ልጥፎች

ከኦክቶበር 7, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትጵያ ህዝብ የፍቅር ስጦታን ኤርትራ አደራውን የት ላይ አኖረችው?

ምስል
ፍቱት። „በፊቴም ደጃፉ ሁሉ የተከፈተ ነው፤ በእሳት ቅርጽም የተሠራ ነው።“ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፶፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።               እሙ በአንቺ የመንፈስ ድንግልና ብቻ የፍቅር ተፈጥሮ አደራ አለ።  ·        ፍቱት አንድ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ፍች ያጣሁለት ህልም አዬሁኝ። ስትፈጠር አንድ ጡት ያላት ሴት በህልሜ አዬሁኝ። በዚህ ነጮቹ ሲፈልጉ ጡታቸውን በሰው ሰራሽ እንደሚያስተልቁት በኦፕራሲዮን ወይንም እንደሚያሳድጉት አይደለም። የሴቶች ጡት በተፈጥሮው ግራ እና ቀኝ ደረት ላይ ነው የሚበቅለው። ይህን እናት ጡት የጠባው ሁሉ ያውቀዋል። ይህ በህልሜ ያዬሁት ግን ማህል ላይ የበቀለ፤ ቅርጹ ሆድ የሚመስል ነው። የደረት ሆድ ልበለው ይሆን? እንደዛ ነው እኔ ዛሬ ሌሊት ያዬሁት። እንደነዚህ ያሉ ገራሚ ህልሞች ሳይ ስነቃ ቤቴ ራሱ የእኔ መሆኑን እጠራጠራለሁኝ። አንድ ጊዜም „እኔ ድምጻችን ይሰማ ነኝ ስል እንዲህ የሚገረም ህልም አይቼ ነበር። ደፍሬ ልናገረው አልችልም እጅግ ከባድ ህልም ነበር ያየሁት።  ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ብዙ ሰረጋላዎች የኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማ ለብሰው አዬሁኝ። ሌላ ጊዜም አውስትራልያ በጋብቻ ልሄድ ወስኜ ነበር እና አውሮፕላን ሰማይ ላይ ቆሞ የማይንቀሳቀስ፤ የማይሄድ፤ ልክ እንደ መሬት ሞተሩን አውሮፕላኑ አጥፍቶ ግን ሰማይ ላይ ቆሞ  እንደ ኩሬ ውሃ ረግቶ አይሁኝ። ዛሬ ደግሞ ስትፈጠር የደረት ሆድ ያላት ግን ጡት የሆነ ጨፍ ያለው ልስላሴውም ተፈጥሮውም ጥራቱም ኢትዮጵያዊ የሆነ ጡት አዬሁኝ፤ እርግጥ ነው አንድ መሆኑ ከተፈጥሮ ውጪ ነው፤ ይዘቱ ጡት ነው፤ አፈጣጠሩ ማህል ላይ ነው ብቻ ከብዶኛል?