብ አለን።
በቅድሚያ …. ዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ የነበረውን ውስጠት፤ ወካባ በሚመለከት ምን ያህሉ እጄ ደገፈ ቢባል የሚል ቢኖር ከቁጥር በታች ነው ብዕር የጨበጠ፤ ማይክ ያገኜ፤ ሚዲያ ያለው ሁሉ በስውርም በግልጽም በዘመቻም ነው የተቃወመው። ህሊና ለነፃነት ያደረ ስላልነበር፤ ክህሎቱም ወና ስለሆነ።
የውጮቹን ሳይቀር ነው ያሳሰቱት። በተሾሙ ዕለት በቅጽበት ክብርት አና ጎምዝ ወጥተው በአደባባይ „ቃል ብቻውን አይበቃም“ ነበር ያሉት። በ አንድ ቀን ልጅ ተጽንሶ ቆሞ፤ ዩንቨርስቲ ግብቶ ተመርቆ ለማዬት። "ይቻላል" ምን አህል አለምን እንዳስደመመ በዘመነ ኦባማ እአወቁ። የሆነ ሆኖ ያ የማን ዶክተሪን እንደሆን ጡጦ የሚጠባ የለም። በወቅቱም ሞግቼበታለሁኝ።
በሚዲያ ልብ ሞልቶ መናገር የሚችለው ሳተናው በትጋት በአዎንታዊነት ብቻ ሳይሆን በሙሉ አቅሙ በብርታት እና በጥንካሬ ሲተጋ ተመልክቻለሁኝ። ከመነሻው ከውስጡ ነበር የደገፈው። ወጀብ ሲበዛባቸው ዶር አብይ አህመድ እራሱ እንዴት ይከፋው እንደነበር እምሰክርለታለሁኝ። እነ ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ፤ እነ ጋዜጠኛ አንተነህ ከበደ በሚችሉት ሁሉ መስክረውላቸዋል። ሌላውማ አማኑኤል አሰኝቶት ነበር። መቼስ አይካድ ነገር።
ከዚያ ባሻገር ዶር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመምጣት ገዱዩ ለሁሉም የመርዶ ያህል ዱብ ዕዳ ነበር። ሁሉም አቅሙ በቻለው ልክ ተፋልሞታል የራሱም ሚዲያ ኢሳትም ድርጅቱም ግንቦት 7ም። ህወሃትን ከመታገል ለኦህዴድ ለእነሱ ጫን ተደል የቤት ሥራ በመፈጠር ማዋከቡን ሁላችሁም ነበራችሁበት - ቅኖቹ። በኋላ ደግሞ የድል አጥቢያ አርበኝነቱን ስንቱ ሰው ታዝቦታል። በወረፋ ለመገናኘት፤ ለመጨባበጥ፤ አብሮ ፎቶ ለማስለጠፍ፤ ሚዲያ ላይ ለመታዬት ወዘተ …
ያን ጊዜ ግን ሁሉም አቅሙ በቻለው ልክ ታግሎታል። ቅኖች እጅግ ጥቂቶች ልበ ብርሃኖች ብቻ ከጎናቸው ቆመው ተፋልመዋል። ስለሆነም የዶር አብይ አህመድን ወደ ፊት መምጣት መቃወም የሳጅን በረከተስ ስምዖን ብቻ ችግር አልነበረም። ጊዜውም ገና ልጅ ስለሆነ ማንም ሊረሳው አይችልም ያምናውን የመከራ ጊዜ። የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነውና።
ጠ/ሚር ሆነው ሲመጡም ሰባራ ሰንጣራ በመለቃቀም ገና በጥዋቱ ምን ያህል መንቀዥቀዥ እንደነበር የነበረው ፍዳ ልብ ያላቸው፤ ማስተዋሉን አብዝቶ የሰጣቸው ቅኖች ያውቁታል።
ይልቅ ቁምነገር ሊሆን የሚገባው አቅም ለመስበር የሚደረገው ትግል አብሮ መሰበርን የሚያውጅ ስለመሆኑ ትምህርት ሊወሰደበት ይገባል። አሁንም በአንድም በሌላም ራሱ ተጠቃሚው በተቀናቃኝነት ቆሞ መንፈስ ሲበትን ስለሚገኝ። ጦስ ያለበትን ቦታ እዬፈለጉ ከማጋጋል መታገስን ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች መትጋት ይገባ ነበር። መተቸት የለበትም ማለቴ ግን አይደለም። አመት ሊሞላው ስለሆነ ...
ብቻ ሁሉንም ልኩን ያሰወቀው ቅኔነት ረጅሙን የመከራ ዘመን ያሳጠረ እርምጃ ነበር ዶር ለማ መገርሳ የወሰዱት። ይህን ማንም የማያደረገው ሥር - ነቀል የዶሞክራሲ አባትነት ተግባር ሲፈጽሙ ዛሬን አልመው ነበር ብልሁ መሪ ዶር ለማ መገርሳ።
ኦህዴድ ልክ አንዴሌላው የተፎካካሪ ድርጅት ወረፋ ደርሶት „ከመለሰውያን ወደ ለማውያን“ በሚል ሰብሮ ለጣል፤ ህዝብ እንዲያድመበት ያልሆነ ያልተደረገ ነበር አልነበረም። ልክ አሁን አማራ ብሄርተኝነትን መሥራቹ ሳጅን በረከት እድርጎ በመሳል አማራን ለማስገለል እንደተሳናደው ፕሮፖጋንዳ ማለት ነው። ሁሉንም ወጀብ አሳልፎ እግዜሩም በቅኞች እና በአቅመ ኮሳሶች ላይ በመንፈስ ደጋፊነት ጎን ሆኖ በጅ አልልም ብሎ ዛሬን በምርቃት አሽሞንሙኖ ሸለመን እንጂ።
· ጥሻ!
ሌላው ልጅ ፋሲል እንደሚነግረን ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት የአማራ ብሄርተኝነትን ቀያሽ ሳጅን በረከትን አድርጎ ነው ያቀረበው። ሎቱ ስብሃት! እግዚአብሄር ይቅር ይበልህ! ምንድነው ቅጥህ? እንዲህ ይለናል አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔ ዓለም …. ሙሉውን ነው የጻፍኩት … ጥቂት በፍርጅ በፍርጁ ልሂደበት … ልክ እንደ ባልደረባው የ እማማ አዘጋጅ ጋዘጠኛ አቶ ማስረሻ አለሙ... ይደግምልናል ...
„ህወሃት አለማዋን ለማሳካት ለማስፈጸም ፊት ካዘመተቻቸው ሰዎች መካከል እንደ በረከት ስምዖን ያገለገላት ሌላ ሰው የለም ብሎ መናገር ይቸላል፤ ህወሃት የአማራን ህዝብ ኢትዮጵያዊነት ትርክቱን ትቶ በአማራነት ብሄርተኝነት አመለካከቱን ብቻ ታጥሮ እንዲቀመጥ የዘረጋችውን እቅድ በግንባር ቀደምትነት ያስፈጸሙት አቶ በረከት ዛሬ ለሚታዬው የአማራነት ብሄርተኝት ስሜት ከፍ ብሎ ለመታዬት የ አንበሳውን ድርሻ እንደተጫወቱ „ይነገራል።“ ለምን እናገራለሁ አትልም። ያለ ካለ ደግሞ እከሌ አለ በለን። ዓይንና ጆሮነት እኮ የሌለውን ገማና ማብጠልጠል ብቻ ሳይሆን የራስህንም ገልጠህ በማሳዬት ነው።
ህወሃት እኔን አጥፋ ብሎ ለአማራ መደራጀት ፈቀደ? ከዬት ነው የተፈጠርከው የትኛውስ ፕላኔት ላይ ይሆን የኖርከው? ትውልድ የማይተካቸው ፕ/ አስራት ወ/ዬስ ያን ሁሉ መከራ ተቀበለው ስለምን ይሆን ያለፉት? አማራ ነኝ ማለት እራሱ አይደለም ኢትዮጵያ ላይ በእናንተ ግዛት በዘመነ አወራናታችሁ እና አራጊ ፈጣሪነታችሁ ዘመን እዚህ ውጭ አገር ይፈቀድ ነበርን? አሁን ፈጣሪ ደግ ነው፤ የሰሜን አሜሪካ የብአዴን ልዑክ ጉዞ ዳኛው እንጂ
… እናንተም አድናቂ ሆናችሁ "ምን እንርዳችሁ" እስከማለት መድረሳችሁ ከትከት ብለን እየሳቅን ታድመንበታል። ያው ካባ እና ወርቀ ዘቦን ባትሉም ሥራው ነው ብአዴን። ብቻ አድናቆቱ ሲርከፈከፍ ለዛውም „ለማምን ገዱም ገዳይ በተባላበት“ አንደበት። በመሆን ውስጥ ሆኖ መዝለቅ እንዴት ያቅታል? ምን ሊቀር? ምን ሊጨመር? ሃብት ማለት እኮ የህሊና ብቻ ነው። ጭብጫ ጎርፍ ነው ወይንም ጤዛ፤ ወይንም የሳሙና አረፋ … የራስ ህሊና ግን አይሰሹትም። የሌለው አቅም ቢሆንም ምንም አይመስለኝም፤ ብድር የማይሻው ሲሆን ግን ?
የሆነ ሆኖ ሌላው ቀርቶ የቅርቡ 20ሺህ የስምጥ ሸለቆ የአማራ ወጣት የጀምላ እስርስ ስለምን ይሆን? አማራ ነኝ በማለት የመጣ እኮ ነው? የባህርዳሩ የጅምላ የሰማዕትነት እልቂትስ? የአንባ ጊዮርጊስ ሰማዕት ህፃናትስ?
ለመሆኑ የ66 ማርክስሲቶች ፖለቲካኞች አማራ እንዲራጅ ይፈቅዳሉን? ታሪክ አንብብ የታሪክ ሊሂቅ አይደለህምን? እንኳን ትናነት ዛሬ የ እናንተ መሪዎች ትክን የሚሉበት በዚህ አይደለም። ሁሉ በብሄሩ እንዲደራጅ ተፈቅዶ የቋሯው ምክንት አማራ አይደረጃም በሚል ነበር የተከወነው። አማራ ገባሪ እንዲሆን ብቻ ነው የሚፈለገው ለዛው በቀዩ ላይ … ድርጅቱ ተቀምጦ። እያበላ እያጠጣ መጠለያ ሆኖ አብሮ እዬተዋጋ ...
አክተሮቹ ስላሉ ጋዜጠኛ አይደለህ ከዬትኛው ብሄረሰብ እንደወጡ ደግሞ መርምረህ ድረስበት። ሲከፋፈሉም ያው እነሱው ናቸው። አዳዲስ የኢህአፓ ቅርንጫፍ ያደራጁት። አሁን ይህን ሃሳባቸውን ይዘው እዛው መከረኛ ህዝብ ላይ ድምጽ ስጠን ይላሉ … ያ ሁሉ ህዝብ አልቆ - ታስሮ - ተሰዶ በእነሱ ምክንያት። የጎንደር እናት ትምስከረው ያቺ መከረኛ። ያቺ ፍደኛ ሌላውማ ምን ቀርቶበት … ተምሯል እስኪበቃው ድረስ...
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ይቀጥላል እንዲህ ...
„አቶ በረከት አማራው በአማራዊው ብሄርተኝነቱ እንዲደራጅ የተጨዋቱት ሚና የብሄር ፖለቲካ አመለካከትን የሚደግፉ የአማራ ተወላጆች እንደ መልካም ሥራ የሚጠቅሱላቸው ነገር ቢሆንም ይህን መልካም ሁኔታ አማራው በአገሪቱ እኩል እንዲጠቀም ሳይሆን እንዲበደል የአማራ የበላይነቱን እናሰወግዳለን እያሉን የህውሃት የበላይነት አንዲተከል ከፍተኛ ሥራ መሥራታቸውን ብዙዎች በቁጭት ያነሳሉ።“
እነማን? ምናው ፈራህ ደፍረህ ንገረን? ፍርሃትህ ልክ የለውም።
አማራ የተበደለው ዛሬ አይደለም 43 ዓመቱ ነው። ወልቃይት የጠገዴ ሰው ፍራንከፈርት አሉልህ ጋዜጠኛ አይደለህ ሄደህ መጠዬቅ ነው። ምን አለ ግንቦት 7 በራዲዮኑ አቶ በረከት ሰምዖን ሥልጣኔን በፈቃዴ እለቃለሁ ሲሉ „በስልክ የብአዴን ጽቤት ተጨናነቀ በድንጋጤ“ ብሎ አንድ ደመነፍስ ዜና ዘግቦ ነበር። ስልኩ የተጨናነቀው እኮ ጭራቁ መንፈስ ስለምን
ይሄድብናል ብሎ ነው እኮ? መሳቂያ።
አሁንም አንተ የምትነግርን ያንኑ ድንብስ ጉዳይ ነው። ቀድሞ ነገር „በአማራ መቃብር ላይ ታላቋን ትግራይ እመሰርታለሁ“ ብሎ የተነሳን ማንፌሰቶ በፊት ረድፈኝነት ለማስፈጸም በቱቦነት የተሰለፈ መንፈስ ይህን እንዲያጠፋ፤ ይህን እንዲከሰም ነው አማራ እንዲራጅ የሚፈቀደለትን? ምኑን እና ምኑን እንደምታገኘው፤ ምኑን እና ምኑን ቀይጠህ እንደምትዛባራርቀው የሚገርም ነው። ከቶ ለጫዋታ ማሟያ ነው ወይንስ ያምርብኛል ብለህ ይሆን? ብልሃት የሌለው ቅላት ...
አማራ 40 ዓመት እንደሌላው ተደራጅቶ ቢሆን ኑሮ ይህ ቀልድና ቧልት ያከትምለት ነበር። በአንድ ህዝባዊ አመጽ እኮ ነው ሁሉም አመዱ ቡን ያደረገው። የአንተ ድርጅትም ተስፋው የተሸኘው በዚኸው ተጋድሎ ነው። ነጻም ሲወጣም የአማራ ታገድሎ ኮፒ ራይቱን አስጠብቆ ነው። አማራ ጉዳዩን በስማ በለው ሳይሆን በባለቤትነት ራሱን ሆኖ በራሱ ውስጥ ሰክኖ ነው በአቅሙ በጥበቡ በቅኔው ልክ አልሞ ነው።
አሁንም ቀጠለ … ጋዜጠኛው እንዲህ እያለ …
„ከዚህ በተቃራኒ ግን ከብሄር ፖለቲካ አስተሳሰብ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት መደራጀትን የሚያስቀድሙ ሃይሎች አቶ መለስ እና አቶ በረከት የኢትዮጵያን አንድነት በማናገት በማፈራረስ ተወዳዳሪ የሌላቸው ካህዲ አድርገው ይስሏቸዋል። አቶ በረከት አማራው ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ በብሄሩ ዙሪያ እንዲሰባሰብ ማድረጋቸውን በኩራት ሲናገሩ ቢሰማም አማራው በብሄሩ ተደራጅቶ ምን ትርፋ አገኜ ሲባሉ ግን የሚሰጡት አሳምኝ መልስ አልነበራቸውም።“
ለመሆኑ አማራ መሬት ላይ ከመአህድ ቀደም ባለው ጊዜ አሁን ከአብን በስተቀር በአማራ ልጆች አንጡራ መክሊት የትኛው ድርጅት ነው አማራዊ ድርጅት የነበረው? እነሳጅን በረከት ስምኦን፤ እና ሳጅን አዲሱ ለገሰ? እነ ዮሴፍ ህላዊ? ማን? የኢህአፓ አፈንጋጭ አንጃ በህብረ ብሄርነት ነበርኩ የሚለው ወደ አማራነት ተቀዬርኩ ብሎ ሥሙን በስላቅ ያሸቆጠቆጠው። እነሱም አይሉም። በማንነት ቀወስ ውስጥ ተዘፍቆ የኖረ ድርጅት ነው ብአዴን። አሁን ይልቅ ምህረቱን ያውርድለት ዘንድ ሱባኤ ይያዝለት።
አይደለም ትናንት ዛሬም ብአዴን ከራሱ ጋር ፍጥጫ ላይ ነው ያለው?ማዳዳጥ ከ እንግዲህ አይችልምና። ወይ ሆኖ አማራ ይቀጥላል፤ ወይ ደግሞ በቁሙ ይፈርሳል። አማራዊ የመሆን አቅሙም ወርዱም አሁንም የለውም - ተዛነፍ ነው። ካልነበረው ደግሞ አማራዊ ብሄርተኝነትን አምጦ መወለድ አይችልም። አልሰማህም ሰሜን አሜሪካ ላይ ዶር አንባቸው መኮነን ሲናገሩ? እኛንም ለውጡ ነፃ አወጣን ሲሉ? የት ነበርክ?
ቀጠለ እንዲህ እና እንዲያ እንደ በርሃ አሸዋ እንደበቀለ እጽዋት መቆሚያ ፋክት አጥቶ የሚንገዋለላው የአቶ ወንድም የጋዜጠኛ ፋሲል ትርክት …
„በዚህ ትርክት ዙሪያ ያሰባሰቧቸው አባሎቻቸው ሳይቀሩ አማራው በብሄሩ ስለተደራጀ ከመገደል ከመፈናቀል ከመሰደድና ከድህነት እንዳልዳነ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።“ አማራ በብአዴን ልክ በ አማራ ድርጅት አልነበረም። አንተ እራስህ አብሰንት በሆነ አምክንዮ ላይ ነው እዬዳከርክ ያለኽው? መካሪ አጣህ።
አማራ በህብረ ብሄር ፓርቲስ ተደራጅቶ ምን ጥቅም አገኜ? ይህን ልትነግረኝ ትችላለህ? ለገባርነት? ወይንስ ለገቫሪነት? ወይንስ ለአንጋችነትን? ወይንስ ለቀይ ምንጣፍ አንጣፊነት?
አሁን የነፃ ሚዲያ ዘመን ስለሆነ ኤርትራ በርሃ ላይ የነበረውን ትራጄዲ ተውኔትም እዬታደምንበት ነው እኮ። ዝም ስትባሉ አያስችላችሁም። ፍርድ ቤትም ማሰቃያም ልክ እንደ ህውሃት ከዚህም ያላፈ ገመና እዬተዘረገጋፈ ነው … በርሃ ላይ፤ በስደት ምድር፤ ህይወቱን ሊገብር ለተሰናዳ ጓድ አሸዋ ላይ ወድቆ ለሚያድር አጋር? ማተበ ቢስነት ነው ይሄ። ያሰጠጋን፤ ክብር ያሰጠ? ባዶ እጃችሁን እኮ ነው የሄዳችሁት?
ለወዳጅም ለጠላትም ሊነገር የሚገባው ሃቅ ታዝሎ አሽኮኮ ተደርጎ በአማራ አቅም መንበር ላይ ቁምብ ማለት ህልም ሆኖ መቅረቱን ነው። እርግጥ ነው ይህ ይመቸኛል ያለ የመንፈስ ተቀኝ ተጠዋሪ ካለ መብቱ ነው። የነፃነት ዋጋን … ለጣሰ የሚገባውን ቢያገኝ ገዱያችን አይደለም።
ትንሽ ሰለምታወድሳቸው የአማራ ልጆች … ይህ መልስ የሚሆን ይመስለኛል። ያው የጥላሁን ግዛው ኮፒዎች ስለሆኑ …
ፕ/ የምንዳርአለው ዘውዴ ነፃነትን ስለማክበርም እንዲህ ይሉናል የጥምር ዕውቅት ፈላስፋው „ሰው የባርነት ምቾትን ከመረጠ ለውሻ አሟሟት መፈረሙ የተረጋገጠ ነገር ነው። በባርነት ደልቶት የኖረ ኑሮው የአሳማ ነው ሞቱ የውሻ ነው። በነፃነት ተንግላቶ የኖረ ህይወቱ ኑሮው የጀግና ነው። ሞቱ የሰምዕታት ነው።“
„በሌላ አነጋገር የሰው ልጅ እግዚአብሄር የፈጠረለትን ግብ እንዲያስብ ነው። ማሰብህን በሆድህ ተክተክተህ ከዛ በኋላ ከአሳማ የምትለዬው በሁለት እግርህ መሄድህ ብቻ ከሆነ የምርም እንደዚህ አይነት ፍጡር እንዲህ አይነቱ ኑባሬ ሁሉን ነገሩን የሸጠ ነው። ነፃነቱን ጨምሮ።
አንድ ጊዜ ነፃነትን ለአንባገነኖች አሳልፈህ ከሰጠህ በኋላ ጊዜ ልጠቀም ብትል ከሱ ልትበደር ይገባሃል። እንዲህ ማለት ነው ነፃነትን ከአንባገነን እዬተበደሩ ከመኖር የባሰ በዚህ ምድር ላይ ትልቅ የምርም ትራጀዲ የለም። በህይወት ውስጥ ያለው የመጨረሻ ትራጄዲ የራሰን ነፃነት ከአንባገነን እዬተበደረክ መኖር ነው። ለምን ትበደራለህ? መጀመሪያውን አሳልፈህ ባትሰጥ ኖሮ። ለምን አሳልፈህ መጀመሪያ ትሰጠላህ? ነፃነትህን ለሆድህ አሳልፈህ ባትሰጥ ኖሮ። ለምን ለሆድህ ቅድሚያ ትስጣለህ? መጀመሪያውን የአሳማነትን ህይወት እና የውሻን አሟሟት ባትመርጥ ኖሮ።“ ይህን ለሚመርጡ መንገዱን ጨርቅ አድርግላችሁ ነው።
· መጪው።
እርግጥ ነው ነገ ጨለማ ነው። የግርግር ፖለቲካ ግብዕቱ ስለተፈጸም። ከዚህም ሌላ ወደፊት ሁሉም እንደ ሥራው በለፋው ልክ ነው ሥልጣን የሚያገኘው። ቀድሞ ነገር ባልነበረ አደረጃጀት የሚታፈስ ሰብል የለም።
የዚህን ታሪካዊ ቅኔ ነው ጋዜጠኛ ፋሲል ለሳጅን በረከት የሸለመው።
ስለዚህ አማራ ተጠቃሚ እንዲሆን በልጆቹ የሚመራ ድርጅት ያስፈልገው ነበር እድሜ ለሀምሌ 5 /2008 ተስፋን አምጦ ውልዷል። አሁን እያንቀጠቀጣችሁ ያለው ንጥር ነገር የአማራ ወጣት ሊሂቃን በአቅማቸው ልክ ተፎካካሪ ሆነው እኩል ከድርጅታችሁ ጋር መታደመቸው፤ እውቅናቸው ጎልቶ ዳብሮ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን በምዕራቡ ዓለምም ሰፊ የሆነ አትኩሮት ስለገኙ ነው። የምጥ ዘመን … የዳጥም የሆነባችሁ።
አይታክቴው ጋዜጠኛ … ቀጠለልን …
„ከዚህም አልፎ አማራ በብሄሩ ተደራጅቶ መብትን በአገር አቅፍ ደረጃ ማስከበር ይቻላል በማለት በርካታ የአማራ ብሄር ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ሆኗል“ አወና! ይህ የሳጅን በረከት ገፀ በረከት አይደለም። ታሪክን አታፍልስ? ሺዎች የታሰሩበት፤ የሞቱበት፤ የተሰደዱበት፤ ጥፍራቸውን የተነቀሉበት፤ የዘር ማፍሪያቸውን የገበሩበት፤ የጎንደር የሥነ - ከተማ ቅርስ በእሳት በግፍ የነደደበት፤ ሌት እና ቀን በአማራ ተጋድሎ አክቲቢዝም የተሰለፉ የአማራ ልጆች የተጉበት ሰብል ፍሬ አፍርቷል። እኔ እንደዛ ቀን አልቅሼ አላውቅም።
„ እነ አቶ በረከት ስምኦን ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር በተያያዘ የተሳካ ሥራ ሠርተዋል ከተባለ ስኬቱ አማራው በአደረጃጀት ብዥታ ጥርጣሪ ውስጥ እንዲገባ ማድረጋቸው ነወ።“
"ብዣታ" ከትክክት .... ብዥታ የተፈጠረባችሁ እናንተ ናችሁ ታሪክን እንዘርፋለን ብላችሁ መነሳታችሁ አልበቃ ብሎ አማራ መደራጀት አይገባውም ብላችሁ ስታውጁ ከርማችሁ አልሳካ ሲላችሁ ደግሞ „አንድ አማራ“ ብላችሁ ስትንጨባረቁ ፉሩሽ ሆናችሁ የቀራችሁት።
አሁን ደግሞ "አሁኑኑ ፓርላምን በትኑ፤ አሁኑኑ ህገ መንግሥት አፈራርሱ፤ አሁንኑ የሽግግር መንግሥት ይመስረት፤ አሁንኑ የዞግ ድርጅቶች በሙሉ ወደ ሲቢክስ ይቀዬሩ ኦህዴድ ግን እኛ ቦታ እስክንይዝ ድረስ ይቀጥል“ ብላችሁ በቪዥን ኢትዮጵያን ይዛችሁ ከች ብላችሁዋል። መቼም ከደሙ ነፃነን አትሉም።
ያው ግማሽ አካላችሁ የሽግግር መንግሥት ትንሳኤን ስታውጁ የዚህን የሊሂቃኑ ጉባኤን ተማምናችሁ ነበርና። ዋናው የትግል ስልት ተጽዕኖ ፈጣሪ መልቀም ነው። አሻም ካለ ደግሞ ቢና ጢናው አውጥታችሁ፤ ማህበራዊ መሰረቱን ንዳችሁ ብቸኝነትን ትሸልሙታላቸሁ። እንደ ጋዜጠኛ ይህን ተጋፈጥ - ካቻልከው።
አምጠን የኖርን መከረኞች አለንና ስደቱ ላይበቃን። ከስንት በሽታ ላይ እንደጣላችሁን እግዚአብሄር ነው የሚያውቀው። ስንት ሴራ፤ ስንት መሳደድ ... በነጻ ለምናገለግል ምንዱባን? ግፍ ፍሩ! አሸማጋይ ነው አስታራቂ ልትሆኑ ነው ሲባል የሰማሁ መሰለኝ። ያማል።
አሁን አብን በመንፈስ ከፈረሰው ግንቦት 7 ጋራ አብሬ እሠራለሁ ቢል ደግሞ እንደለመደባችሁ ጓዛችሁን ጠቅልላችሁ „አብን የእኛ ጀግና“ ስትሉ ትገኙ ነበር። ዛሬ አንድ ቃለ ምልልስ ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው አድርጎ ነበር ከአንድ ሊሂቅ ጋር „በመንደር አማራ መሰባሰብን አስመልክቶ“ የእሱም ቃለ ምልልስ ያው እምታተመሱበትን የአብን ጥንካሬ እና ጉልበት የጣለበችሁን ስጋት አመላካች ነው። ከዶር ዮሖንስ ገዳሙ ጋር ነበር ቃለ ምልልሱ በትኩረት ዝግጅት እንዳደመትኩት ምጥ ላይ ናችሁ።
እንደ አንተ መስመር ጥሶ ስልልሄደ የልብ ትርታችሁን መከራ እና ማቅ የለበሰውን መንፈስ ግን ለማድመጥ ችዬበታለሁኝ። ተርበተበታችሁ? መጥኔ ብለናል። መሬት ቢሮ ከፍታችኋዋል በቃ በሥራችሁ ልክ መሞከር ነው። ምርጫ ሎተሪም ነው ...
ለዛውም እያንዳንዷ ደቂቃ በዝቀሽ አዳዲስ ዜና የሰመረ ተግባር በመከወን ላይ የሚገኘውን የጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ አሸንፎ ለመውጣት ከተቻለ መሞኮረ ነው ሜዳውም ፈረሱም … እሱን ሞግቱ ለፕሬዚዳንትንት … ለነገሩ አሁን ለማን ይሆን እምትሟገቱት? አለን ድርጅታችሁ? አዲስ ውህደት ምንትሶ ቅብጥሮሶ አዲስ የሚዲያ ሞገድ እዬጠበቅን ነው። ያው የ እናንተ ነገር ያልታከተው ደግሞ ይደከምበት ...
· ቀጣዩ … የመጨነቅ ሐተታ …
„ካለፉት 27 ዓመት ጀምሮ የአማራ ህዝብ በምን መልኩ ቢደራጅ የራሱንም የሌሎችንም መብት አስከብሮ ኢትዮጵያን ማዳን ይችላል የሚለውን ጥያቄ አንስቶ ከፍተኛ ክርክር አደርጎበታል። ክርክሩ ግን ሁሉንም ህዝብ የሚያቅፍ ሁኔታ አልተቋጨም፡፤ ገሚሱ በብሄር መደራጀት ያዋጣል ሲል ገሚሱ ደግሞ በ ኢትዮጵያዊነት መደረጃት ይበልጥ ያዋጣል ይላል፤ ዛሬ ድረስ ይህ ልዩነት በቀላሉ ለምፍታት አልተቻለም።“ ከ አንድ ቤተሰብም ልዩነት እንዳለ አታውቅም። አሁን ታናሽ ወንድሜ ከ እናነተው መንፈስ ጋር ነው ያለው ቀለሜዋ ስለሆነ ተፈላጊ ነው። ሥልጣን ባይፈልግም ግን የመንፈስ ዝንባሌ ያለው ይመስለናል፤ በነገረ አብይ ደግሞ ዴያቆን ስለሆነ ምሰጣው እዬር ሚስጢር ስላቀበለው ተግቶበታል።
ብቻ ምን?! የፈለጉት አበረዋችሁ እዬሰሩ ነው። ያው መቅኗቸው በብልጠት ፖለቲካ ሲሟጠጥ ደግሞ እያለቃቀሱ ይመጣሉ ተሸከሙን ብለው …
የሆነ ሆኖ በአሮጌ በሬ አርሶ ያተረፈ የለም። የሞኝ ጨዋታ መልሶ መላልሶ ሁኖባችሁ ነው። ዓመት ይዞ እስከ አመት አይሰለቻችሁም። አማራ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ያላት? የ80 ብሄር ብሄረሰብ አገር እኮ ናት ኢትዮጵያ። ለነገሩ ኦሮሞም፤ አፋርም፤ ኡጋዴንም፤ ሲዳምም ተሞከረ አሹልኮ አስቀረ እንጂ። ይህን ጎንደሮች „ከሞቱ አሟሟቱ“ ይሉታል። ቁጭ ብላችሁ እያያችሁት ነው ሁሉንም … የሆነው ንደቱም ፍርሰቱም ... መቼም ለመርዶ አጨብጭቡ እንደማንባል ነው?
እማታውቁት ነገር አለ። አሁን መጠጊያ ሌላ ብሄረሰብ የሌላቸው የአማራ ልጆች መቆረጣቸውን ነው። አንተ ችግር የለብህም። እኔ እና የእኔ ቤተሰብ ሆኑ የእህት ወንድሞቼ ልጆች ግን አሁን የጠራ መንገድ ካልተከተሉ ህልውናቸው አይቀጥልምና በአማራነታች መትጋት ግዴታቸው ነው።
መኖር እራሱ በሲሶ ዜግነት ነው። አይደለም ኢትዮጵያ ምድር እዚህ እኔ እህትህ የኖርኩት በሲሶ ዜግነት ነው። ነፃነት ነበር ልትሉን ይሆን ውጪ አገር? ከሆነ እዛው ከቅርብህ ያለውን ዶር አሰፋ ነጋሽን አቅርበህ ስለምን አትሞግተውም? ያውም እሱ በብሄር መደራጀትን አይደግፍም? የአማራን በደል በፍልስፋና ከማብራራት በስተቀር ለሥልጣንም ለዝናም የቆመ አይደለም።
እናንተ ስልጣን ብትይዙ እሱን ዜጋ ማድርግ ትችሉ ነበርን? እኔንስ? በህይወት እንድንኖር ከተፈቀደልንም ያ የሰማይ ገድል ነው። ብዙ ነገር ነው እኔ እማውቀው። ክድን አድርጌ የያዝኩት ብዙ ገማና ነው ያለው።
ዝም ስትባሉ እንዲህ ስለምተነካኩን ነው ሊነገራችሁ ስለሚገባ እምጽፈው እንጂ ፈጣሪዬ የለምነኩትን ስለ አሳዬኝ ስለሰጠኝም ብዙም በዚህ የፍርሻ ፓለቲካችሁን ንቆ መተው ነው የሚጋባው የነበረው።
መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆን እኮ እያዬህ ነው? የትም ቦታ የማያሳፍር፤ ሊደመጥ የሚናፍቅ። ሁሉን አቃፊ። ት/ቤት እኮ አዬር ላይ ተከፍቷል። የደግነት፤ የርህርህና፤ የወገናዊነት፤ የሰብዕዊነት የተፈጥሯዊነት የምርምር ማዕከል ሆኖ የመገኘት ወዘተ …
· ህም?ስትገርም!
„በትግል ጓዶቻቸው ዘንድ ያለፈውን በማዬት እና የወደፊቱን በመናገር የሚደነቁት አቶ በረከት ስምዖን የተንነታኝነት ዕወቅታቸው፤ እንደ ጠንቋይ የሰዎችን እንጂ የራሳቸውን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የማያሳያቸው ሆኖ በመገኘቱተ በመጨረሻም ባሳደጓቸው የርዕዮተ አለም ልጆች የፍ/ቤት ነፃነትን ያዩ እና ታርመው ይወጡ ዘንድ የእስር ቤትን እንዲዩ ተደርጓል።“
አሁን ምኑ ይሆን የሳጅን በረከት መደነቅ? አሁን ጢስ ምኑ ነው የሚደነቀው? እነሱም አደነቅ ቢሉ በአንተ ሚዲያ እንዲህ መነገር ነበረበትን? ገዳይ አፋጅ ሴረኛ ሸረኛ የተንኮል ሥር ምኑ ይሁን በሰዎች ማህበር የሚደነቀው?
„ባሳደጓቸው የርዕዮተ አለም ልጆች የፍ/ቤት ነፃነትን ያዩ እና ታርመው ይወጡ ዘንድ የእስር ቤትን እንዲዩ ተደርጓል።“ ያው ብአዴንን // አዴፓን እንደማለት ነው። አሽሙር መሆኑ ነው። ብአዴንንስ ይበለው። ደግ አደረክ። ከፍና ዝቅ ሲል አይደል የባጀው።
አብንን ለብአዴን ተቆረቆርን ብላችሁ ስታብጠለጥሉት ደግሞ ነበር? ምነው ኤድትርያል ቦርዳችሁ ወጥ አይደለንም? አትናበቡንም? አንዳችሁ ስትክቡ አንዳችሁ ዋቢ ስትሆኑ ሌላችሁ ደግሞ እንዲህ በአሽሙር ትንዱት አላችሁ? ግን ስለምን ይመስልሃል? የብልህነት ፖለቲካ ድህነት?
እዛው ብአዴን ውስጥ ያሉ የአማራ ልጆች አማራነታቸውን ማክበራቸው ነው ኦህዴድን ለዚህ ድል ያበቃው። ሳጅን በረከት ጭንቃላትም የጽልመት ማህበርተኛ የሆነው። ያ ስለሆነ እኮ ነው አሁን ህውሃት ያዝኙ ልቀቁኝ የሚለው። ቢያንስ ይህን ማገናዘብ እንዴት ተሳነህ?
ያው ለኦህዴድ ፈርማችሁለታል እኔ የዛሬ ዓመት ብሄራዊ ድርጅት የመሆን አቅም አለው ስል አፍራሽ የሆነ ዘመቻ ነበር፤ ዘንድሮ ሁሉም የዞግ ድርጅት ይፈርስ ስትሉ በሊቃናት ጉባኤያችሁ፤ ያው ካባ በወርቅ ያለበሳችሁን ብአዴን ጨምሮ ከስሞ ኦህዴድ ነፍሳችን ይቀጥል ደግሞ ተደመጠ። እንደ ሸንብራ ቂጣ መገላብጥ … ሙገሳው ቁልምጫው እስኪያቅለሸልሽን ድረስ አዳምጠናል። ለነገሩ እጅ አውጥቷል። አንድ ዓመት ቢቆይ ብነቱ ሳይታለም የተፈታ ነበርና ... ባይሆን በጽናቱ ይዘልቅ ነበር፤ ለመፍረስ ምን ያጣድፍ ነበር?
· የማልደብቀው።
የሆነ ሆኖ የፍልስፍና ፍደሰት አለበህ። አሁን ሳጅን በረከትን ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር ለማገናኘት የሄድክበት መንገድ ለፈረሰው ማንፌስቶ ጠቃሚነት ያብቃህ አያብቃህ ወፊቱ ትጠዬቅልህ።
በሌላ በኩል ህውሃት „አማራ ጠላት ነው“ ብሎ ፈርጆ 79 ብሄር ብሄረሰቦችን አሳድሞ በአማራ ላይ የፈጸመው የሥነ - ልቦና የዘር የታሪክ ውደምት አንሷል ነው አሁን የሠራኸው። ሁሉም ሰው ሳጅን በረከትን ሲጣላ ሲጸዬፍም አማራ ብሄርተኝነትም በዛ ልክ በዛ መስክ እንዲጠላ፤ በዛ ልክ እንዲመዝን፤ በዛ ልክ እንዲያወግዝ፤ በዛ ልክ እንደያገለል ለማድረግ እጅግ መሰሪ የሆነ መንገድ ነው የተከተልክው። እንዲህ አደናግሬ ትሆናልህ ብዬ አስቤ አላውቅም። ምን ሲል ትዝ አለህ?
ሌላው ስለ ኢትዮጵያዊነት መጠዬቅ ካለበት ድርጅትህን ጠይቀው። አማራ ስለ ኢትዮጵያዊነት አስተማሪ፤ ቀስቃሽ፤ ፕሮፖጋንዲስት አይሻውም። ብቃቱም አቅሙም ለራሱ ይበቃዋል። ትውስትም ገባሪ ወንዝም አይሻም። አማራ ያለው ይበቃዋል። ከሁሉ በላይ አማራ የበታችነት አይሰማውም። ስለምን? ምን እንዳለው? ምን እንደሚችል? ምን ደግሞ እንዳማይችል ጠንቅቆ ያወቃልና? አማራ የመብቱን ጣራና ግድግዳ ያውቀዋል።
የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ለአማራ ለማስተማር ደረጃን ማወቅ ይጠይቃል። አማራነትን የመተርጎም አቅምንም ማጥናት ይጠይቃል። አንድ ማህበረሰብ በመደዴው አይተረጎምም። በዬቤቱ ያለውን ሞገድም ልትለኩት አትችሉም።
በውስጣችን የሚነደው አቅም በቦታው ልክ ቦታውን ማግኘት ግድ ይላል። „ያልተወለድኝ ልጅ ቢለኝ ባባ አፌን አለው ዳባዳባ“ እንዲሉ። ታያችሁ፤ ተፈተሻችሁ፤ የሚገርመው አሁንም ከአማራ ራስ ልተውርዱ አልቻላችሁም። ተወደደም ተጠላም አማራ በብቁ ልጆቹ የአባቶቹን ሌጋሲ ያስቀጥላል።
ይልቅ ስለድርጅትህ „ፈረስ ነው ተዋህደ“ ብቻ ያለዬለት ቅጥ አንባር የሌለው ዜና ሰምቼላሁ እንዲህ ። ተዘባረቀ። አገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞችም እዬተቸገሩ ነው በሥሜለሹ ሥም ወይንስ በቀደመው በዬትኛው እንጥራቸው እያሉ?
እና ድርጅትህ ግንቦት 7 አብን የሚመጥን ሊሂቅ ለማውጣት ይጣር? ፖሊስም ይኑረው? እዚህ እኛን አፍኖ፤ ጠርንፎ፤ አላንቀሳቅስ ብሎ፤ የግል ሰላማችን አውኮ እንደያዘው አገር ቤት ዛሬ ላይ የቤ መንግሥት ሹም ስላልሆነ አይችልምና።
ሌላው ግን ሙግት አትፍሩ። ከፈራችሁ ትረሳላችሁ። ወቃሳንም አትሸሹ። አንድ ጥያቄ ለመጨረሻ ላቅርብልህ ... ቀሪው ጦር የምትመዙበት፤ የምታዘምቱበትም አዲስ ድርጅት ደግሞ ማን ይሆን? ማን ይሆን ባለሰምንት? ይህን በ2008 ጽፌላችሁ ነበር? አውዳችሁ በግጭት የቀለመ ስለሆነ።
እንዳልኩትም „ከመለሳውያን ወደ ለማውያን“ ይዛችሁ ከች አላችሁ። አሁን ያነ አቅም አልደፈር ሲል ደግሞ ወደ አብን ኮተት አላችሁ ነገስ ነው አብዩ ጥያቄው? ለቀጣዩ ለግጭቱም የመንፈስ ትርምስም ለመፍጠር … ይቅናችሁ¡ እንላለን።
አንድም ድርጅት አንድም ሚዲያ ከአብን ጋር እሰጣ እገባ ያለ የለም ከእናንተ በስተቀር … ለዛውም አሁን አለን የምትሉት ድርጅት አልተሰማም ሽግግር ላይ እንዳለ ነው የምነሳማው ሥሜለሹ የመንፈስ ድርጅታችሁ …
መሬት ሁሉንም ስለምትችል ላብን ጠብ አድርጎ የሚሹትን ማግኘት ነው … ወይ ደግሞ መሸነፍን ተቀብሎ ደረጃን ባወቀ ድርድር ካላቸው እንደለመዳባችሁ ጸባአችሁን አሳምራችሁ ተጥግታችሁ መሰረት መያዛችሁን ስታረጋጋጡ ደግሞ ቅብረት?
የሆነ ሆኖ ሜዳውም ፈረሱ ተብላችሁ የለም … ጋዜጠኛም አገር ቤት ቃሊቲ፤ ዝዋይ፤ ቅሊንጦ ለመያዣ፤ ለማሳጫነት የታሰረ ስሌለ ማመካኛም ያለ አይመስልም አሁን ተሆነ … ስለሆነም ቀበቶን ጠበቅ፤ የማህበራዊ ሚዲያን ሰራዊትም ትምክህታችሁ ስለመሆኑ አዳምጫለሁ ማሰለፍ ነው ...
ይልቅ አንድ ነገር ጀርመን ለጤነኛው መንፈስ ቤተኛ ሆኗል። መርዶ ነው ደስታ? አንድ የስልክ፤ አንድ ሉዑክ ቀድሞ በመላክ አሳሳ አድርጎ፤ አንድ ይፋዊ ገብዣ አስከትሎ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሩ ፕሬዚነዳንት የሚመራ ከፍተኛ ልዑክ ልኳል።
መሠረት ያለው ተግባር እንዲህ በቋሚነት ያሰደምማል …. ፈርሶ አይሰራም፤ ተሠርቶ አይፍርስም … ተፍሶ አይለቀምም፤ ተለቅሞ አይፈስም። “ የናቁት ይወርሳል ሆነ…“ አውሮፓ ህብረትም የነበረውን የምሥራች ዜና ክብር እና ሞገስ ሰምተሃል አይደል? ዜና ቢጤ ኮለምክለት ወይንስ በዝምታ እምታ ተሰክቶ ተሰከነ?
· እህ።
አንድ ጊዜ ስለመሬት ያነሳህው የፍልስፋና ዝበትን ሞግቼህ ነበር። የአገር መሪነት እና የጦር ሀይል ጠ/ አዛዥነትን ሉላዊ መርሃዊ ጉዞም ያላገናዘብ ነገር አንድ ጊዜ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደፊት ሲመጡ ጽፈህ ነበር፤ የሳቸው የመኮንነት ደረጃ እና የህወሃቶች ጄኖራሎችን የመምራት ክፈተት አስመልክተህ።
እንኳንስ በሚሊተሪ ቤተኝነት የነበሩ ቀርቶ በዬትኛውም ዓለም የግድ የአንድ አገር መሪ የሚሊተሪ አባልተኝነት አይጠይቅም፤ እናንተም ያነን አስልታችሁ ነበር እኮ ... ብቻ ቢጠይቅ የአሜሪካ ፕ/ ዶናል ትራንፕ አይመረጡም ነበር።
አሁን ደግሞ አማራን ጨቋኝ አድርጎ የተነሳን ንድፈ ሃሳብ ፕሮፖጋንዲስት ሳጅን በረከት ስምዖንን የአማራን የህልውና ተቆርቋሪ አድርገህ ብሄርተኝነትን አዋላጅ አድርገህ ስታቀርብ መገረም አይደለም ውስጥ እቃህን መመልከት ቻልኩት።
የአምክንዮ አቅም የለውምና ያቀርብከው ትንተና። ከተጠሉት፤ ከምንጸዬፈው መንፈስ ጋር አዳብለህ ያቀረብክበት መንገድ ራስህን አጋላጠህ።
አዬህ አሁን አይታወቅም ቀስ እያለ ግን መደመጠንም እያሳጣህ ይሄዳል። የ2015 ያ ሞገዳም ድጋፍ አሁን አለን? ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል ብዬ በ2008 ጽፌላችሁ ነበር „የነፃነት ሃይል“ እያላችሁ የታሪክ ዘረፋ ስትጀምሩ። ይህን ብዙ ሰው አዳምጦልሃል ወደ 40 ሺህ የሚጠጋ ያዳመጠህ ፍሬ ነገሩን ከልቡ ያላዳመጠው አማራው ወገነህ ጭምር ነው። ፈልፈል አድርገን ስናሳዬው ደግሞ ቀስ እያለ እውነት ወደ አለበት ባዕቱ ቀልቡን ይሰበስባል …
ሌላው ልነግርህ የምፈልገው እኔን ሥርጉተ ሥላሴን የሳጅን በረከት ስምዖን አቅም አማራ ሊያደርገኝ አይችልም! ፈጽሞ! መአህድም፤ ሞረሽም አልቻሉምና። ራሱ የሳጥናኤሉ ምስል ለአማራ ህዝብ የጎንደር ህብረትም ጎንደሬ አላደረገኝም! አማራም አላደረገኝም። እኔን አማራ የደረገው ከውስጤ ያደመጥኩት ግለት ነው።
ግለቱ እኔን በሚመለከት ጌጤ ነው የኖርኩበት። ግን አማራን ወክሎ የተገኜ አንድ የአማራ የህልውና ተጋድሎ አክቲቢስት መምህር አቻምዬለህ ታምሩ 2 ደቂቃ የቤተመነግሥቱ የእልፍኝ አስከልካይ ከሆነው ከቪዥን ኢትዮጵያ ሲጠይቅ ያ ቅጽበት ነው እኔን አማራ ያደረገኝ። ቤተሰቦቼ እስካሁን አያምኑም።
ለዛ የአማራ የህልውና ተጋድሎ ለኢሠፓ ለምወደው ፓርቲዬ የሰጠሁትን የመንፈስ ድንግልና ነው የሰጠሁት። ሁለመናዬን ነው የሰጠሁት። እርግጥ ነው የቀደመ አጀንዳ ስለነበረኝ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ በዛ ላይ ብተጋም በሎቢ ተግባር፤ ብራና ላይ ግን ሞግቼቻችሁ አለሁኝ። ደግሞም እረትቻችሁላሁ።
ያ ሁሉ አቅም ያለው ከፍተኛ ድርጅት የእኔ ጹሑፍ አርበትብቶት በዬዘመኑ እያሰደደ ጹሑፌን ማሳገድ ችሏል። ከጹሑፌ ጋር የሚለጠፉትን ፎቶዎች እራሱ መሸነፍን ነው የሚገልጹት። እዬተከታአተላችሁ ምን እንደምትሰሩ ታዳሚ እዬታዘበ ሊንኩን ይልክልኛል። ምን ችግር አለው ዛሬ … ሚዲያ ..?
ከእናንተ የቀደመ የጸጋዬ ድህረ ገጽም፤ የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራምም ያለኝ ሴት እኮ ነኝ። በእጄ ለሚቆረጠው ልመና እምሄድ መስሏችኋዋልን? ለጤነዬ ስል ነበር እንደዛ ያደረኩት። ብቻ እኔን መገደብ ግን አልተቻለም። ቀንበጥ ተጀመረ። በሙሉ በአብይ አክቲቢዝም ላይ የሰራሁት አርኬቡ ላይ አለ። ባልፍም ታሪኩ ህያው ይሆናል። እኔን የሚገድበኝ ሞት ብቻ ነው።
ተረገጡን እምነግርህ አላፍርበትም አማራነቴን ሆነ ጎንደሬነቴንም ። እንዲያውም አማራም ጎንደሬም መሆኔ ባልመካበትም ሐሤት አድርግበታለሁኝ። አባቴም እናቴም አማራ ናቸው። ክብር ለአማኑኤል ይሁን እና ለድምጽ አልባዎቹ እናቶች ልጅ ሰጥቷቸዋል አብዩ አሜኑ የሚባል። ከ እንግዲህ በዚህ ዙሪያ አልደክምም። የትውልድ ሃላፊነቴን አሳምሬ ከውኛለሁኝ። ባልኩት ልክ የሴቶች ጸሀይ ይወጣል እለኩኝ ምስክርነት ሰጠሁኝ፤ ባልኩት ልክ ሁለመናው ተከወነ። ተመስገን!
ወግ ደርሶን 50% የካቢነው እኩሌታ እህቶቼ ይዘውታል። የአገር ፕሬዚዳንት ለመሆን በቅተናል። የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ለመሆን ችለናል። ፍዳዬን ከፍለኩባት፤ የተሳደድኩባት ነፍስም የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሁናልኛለች።
የሞገትከለትት የቅነንት መንፈስ የዓለም ውዳሴ ማርያም ሆኖልኛል። በቃ ከእኔ በላይ ማን ጌታ አለና? ኑሮዬም በቁጥብነት ነው ሞቴም በሰናይ ነው። ይህን የፍሰሃ ዘመን አይ ዘንድ የጓጓሁለት መልካም ዜና አድምጫለሁኝ።
በ2008 የፃፍኩት ቁሞ የሚጠበቅ ስታግናንት የሆነ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናም አመክንዮ የለም ብዬ ከዘመኑ ጋር ትዋህዱ ዘንድ፤ ዘመኑን ታደምጡ ዘንድ በትህትና ጽፌላችሁ ነበር። ያን ጊዜ በዛ እናንተ ባትመሩበትም በራሳቸው መንገድ ዘመንን ያዳመጡት የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ እና የኦሮሞ ፕሮቴስት ተጋድሎን ባክኖ እንደ ለመደበት እንዳይቀር ከውስጣቸው አዳመጡው ልድል አብቀተውታል ብቁዎቹ የመቻቻል አርበኞች።
እናነትንም ጨምሮ ነፃ አወጣችሁ፤ አሁንም እዬሄዳችሁ እምተላተሙት ከማህበራዊ ንቃተ ህሊና ጋር ነው። የጠ/ሚር ቢሮ አብን በሚመለከት ዕወቅና ሰጥቶ አብሮ መክሯል። ከዚያም ባለፈ አንድ ጊዜ ከኦነግ ጋር አንድ ጊዜ ከህወሃት ጋር ስታመሳስሉት፤ የፖለቲካ ነጋዴ እዬተባለ በተብጠለጠለ በማግሥቱ በመንግሥት ሙሉ ድጋፍ ሚዲያ ላይ መግለጫ ሰጥቷል ያው እንደ ደመኛ የምታዩት አብን። የ አባታችሁ ገዳይ አደረጋችሁት።ትንሽ ማህበረሰቡን ማክብር እንዴት ያቅታል? ምልዕተ ጉባኤው እኮ ታይቷል። እነዛም ዜጎች ናቸው። መብታቸው ሊደፈጠጥ አይገባም ነበር።
ለመሆኑ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ "ቅንጅት መንፈስ ነው" ስትል ለመሆኑ የድል አጥቢያ አርበኝነት ነበርን ያነ? የቀድሞ የ አሜሪካ ፕ/ ባራክ ኦባማስ "ይቻላለን" ሲሰብኩ ከዛ በፊት በዬትኛው የትግል መስክ ነበሩ? ደግሞስ ሌላው ለጽድቅ ነው የሚሠራውን? ለፖለቲካ ትርፍ አይደለምን? አውራነት ቀረብን እኮ ነው ይህን ያህል አመት ይዞ እስከ አመት ከአማራ እራስ አላስወርድ ያላችሁ።
ብቻ እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው በሚያስማማው ጉዳይ ላይ ከብአዴን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል አብን። አዬህ ሥራው የእዮር ነው። ፈጣሪ የተገፉትን፤ የተናቁትን ይደርስላቸዋል። ለእኔ አብን እንደ ሌለው ድርጅት ነው እማዬው ጥቃቱን ግን ማዬት አልሻም። አንገት አልሰራላችሁም እንጂ ለእናንተም ስንት እንደሞገትኩላችሁ ታውቃላችሁ "ጉዲት" መባልን ...
ስለ እናንተ ግን ባላዝንም ትግርሙኛላችሁ በቅጡ፤ በጥንቃቄ ልትይዙት የሚጋባው ዕድላችሁን እንዲህ እያሸለካችሁ ነው የምትሄዱት። ኦህዴድን አንታገላልን ብላችሁ ተነሳችሁ መልሳችሁ ከእነሱ እጅ ወደቃችሁ።
ከአብን እጅ ትወድቃለችሁ እያልኩ አይደለም የቀረው የአማራ ህብረ ብሄር መንፈስ በምትወሰዱት እርምጃ ልክ እዬሸሻችሁ ይሄዳል ነው ቁም ነገሩ። ማለቃችሁን እምታውቁት ዘግይታችሁ ነው ብዬ ነበር። አሁንም ዕድሉ እንደዛ ነው። አንዲት መረጃ አፍታ አትቆይም ከማናወቀው ሰው ነው የሚላከው አማራ ነክ ከሆነ። ቢያንስ አሁን ልብ ግዙ። ትንተናው ሁሉ አፈር ድሜ ነው የጋጠው። በጠ/ሚሩ በአሉታዊነት የተተነበዬው ሁሉ ... ብን ትን ብሎ ነው ከስሞ የቀረው ...
ሚዲያ የእናንተ ብቻ አይደለም ዛሬ ተደማጭ የሆነው። የመንግሥት ሚዲያም እኩል ነው የሚደመጠው ዛሬ ላይ። የአብይ ሌጋሲ ለመገምገም እንኳን ጊዜ ሊሰጠን አልቻለም እያጣደፍን ነው ሰንበት የለም አውድዓመት የለ። ውጦናል ማለት እችላለሁኝ። እሚደመጥ ሞልቷል፤ ለዛው እሸት የሆነ፤ ያልጠነዘለ - ያለወዬበ - ዝናብ ሲሄድበት የከረመ አለት ያልሆነ …
ይህ ሁሉ ለማውያን ለሆነችው ሥርጉተ ሥላሴ እለታቱ፤ ደቂቃት፤ ሰከንዳት ሁሉ የልደት ነባቢተ ነፍሷ ናቸው። ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ በዬዕለቱ ሻማ ይበራል። አልጠገብኩትም ያን ሐሤት።
የምኞቴን ነው ያገኘሁት። ያን ቦታ እንዲይዝ እና አቅሙን እንዲያሳይ የኢትዮጵያ ህዝብም አውሮፓ በወጥነት አቅሙን ዕውቅና እንዲሰጠው ነበር ተጋድሎዬ። ተሳክቶልኛል። በህይወቴ እንዲህ የተመኘሁትን አግኝቼ አላውቅም።
ብዙም ግድ አማትሰጠኝ ይህቺ አመዳማ ዓለም ከእንግዲህ ብትቀርም ጉዳዬ አይደለም። ማዬት የተመኘሁትን ልዑሌ አሳይቶኛልና። አይደለም ለእኛ ለአፍሪካም። አሁን ሰው ሚዛን አለው። አንደበትን ሞልቶ የሚያናግር ሙሴ ኢትዮጵያ አላት። የአሮን በትር በዬሄደበት ለምለም መቻልንም የሰጠው የመረቀው። ስንት ግፉዕን ነፍሳችን እንዴት እንዳረፈ እዮር ይመረምራዋል።
ይሄ የቀደመ የጻፍኩላችሁ ነበር።
ሃቅን አትፍሩ!
ቁሞ ዬሚጠብቅ (stagnant)
ዬሆነ ዬአመክንዮ ድንጋጌ - ዓለም አስተናግዳ አታውቅም!
የጎንደሩን አብዮት ሳብያ ስትሉም አንቀጽ 17 የውጫሌ ውል ሳቢያ ነበርን? ብዬም ጽፌ ነበር። የጎንደር አብዮት ሳብያ ሳይሆን ምክንያት ስለነበር። አሁን የናቁት ይወርሳል ሆነ ቁጭ አለ … ወደፊትም እንዲህ የምትዘምቱባቸው ሁሉ እያለፉ ሲሄዱ ቁጭ ብሎ መቅረት አይቀሬ ይሆናል። ለምን? በቅጡ ዘመንን ለማዳመጥ አቅል ስለሌ። ጭፍልቅል የሚያደረግ የግል ክህሎት ሊኖር ይችላል እኔ ተቀብሬ እንደቀረሁት ማለት ነው።
ማህበረሰብን ግን አትችሉም። አማራን ከእንግዲህ ጨፍልቄም ደፍጥጬም እገዛለሁ የሚል ማንኛውም መንፈስ አይችልም። ቆቅ ነው ዛሬ የአማራ መንፈስ። ይህን መንፈስ እወርሳለሁ ወይንም አጥላልቼ አመክናለሁ ማለት ግድግዳን እንደ መደግፋት ነው ከተቻለ ይሞከር …
· መደምደሚያ።
ለፖለቲካ ትርፋማነት ብልህነት ቅንነት እንጂ እንትሪግ እና ብልጠት ዳጥ ነው። የሚያንዘላላጥ ብቻ ሳይሆን አውርዶም የሚያፈርጥ። ቢያንስ የምናከብራችሁ ወንድሞቻችን መንፈሳችን ባትፈትኑት ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቤተኝነት ባናጣችሁ ምርጫዬ ነው።
ሁልጊዜ መውደቅ። መቼ ይሁን እምትሟገቱለት መንፈስ ፈተናውን አልፎ፤ ውጥኑም ባለበት ጸንቶ ደርጅቶ ቡቃያው በቅሎ በቃል ልክ አስብሎ፤ በኩራት ልክ ለምቶ እንዲያው ከ100%/50 ቁንጥጡን የሚያገኘው እሱ ተነስቶ በወደቀ ቁጥር ከፍና ዝቅ የምትሉለት ድርጅታችሁ ግንቦት 7?
ውዶቼ ታዳሚዎቼ „ተናግሮ ከአናጋሪ ያድናችሁ“ ይላሉ የጎንደር ሊቀ - ሊቃውንታት። አላስቀምጠን አሉ።
· አዬህ አቶ ወንድም ..
ከተሞገታችሁበት በጥቂቱ ነው ይህን ለማስተወሻ በጭልፋ የለጥፍኩት እንጂ በዛ መንፈስን በሰልት አዎንታዊነትን እና ብሩህ ተስፋን ክፉኛ በሚያውከው ቀለም እና ድምጸት ልክ ሞጥሬ ሞግቻቸሁለሁኝ።
አሁን በልባችሁ ትክክል እንደ ነበርኩኝ የምታትሙበት ይመስለኛል። ማህል ላይ የነበረው ታዳሚም እንዲሁ። ለዛውም በራዲዮ ፕሮግራሜ ብመጣ ሞገዱ የሚቻል አልነበረም። ዕውነት ከተወገነ ሁልጊዜም ቀን ይወጣለታል።
እኔ ዶር አብይ አህመድ ይሁኑ፤ ኦህዴድ ይሁን እንደ ድርጅት፤ ዶር ለማ መገርሳ ይሁኑ ከግንቦት 7 አይቀርቡኝም አይርቁኝም። ግን አቅም የለሽ ድርጅት ቢያንስ ድምጡን አጥፍቶ ነፍስ ያለው ባለክህሎት ስንዱ አቅም፤ አሸናፊ ሆኖ ይወጣ ዘንድ በሁሉመና መደገፍ ሲገባው በሠራዊት ብዛት አገር ይድን ይምስል ሞከረው እኔም ተዳፈርኩት። እናም ባልኩት ልክ በሞገትኩት ልክ አሸንፍኩኝ። ይኸው ነው።
ውዶቼ የቻላችሁ ፌስ ቡክ ላይ ሸር አድርጉልኝ። ኑሩልኝ። … ጨርስኩኝ።
„አማራነት ይከበር!“
የኔዎቹ ቅኑኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ