ልጥፎች

ከኦገስት 16, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ግልበጣ በዬፈርጁ። ድንግዝግዝ በብርዝ ዲቃላዊ መንፈስ።

ምስል
ቆራጣ ነገር ለሚዛናዊ ዕይታ። „እውቀትን ለማን ያስተመረዋል፤? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተው ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ‚ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፲ ከቁጥር ፱ እስከ ፲ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 16.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·          መነ ሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=orfish9aARg Ethiopia - በአዳማ ከተማ የተነሳው ብጥብጥ ዝርዝር መረጃ ይመልከቱ   v      መንትዮሽ እይታ በዚህ ዜና ውስጥ። ·       አንደኛው። አንደኛው ዶር ለማ መገርሳን አዬሁኝ። ግን ከቀደሙት አመራሮች ከማውቃቸው አንድም ሰው የለም። ተሳታፊው ኬፕ ተዘጋጅቶለታል። ዓርማው  ኦህዴድ የቀደመው ዓርማ ነው። ኬፑን እራሱ ሁሉም አላደረጉም። ስለምን የ ኦነግ አርማ ከዚህ እንዳልታዬ አላወቅም፤ ሚሊዬነም አዳራሽ ያን ያህል የፏለለ አርማ ...  ታዳሚው እንደምርጫው መብቱ ተጠብቆለታል። ዶር ለማ መገርሳ ተዝቆ በማያልቀው የስሜን አሜሪካ የህዝብ ፍቅር ከተጠመቁ በኋዋላ ዛሬ ሳያቸው በዛ የሞራል ልዕልና ውስጥ ሆነው አይደለም። አብሶ የሚኒያ ንግግራቸው ድፍረት፤ ወኔ ቆራጥነት የጉድ ነበር፤ የማላውቃቸው እስኪመስለኝ ድረስ። እኔ ብቻ አይደለሁም ሌሎችም መሰል ዕይታ ነበራቸው ... ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ሲሆኑ ደስታቸውን የገለጹበትም ዘይቤ ልዩ ነበር።  በተለይም የአንቦው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የነበራቸው  የዶር ለማ መግርሳ የማሸነፍ ለዛ እና ውስጥ ዛሬ የለም። በቀዘቀዘ እና በደመነ መንፈስ ውስጥ ነው ያዬኋዋቸው። ሰላም መሆናቸውን ማዬት ግን ጥሩ ነው ብያለ

መፍትሄ መፈለግ ብልህነት ነው። በማይታወቅ መንገድ ላይ ነን።

ምስል
መዘናጋቱ አትራፊ አይደለም። በእርግታ አይቶ ለወል መፍትሄ መትጋቱ ግን ግድ ነው። እንዲያውም አንድ ቀንጣ የመፍትሄ አፈላላጊ ነፍስ በመጥፋቱ አሁንም ተዘግይቷል። „በአምላክህ በእግዚአብሄር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም  ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይንም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሰዋ“ ዘዳግም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ሥላሴ 16.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ·       ግ ብግብ ከጭብጥ ጋር። ዶር አብይ አህመድ በሙሉ አቅም ቢሆኑ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው የጠራራ ጸሀይ ግድያ፤ የቆመስ ፈቃዱ ተ/ ማርያም በሥጋ መለዬት፤ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ድንገታኛ ህልፈትን አገር ቤት ሲመለሱ ቢያንስ ለቤተሰብ ደውለው አያጽናኑም ነበርን? የደራሲ ምስብዕከ ወርቁ እኮ ሁኔታውን እንደሰሙ ደውለው ነው ቀጠታ በስልክ ያነጋገሩት፤ በሰኔ 16 ቀን የግድያ ሙከራም ላይ ወዲያውኑ መግለጫ ሰጥተዋል፤ ለዛ ድንጋጤ ሳይንበረከኩ ወዲያውኑ ሄደው ለሰማዕታት ጽናትን በየሆስፒታሉ ተገኝተው ነው የመገቡት፤ ለተሰዉት ቤተሰቦች ደውለዋል፤ ቀድመው ሄደው ደማቸውን ሰጥተዋል። የእርዳት ገንዘብ ሁሉ ሲሰብ ነበር።  በደቡብ ያን መሰል ሰው ሰራሽ ችግር ሲመጣም "ችግር ከማድረሳችሁ በፊት ስለምን እኔን አትጠሩኝም ነበር፤ ብር ብዬ እማጣ አልነበርንም?" ብለው በቦታው ተገኝተው የህዝባቸውን ችግር አዳምጥዋል፤ በማህል የኤርትራ ቸር ወሬ ሲመጣም ልመለስ ልቆይ ሳይሉ አባ ቅንዬ ወዲያውኑ እዛው ላይ እያሉ መልስ ሰጥተዋል። ይህም ብቻ አይደለም በሳቸው ጉብኝት ወቅት የሚደሙጡ የወቀሳ ነገሮችን ሁሉ አጀንዳዬ ብለው በዬተገኘበት አጋጣሚ መልስ ሲሰጡ ነበር። ሌላም ደቡብ አፍሪካ ላይ አንድ የወንጌላውያን ልዩ ዝግጅት ነበ