የዘመን #ዓይናማዊነት በእናታዊነት የምክር አገልግሎት በቅኔ ሲጸና።
የዘመን #ዓይናማዊነት በእናታዊነት የምክር አገልግሎት በቅኔ ሲጸና። " #ምስጉን ነው፤ በክፋወች መንገድ ያልሄደ፥ በኃጢያተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞች መንገድ ያልተቀመጠ።" (መዝሙር ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩) #ምዕራፍ ፲፱። #ጠብታ ። ቤተ - ሥርጉትሻ ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዓለም በየለቱ አዳዲስ ክስተቶች ታጌጣለች፤ ትደመማለች፤ ትጠሞናለች። በዚሀህ በ2026 የዓለም ዋንጫ ሂደት ዓለማችን በፋመ የጦርነት ወላፈን ሆና፤ የወላፈኑን ግርፊያ #ረብ የሚያደርግ ነፋሻ አየር የሆነው የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ የየለቱ ክስተታዊ ገጠመኞችም ነው። ይህ የዓለም ዋንጫ ካስተናገዳቸው ጉልህ እና ጉልበታም ክስተቶች የጊዜውን ሁኔታ የገዛው የስፔን እና የፖርቹጋል ጨዋታ የፈጠረው ክስተት አንዱ ነው። በመጨረሻው የዋንጫ ቀን ከሚፈጥረው ውስጣዊ ስሜት በጣም የላቀው፤ ቃላት ሊገልጹት ያቃታቸው የክርስትያን ሮናልዶ የመራራ የስንብት ሂደት ክስተት አፈፃጸሙ የውስጥ ኦርጋኒክ ነበር። በአንድ ወቅት ዘባስትያን የጀርመኑ ብሄራዊ ቡድን እና የባየር ሙንሽን ተጫዋች፤ ከብሄራዊ ቡድኑ ሲሰናበት፤ እንዲሁም የዶርት ሙንድ አሰልጣኝ ዩርግ ክሎፕ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ ሲሰናበቱ፤ የነበረው ስሜት ብሄራዊ መልክ እንደነበረው አስታውሳለሁኝ። የክርስትያን ሮናልዶ ግን ከዚህ ይለያል። #ግሎባል ነው። ጥልቅ በጣም ጥልቅም ነው። የሁኔታው አፈፃጸም ደግሞ የቀጣይ የተስፋ ዕድል በመቀስ የተቆጠረበት ቅጽበት ፍጹም በሆነ በተለዩ ሁኔታ ነበር። ኤራ ነው። ስለሆነም ይህን ፔጄ በዝም ብሎ እንደ አልባሌ ሊያልፈው...