፭ቱለ፯ዓመታት #የፖለቲካ ፋክክር ስለ ኢትዮጵያ የትውልድ የተስፋ #ልምላሜ ወይንስ #ጥንዘላ?
፭ቱለ፯ዓመታት #የፖለቲካ ፋክክር ስለ ኢትዮጵያ የትውልድ የተስፋ #ልምላሜ ወይንስ #ጥንዘላ ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" (1) ዶር ደብረጽዮን ገብረ ሚኬኤል፤ (2) ጠሚር አብይ አህመድ አሊ፤ (3) አቶ እስክንድር ነጋ፤ (4) አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)፤ (5) አቶ (ጃል) መሮ፤ • ፋክክሩስ የፖለቲካ ድርጅት ፎርማት ይዞ ወይንስ የሰብዕና ምኞት አዝሎ? • በገፍ ለሚገበረው የሰው ልጅ እልቂት ተጠያቂነት እና ኃላፊነቱ የማን ይሆን? • ብድሩ እስከ አራጣው ሳይመለስ የወደመው የህዝብ አገልግሎት ተቋማት ጉዳይስ ባለዕዳው ማን ይሆን? • ቁጥቦቹ የአፋር የፖለቲካ ሊቃናት የእነሱ ሰራሽ ባልሆነ የፖለቲካ ፋክክር ለደረሰው ሁለገብ ድቀት፤ የእድገት መስተጓጎል ምን ካሳ ታስቦላቸቸው ይሆን? • በዚህ እልህን አንቀልባው ባደረገ፤ አደብ በነሳው ፭ቱ የ፯ ዓመታት የሊቃናቱ የፖለቲካ ፋክክር የመከራ ዘመን ትውልዱ ምን አተረፈ? • የ፭ቱ የፖለቲካ ፋክክሩ በቀጠለ ቁጥር በትውልዱ ሥነ ልቦና ከፍታ እና ዝቅታ ትዕይንቱ ውስጥ ኢትዮጵያ ታተርፍበት ወይንስ ትከስርበት ይሆን? • የኖቤል ሽልማት ምን አሳጣ፤ ምን አስገኜ? ምንስ እማናውቀው ሚስጢር ገለጠ? • የኢትዮጵያ የደም መሬትነት ሂደት ማብቂያው መቼ ይሆን? • ኢትዮጵያ በቲም ብትመራ ተስፋዋን በጤናማ መንፈስ ማብቀል ይቻል ይሆን? • በነፃ የሚለገስ የአቅም አያያዝ፤ የአቅም አደረጃጀት፤ የአቅም ዕቅድ፤ የአቅም የዕቅድ አፈጻጸም መቼቱ ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ጋር ይተዋወቅ ይሆን ጥሞና የሚባል የራስ ላፒስ ለኢትዮጵያ መሪነት ራሳቸውን ካጩት ጋር መቼ ይሆን ድፍረቱን የምና...