ልጥፎች

ከኦገስት 18, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። #ፍቅር ሲያልቅም ትዕግሥት ይሰደዳል።

ምስል
  #ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። #ፍቅር ሲያልቅም ትዕግሥት ይሰደዳል።   "ዳዊትም ሰው ከንቱን ይመስላል፤ ዘመኑም እን ጥላ ያልፋል፤ እያለ ስለእሱ ተናገረ።" (መጽሐፈ መቃብያን ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፳፫)   #ምዕራፍ ፲፱።   ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅር ሲያልቅም ትዕግሥት ይሰደዳል። በህወሃት መሸኛ ዘመን እጠቀምበት የነበረ አገላለጽ ነው። የሆነ ሆኖ አብን የሚሊዮኖች ድምጽ ሆኖ ወጥቶ፤ ያን ኃላፊነት እና ግዴታውን የተወጣበት መንገድ ግን ተስፋ ሰጪ አልነበረም። ሥልጣንን በሚመለከት አንድ የፖለቲካ ድርጅት የሚታገልበት በኽረ ጉዳይ ስለሆነ ለጋሱ ብልፄ ያቀረበለትን ገጸበረከት ይሁንታ ሰጥቶ መቀበሉ ለእኔ የሚጎረብጥ አልነበረም።    ግን መነሻውን ከመድረሻው ለማዋህድ የተከተለው መስመር ግን ለአማራ ይሁን ለኢትዮጵያኒዝም የተስፋ ሂደት #እክል ነበር። ለብልፄ ብሎ አላስፈላጊ ቅራኔ ሁሉ ይገባ ነበር። ሁልጊዜ ከህውሃት ("ትህነግ") ጋር የነበረው አቲካራ አላስፈላጊ ነበር።    አንድም የአማራ ጥያቄን የማስመለስ አቅምም አልነበረውም። በሌላ በኩል እሱ ያመነበትን መንገድ የሚከተሉ አማራወችን የማግኜት ዕድሉም ስስ ነበር። ስለሆነም ብልፄው የአማራ ህዝብን አራጦ ለመግዛት ዕድሉን አብን የማመቻቸት ዕድል ለብልፄ ማጉረስ አልቻለም። የተወሰኑ የአብን አመራሮች ህይወትን የማሻሻል ነገር እንደ ትርፍ ካየው ይሁንለት።    የሆነ ሆኖ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #የበኽር ልጃቸው ነው። ለትውልድ እንዲሆን አድርገው በሚገባ አደራጅተውታል። እኔም እከታተላቸው የነበረው ከዛ አንፃር ነበር። ልዩ ጊዜ ያሳለፋበት በኢትዮጵያኒዝም መንፈስም ያ የማይገኝ ጊዜ ይመስለኛ...

"ላም እረኛ ቢቆጣ ምሳው ራቱ ይሆናል።"

ምስል
  "ላም እረኛ ቢቆጣ ምሳው ራቱ ይሆናል።"   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       አንድ ቀን ለቀረው የምክክር ኮሚሽን ጉባኤ የትኛውም ተቋም፤ የትኛውም ድርጅት፤ የትኛውም ቡድን የምክክር ኮሚሽኑን ስብሰባ #ጥሎ ቢወጣ የሚያመጣው #ለውጥ ምንም የለም።   ይልቁንም በራስ ላይ ድርብ #ሰንሰለት ከማምጣት በስተቀር እርምጃው አትራፊ አይደለም።   ከተገኙ ላይቀር #በንቃት #መሳተፍ ፤ የማይመቹ ጉዳዮችን መሞገት፤ ቅሬታን በተደራጀ ሁኔታ መግለጽ።    የራስ ደህንነትን መጠበቅ። ከትርፍ ንግግር መቆጠብ ይገባል።   በተረፈ #በተጠናቀቀ ሁኔታ ላይ #ጥሎ መውጣት አትራፊ ውሳኔ አይደለም። ከራስ ጉዳት በስተቀር #ለብፄ #የሚያጎድልበት ነገር #አንዳችም የለም።    ውዶቹ ደህና እደሩልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ 18/08/026. ውብ የእንቅልፍ ጊዜ እመኛለሁኝ። See less