ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ- ሕይወት! 31.12.2014ትን በምልሰት።
ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ- ሕይወት! „ለፍጥረቱ ሁሉ ትራራለህ ይቅርም ትላለህ።“ መጽሐፈ ጥብብ ፲፩ ቁጥር ፳፯ ኢትዮጵያዊነት የፍጥረት ዓይነ - ህሊና ነው! እውነተኛ ሐሴትን የመፍጠር አቅሙ ሙሉዑ! ኪናዊ! ከሥርጉተ© ሥላሴ (Seregut© Selassie) ከጭምቷ፡ሲዊዘርላንድ። 31.12.2014 ለመነሻ። የኔዎቹ የፈተና ጥጉ ከ እሰከ የማይበልልት ኢትዮጵያዊነት በ2013 አዲስ ያገረሸ መከራ ነበረበት። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደ መድረክ ብቅ ያሉበት ጊዜ ነበር። የዛን ጊዜ ወጣት ጃዋርውያን በሁሉት ዙር ኢትዮጵያዊነትን ወጥረው የያዙበት ወቅት ነበር። በዓይነት ነበር ፓልቶኩ። ለመስማት ቀርቶ ሰምቶ ለመኖር ፈታኝ ጊዜ ነበር። እናም ይህን ጻፍኩኝ። ዘሀበሻም ፖስት አድርጎት ነበር። ዛሬ በምልሰት ሳስበው የዛን ጊዜው ጉግስ በተለያዬ ሁኔታ እዬታዬ ነው። ኢትዮጵያዊነት ጎላ ብሎ ሲወጣ ኦነግውያን እና ወያኔውያን ደማቸው ይፋላል፤ እሱን እንደ አንጡራ ባላንጣቸው ነው የሚዩት። ልብ ለልብ ሳይገናኙ እነሆ ዘመናት ነጎዱአ እነሱም አፈጁ። ትውልዱም አዲስ ዓራት ዓይናማ አብቅሎ ቀስ እያደረገ እያለበው ነው ጉድፋ ጉድፉን ጉንፋን ዕሳቤ። ተመስገን ነው። በታህሳስ 31 ቀን 2014 የተጠፈው በዛሬው ታህሳስ 11 ቀን 2018 ቤት ለእንግዳ ትለዋላች እትጌ ቀንበጥ። እትጌዋ አብራችሁ ትሆኑም ዘንድ በሞንሟናው ኢትዮጵያዊ አክብሮት ታከብራችሁለች። ማክብረን አትሰስትበትም እና። · ይህ ነበር መንፈሱ … ዛሬ ላይ እትጌ ትግራይን ሳስባት እንደ እኔም እሰቧት በዚህ ውስጥ … የእነ ማህበረ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንታት የትጥቅ እና ስንቅ ጉዞ …...