ልጥፎች

ፍቅር፤ ምህረት፤ ይቀርታ ታማኝነትን ይጠይቃል።

ምስል
ፖለቲካም ታማኝነት  ይርበዋል፤ ይጠማዋል፤ ይናፍቀዋልም።  „ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፤    በእኔም ደግሞ እመኑ።“ የዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                                                       ክብር ናችሁ! ኑሩልን! ·        መቅድም። እንኳን ደስ አላችሁ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ፤ እና አቶ ደመቀ መኮነን። እንኳን ደስ አላችሁ ቅድስት ኦርኦቶዶክስ ተዋህዶ እና ድምጻችን ይሰማ። እንኳን ደስ አለህ የ ኢትዮጵያ ቅን እና ቻይ ህዝብ።  ወግ።  ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል የእቴጌ ጣይቱን ዘመን ጠገብ የብርሃን ውቅር መክሊት ሥጦታ አስጠብቀዋል። ቀደም ባሉት ጹሑፎቼ የቀደመው ዓላማ ዲዛይን ይኸው መሆኑን አስቤ የኢትዮጵያን ሴቶች የፖለቲካ ብልህነትን አነገት እንዳያስደፉ ማሳሰቢያ ጽፌ ነበር። አሁን እሳቸው ያደረጉት ይህን ነው። የኢትዮጵያ ሴቶችን ታማኝነት ልቅና አሳይተዋል። ለፖለቲካ ፍጹም የሚያስፈልገው የአቅም ምንጭ ታማኝነት ነው። የ አገር ፍቅር ብሄራዊ ስሜትም እንዲህ ይገለጣል። ከኢጎ በላይ አገርን ማዬት ይኸው ነው አብነቱ።  በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በህልሙም የማይገኘው ግን አፍቅሮተ ግራ ፖለቲካ ነው። ታማኝነት በግራ ፖለቲካ አሞራ በረረ ቅሉ ተሰበረ ነው። ቀን ሲገነባ አብሮ ይውላል ግራ ዝንባሌ ማታ ሲንድ ያድራል። „ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!“ ያለው ሁሉ አማኝ እንዳልሆነው ሁሉ እንደ ማለት …. አሁን የለውጡ አማራር ሊሂቃን ቁጥር ከፍ ብሏል። ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል፤  አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ለማ መገርሳ፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዶር አንባቸው መኮ

ህመም።

ምስል
የተደከመበት እሾኽ በቀለበት። „እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፤--- በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፤ ሬሳውም በቀን፤ ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይሰጣል።„ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ህመ ም። የጎንደር የአማራ የማንነት የህልውና አብዮት የወለደው የጣና ኬኛ አብዮት ሥጦታ የሰማይ ነበር። መክሊቱም የሰማይ ነበር። ሶሻሊዝም የዘራውን የሴራ የመከራ ምንጭ ከሥሩ ለመንቀል የሚያስችል እዮራዊ መልዕክት ነበር። ሶሻሊዝም ንደፈ ሃሳቡ ብቻ ሳይሆን በዚህ ፍልስፍና ውስጥ ያሉ ሰውን የሚፈትኑ የራስ በሽታዎች አገርን ህዝብን፤ ሰብዕናን የሚንዱ ረቂቅ የወረርሽኝ ጠንቅ አምራችነቱ የግራው ፍስፍና የማህበርስብ ሞራል ጠንቅንም ነው። ህመም! የጎንደሩ አብዮት መንፈስ የጠራው ያ የጣና ኬኛ አብዮት ይገላግለናል ብለን ብዙ ደከምን። ብዙ ለፋን። አሁን ሁሉም ታጥቦ ጭቃ ሆነ። ለውጡ ከሴራ፤ ከተንኮል፤ ተሰርጎ ገቦች  ጥቃት መዳን አልተቻለውም።  እንደ ገና አሁን እንደ ተለመደው በዬጎጆው ጉግስ አለ። ጦርነቱ ጦፏል። ዕንባም መጠጊያ አጥቷል። በዬቀኑ ቤት አልባው ህዝብ ቁጥር እያሻቀበ ነው። ዕንባም የትም ቦታ በዬትኛውም አድርሻ ማግኘት ይቻላል። ዕንባ አብቃይ መሬት መቼ ትዝታ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር፤ "ነበር፡ የምንልበት ዘመን መጣ ሲባል ጥሎን ሄደ ….. ሄደ ሄደ ነጎደ ነጎደ ….ተስፋን እዬጎራረደ፤ የራይ ጥሪትን እያንጓዳጎደ። ህመም! ለችግሩ መንስኤ እኔ ነኝ የሚል አልተገኘም። የችግሩ መንስኤ ግን ቅናት ነው። ቅናት ደንበር ዘለልም ነው። ቅናት የፈጠረው ጦርነት ነው አሁን ይህ ሁሉ ህውከት የሚታዬው። በማንም በምንም አይመከኛም።

ጥርጣሬ ማምረት ለውጡን አይጠቅመውም።

ምስል
የማይጠቅም። „እንግዲህስ እነግርህ ዘንድ እንደ ባለ አዕምሮ ሰው ቁም አለኝ።“   መጽሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፵፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ሳተናው ላይ ስገባ አንድ ጹሑፍ አገኘሁኝ። ጠቅላለ መንፈሱ ቢጠቅም መልካም ነበር። ግን የማይጠቅም አስተሳሰብ ስላለው ትንሽ ማለት ፈልግሁኝ። የሚጠቅመውን አልነካካውም፤ አይጠቅምም የምለውን ሐረግ ብቻ ነው የማነሳው። አግረ መንገዴን አብን ስለተነሳ አንድ ነገር አያይዛለሁ፤ መንፈሱ በቀጥታ ርስቱ አህቲነት ስላለው። መቼም በአብን ላይ  ያለው ማዕት ብአዴን/ አዴፓ ላይ ተሰውሮ የተያዘ መከራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል አዴፓ/ ብአዴን።  https://www.satenaw.com/amharic/archives/65486 የሐዋሳው የኢህአዴግ ጉባኤ እና የለውጥ ሂደቱ ፈተና ! – ኤርሚያስ ለገሰ ፤ ·        የተከበረ ው ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እንዲህ ይላል…   „ የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ከህውሃት ጋር በጠላትነት ከመፈራረጃቸው ባሻገር ጨዋታቸው ኢኮኖሚስቶቹ ” የአውራ ዶሮ ጠብ ” (Chicken Games) መሆኑ በግልፅ ወጥቷል። ለህውሓት ከአዴፓ ይልቅ የአብርሃ ደስታ አረና ፓርቲ ወዳጁ ነው። ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው። ልዩነታቸው እኔ የወከልኩትን ሕዝብ የበለጠ የሚጠቅም አጀንዳ አለኝ የሚለው ላይ ነው። በሀሳብ መተጋገዝ ካየነው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሚቀርበው ዶክተር ደብረፂዮን ሳይሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው። የህውሓት አመራሮች ” ቲም ለማን !”