፭ቱለ፯ዓመታት #የፖለቲካ ፋክክር ስለ ኢትዮጵያ የትውልድ የተስፋ #ልምላሜ ወይንስ #ጥንዘላ?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"





• ፋክክሩስ የፖለቲካ ድርጅት ፎርማት ይዞ ወይንስ የሰብዕና ምኞት አዝሎ?
• በገፍ ለሚገበረው የሰው ልጅ እልቂት ተጠያቂነት እና ኃላፊነቱ የማን ይሆን?
• ብድሩ እስከ አራጣው ሳይመለስ የወደመው የህዝብ አገልግሎት ተቋማት ጉዳይስ
ባለዕዳው ማን ይሆን?
• ቁጥቦቹ የአፋር የፖለቲካ ሊቃናት የእነሱ ሰራሽ ባልሆነ የፖለቲካ ፋክክር ለደረሰው
ሁለገብ ድቀት፤ የእድገት መስተጓጎል ምን ካሳ ታስቦላቸቸው ይሆን?
• በዚህ እልህን አንቀልባው ባደረገ፤ አደብ በነሳው ፭ቱ የ፯ ዓመታት የሊቃናቱ የፖለቲካ
ፋክክር የመከራ ዘመን ትውልዱ ምን አተረፈ?
• የ፭ቱ የፖለቲካ ፋክክሩ በቀጠለ ቁጥር በትውልዱ ሥነ ልቦና ከፍታ እና ዝቅታ ትዕይንቱ
ውስጥ ኢትዮጵያ ታተርፍበት ወይንስ ትከስርበት ይሆን?
• የኖቤል ሽልማት ምን አሳጣ፤ ምን አስገኜ? ምንስ እማናውቀው ሚስጢር ገለጠ?
• የኢትዮጵያ የደም መሬትነት ሂደት ማብቂያው መቼ ይሆን?
• ኢትዮጵያ በቲም ብትመራ ተስፋዋን በጤናማ መንፈስ ማብቀል ይቻል ይሆን?
• በነፃ የሚለገስ የአቅም አያያዝ፤ የአቅም አደረጃጀት፤ የአቅም ዕቅድ፤ የአቅም የዕቅድ
አፈጻጸም መቼቱ ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ጋር ይተዋወቅ ይሆን ጥሞና የሚባል የራስ
ላፒስ ለኢትዮጵያ መሪነት ራሳቸውን ካጩት ጋር መቼ ይሆን ድፍረቱን የምናየው፤ ይህ
ሃሳብ አቶ ጃዋር መሃመድን (ሃጂን) አይመለከትም። ሆኖ አሳይቶናል እና።
• ልዩ ማስታወሻ።
የፎቶው ቅደም ተከተል የፖለቲካ ሲነሪቲን የተከተለ ነው። ስለ ፖለቲካ ስንጋገር ፕሮቶኮል አውራ ጉዳይ ይሆናል። ያን ሰብዕና ጉዳያችን አድርገን ስንወያይ። እኔ የፖለቲካ ህይወቴ ሀሌታ ያለው በዚህ ዲስሊን ውስጥ ነውና። በየፖለቲካ ድርጅታቸው ቁጥር አንድ ሊሆኑ ይችላሉ። ለእኔ የዕይታ ግምገማ ግን በፖለቲካ የአደረጃጀት መርሆ ሊሆን ግድ ነውና በፖለቲካ ተሳትፏቸው አጀማመር ቅደም ተከተል ሊሆን ይገባል።
• የጉዳቱ ማህበርተኞች።
(1) የአማራ ህዝብ።
(2) የተጋሩ ህዝብ።
(3) የአፋር ህዝብ።
(4) የኦሮሞ ህዝብ።
(5) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እንደ ተቋም፤ ማህበረ ምዕመኗ፤ ወዳጆቿም።
(6) የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት።
(7) የኢትዮጵያ ሥልጣኔ።
በዚህ መሰል ጹሁፍ ተጠፋፍተን ሰነበትን። ማህበረ ቅንነት እንዴት ሰነበታችሁ? ለመነሻ ያቀረብኳቸው መጠይቆችን እናንተው ፈታትሿቸው። እኔ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ልል ፈቃዴ አይደለም። በጥቅሉ ግን የማነሳቸው ሃሳቦች ይኖሩኛል።
የሆነ ሆኖ #በደም #የተነከረው የ፯ ዓመታቱ ገጸ ባህሬ ስገመግመው የፖለቲካ ድርጅቶች ተፈጥሯዊ ፋክክር ሆኖ አላገኜሁትም። በዚህ የ፭ቱ እልህ አስጨራሽ የፖለቲካ ፋክክር ያልጠፋ፤ ያልተቃጠለ የመንፈስ አቅም፤ የተስፋ ቋት፤ የምኞት ጉልላት የለም።
በአመዛኙ የተፈጠረው ውድመት ይሁን ሰቆቃ እስኪ አቅማችን #እንለካካ ዓይነት፤ ባልተመጣጠነ የአቅም እሰጣ ገባ እና ፋክክር ነው ሙሉ ፯ ዓመት ኢትዮጵያ እና ልጆቿ የመከራ ዝግን እንዲዘግኑ የተገደዱት።
ሳይለንት ማጆሪቲ ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ዕይታቸውን ቢያጋሩን ምኞቴ ነው። እኔ የደረስኩበት ማጠቃለያ ግን ይህ ነው። የሁሉም የኢትዮጵያ ችግር መዳረሻ የ፭ ሰብዕናወች #የምኞት የፖለቲካ ፋክክር ሆኖ ነው ያገኜሁት። ስለሆነም መፍትሄው ሊፈልቅ የሚችለው ከእነሱ ዘንድ ነው ብዬ አስባለሁኝ።
በተለይ ባለ ሙሉ ሥልጣን ባለቤቱ ጠሚር አብይ አህመድ ትዕግሥት አልቦሽ እርምጃቸውን ወደ ኋላ ተመልሰው ገምግመው፦ በራሳቸው ጊዜ ይህ በዬቀኑ በግፍ የሚደበደበውን የንጹኃን ግድያ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊያስቆሙት ይገባል የሚል ጠንካራ ዕሳቤ አለኝ። መጀመሪያ ሰው ሰራሽ የሆነው የህዝብ ሞት ይቁም።
ማንም ሰው እመጥናለሁ ብሎ ለሚያስበው የመሪነት ቦታ እራሱን ማጨት ጤናማ ሃሳብ ነው። ሌላ ጓዝ ካልተሸከመ። ጓዝ ሲኖር ነው የበቀሉ ፋስ የሚጠነክረው። እኔ ፯ ዓመት ያዬሁትም ይህን ነው።
ፋክክሩ የቀጥታም፤ የጎንዮሽም አለበት። አስፈላጊ አይደለም ብዬ እንጂ በግራፍም መሥራት እችል ነበር።
1) #ለምሳሌ ዶር ደብረጽዮን ፋክክራቸው ከጠሚር አብይ አህመድ ጋር እንጂ ከአቶ እስክንድር ነጋ ወይንም ከአቶ ጃዋር መሐመድ (ሃጂ) ወይንም ከአቶ (ጃል) መሮ ጋር ሆኖ አስተውዬ አላውቅም።
2) #አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እና ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር እንደሆነ ይሰማኛል።
3) አቶ እስክንድር ነጋም አሁን ከሆነ ተጨማሪ ተፎካካሪ ቢኖረውም መነሻው ግን ከጠሚር አብይ አህመድ፤ ከአቶ ጃዋር መሃመድ፤ #ከደን ባለ ሁኔታም ከቲም ገዱ ጋር እንደ ነበር ይገባኛል።
5) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ከሁሉም ከአቶ እስክንድር ነጋ እና ከአቶ ጃዋር መሃመድ ጋር ጠንከር ያለ የውስጥ ፋክክር
እንደሚያደርጉ ይሰማኛል። ቀደም ባለው ጊዜ ከዶር ደብረጽዮን ጋርም፤ በተለይ በውስጣቸው ለአቶ እስክንድር ነጋ የፖለቲካ አነሳስ ዕውቅና ለመስጠት በጣም የሚያቅራቸው ብቻ ሳይሆን የመከራው መዶሻ ማወራረጃ የአማራ ህዝብ በነቂስ እና የአዲስ አበባ ህዝብ እንደ ሆነ ይሰማኛል። ብዙ ግብር ሁለቱም ከፍለውበታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቀደምት የአብነት ተቋማት እና ገዳማትም ከበቀሉ ፋስ አላመለጡም።
ምን ዓይነት መላዕክ ቀን ቀርቦ፤ ምንኛ ብንታደል መገመት የማልችለው ጉዳይ ቢኖር አቶ እስክንድር ነጋ እና ጠሚር አብይ አህመድ በአካል ተገናኝተው ችግሩን ይፈታሉ ብዬ ለማሰብ በጣም ይርቅብኛል። የአማራ ህዝብ በክልሉም ይሁን ከክልሉ ውጪ ለከፈለው ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራ ሚስጢሩ ያለውም ከዚህ #ዕድምታ ውስጥ ነው። በክብ፤ በዲያጎናል፤ በትርያንግል፤ በሬክታንግል ሳሰላው የመከራው ፒላር ያለው በዚህ ውስጥ ነው።
ቢያንስ የኦሮሞ ህዝብ ሁነኛ አለው። ለዛውም ተፈሪ። የፖለቲካ ድርጅቶች አነሰም አደገም አላቸው። የአማራ ህዝብ ግን የፖለቲካ ድርጅት የለውም። የሚፈራ የለውም። ግዙፋን መስዋዕትነት እዬከፈለ የሚገኜው ፋኖ እንኳን በሩ ዘብ የሌለው ስለሆነ ማህበራዊ መሠረቱን ያጣው፤ በእሱ ማገዶነት ምኞቱን ማሳካት ለሚፈልግ ሁሉ በኮፒ ራይት ነው ፍዳውን እያዬ የሚገኜው።
የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ትርፍ የማህበረ ኦነግ ኢትዮጵያን፤ አህጉሩን ይመሩ ዘንድ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ውጪ ትርፋ ምንም ነው። በግለሰብ የዕውቀት ልቅና ዕድል፤ ወይንም ሽልማት ቢጤ እና ዕውቅና ያገኙ ነፍሶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ከዚህ በተረፈ መኖሩን ያጣበት ክስተት ነው የተፈጠረው።
#ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ………
በዚህ ሂደት ወደ ትግል የተሳቡ ነፍሶች ይኖራሉ፤ አዲስ ተጽዕኖ ፈጣሪወች ተከስተዋል። ነባር ትንታጎችን ደግሞ ትግሉ አጥቷል። በሞትም በዘመቻም።
በነገረ አማራ ጉዳይ ባለቤቱ ብዙ ነው። የደከመውም ብዙ ነው። መስዋዕትነቱም ወዘተረፈ ነው። ስለሆነም ከአንድ ሰብዕና ጋር አብይዝም ድርድር ቢፈጽም የችግሩ መፍቻ ቁልፍ ሊገኝ የሚችል አይመስለኝም። እርግጥ ነው የአዲስ አበባ ህዝብ እና የአማራ ህዝብ የከፈለው መስዋዕትነት የሁለት ሰብዕና ስውር ፍትጊያ ነው ያስተዋልኩት።
እዬዋለ እያደር ሲሄድ አሁን ባለው ሁኔታ እኔ ስታዘበው፤ የትግሉ መጠነ ሰፊነት ባለ ሙሉ ድርሻ ነን የሚሉትን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዕውቅና ሰጥቶ ችግሩን ዘላቂ ዕልባት መስጠት የዊዝደም መሰጠትን ይጠይቃል።
በተለይ ጠሚር አብይ አህመድ በዬጊዜው አያልቅ ዘመቻ በዘመቻ የአማራን ህዝብ መንፈስ አስገብራለሁ ብለው የሚሄዱበት ጉዞ አድካሚ፤ አውዳሚ፤ ዳጥ እና ዳገት እርምጃ ነው ብዬ አስባለሁኝ። መሪ ሁልጊዜ አሸናፊ መሆንን ሊመኝ ይችላል። ለትውልድ ሲል ደግሞ መሸነፍን ሊቀበል ይገባል ብዬ አምናለሁ።
ሁላችንም በህይወታችን ማሸነፍ የአባት ነው እንመኛለን። የሸነፍ ሲመጣ ቢጎመዝዝም አጣጥመን መቀበል ካልቻልን፤ ህይወት አይቀጥልም። ይቋረጣል። ለፖለቲካ መሪነት ግትርነት አኞ ሥጋ ወይንም ጠፍርነት ነው። የሽጥ ሥጋነት ግን ለትውልድ ይበጃል። ገራራው መንገድ የአማራን እና የአዲስ አበባን ህዝብ ዋጋ አስከፍሏል።
ቅጽበታዊነት፤ አደብ ማጣት፤ ተረጋግቶ ፍላጎትን ማስከን አለመቻል። በመርህ ለመመራት አለመፍቀድ በውስጥ በሚፈጠር አናርኪዝም አካባቢውን እዬበከለ ባልተለመደ የወንጀል ዓይነት ህዝባችን ተገርፏል። በቃ! ሞት። በቃ! እንግልት። በቃ! ስጋት። በቃ! አሳይኃለሁ ፋክክር። #አንድ ልጅ የጀንበር #ዳንቴል አይደለም። ብዙ የኢትዮጵያ እናቶች ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ማህጸናቸው አሯል። ሊካሱ ይገባል። ይህ ደግሞ ከመንበር ቁብ ባለ ትዕቢት እና አሜኬላዊ ሴራ ሳይሆን በትህትና እና በቅንነት ሊሆን ይገባል።
በጣም ሩቅ የሆነው ለሰው ልጅ ማዘን፤ መራራት። ለእንባው ፈጣን ደራሽነት እና አጽናኝነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልተለመደ ቢሆንም እራስን አሸንፎ መጀመር ግን ሥልጣን ላይ ከአለው አብይዝም የሚጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ይመስለኛል። አዲሱ ዘመቻም ክረምት ከመግባቱ በፊት የሚባለው ሊገታ ይገባል። #ተግ ይባል። ሁልጊዜ ለመግደል መፍጠን ሰይጣናዊ ንቅናቄ ነው።
በትህትና፤ በደግነት፤ በርህርህና ግትር ያሉ ሁነቶችን መግራት ይቻላል። መሪነት ማለት ለእኔ ይህ ነው። የመሪነት ሥልጣኔ ለእኔ #ሰዋዊነት ነው። አስፓልት፤ ህንፃ፤ መዝናኛ መንፈሱ የተረጋጋ፤ የመኖር ዋስትናው የተረጋገጠ ህዝብ መሻት እንጂ አዳራሽ ሙሉ ስጋት አጭቶ መዝናኛ??? --- ያቅራል። ለእኔ ጭካኔም ነው። መቅድም አፈሙዝ ፀጥ ረጭ ይበል። መጠለያ ከፈን ይኑር። ንፁህ ውሃ እና የህክምና አገልግሎት ይሟላ። ቅንጦት ጥሩ ነው። ግን የአስተዳደር እና የአመራር ሰውኛነት ይቅደም። ተፈጥሯዊነት ይቅደም። አይዟችሁ ባይነት ይቅደም።
#የፖለቲካ አቅም፦ እንደ መከወኛ።
1) በመሪነት ጥራት እና ብቃት፤
2) በትልም ሃሳብ እና አፈፃፀም፤
3) በማደራጀት አቅም እና ክህሎት፤
4) አዲስ ሃሳብ በማፍለቅ እና በአፈፃፀም ክትትል፤
5) በርህርህና እና በአጽናኝነት ምርቃት፤
6) በንግግር ጥበብ እና ዕድምታው፤
7) በተንባይነት አቅም እና ክስተታዊነት፤
8) በበሳል ሃሳብ አፍላቂነት አደራጅነት እና መሪነት፤
9) ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን በመቀበል እና በመወጣት፤
10) በጠፋ ጥፋቶች ላይ በራስ ላይ በሚወሰድ እርምት፤ ጸጸት እና ይቅርታ በመጠዬቅ ደፋር እርምጃ አወሳሰድ፤
11) በሰውኛ እና በተፍጥሮኛ አቅም፤
12) ለኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ቅርበት እና ርቀት። የሰው ልጅ የመስክ ስንደዶ ወይንም ሰበዝ አይደለም እና። አሁንም ለመነሻ በአቀረብኳቸው አመክንዮወች አንባብያን የራሳቸውን ነጥብ ሊሰጡ ይችላሉ፥
13) የረጋ የመንፈስ ውርስ ከዬትኛው ፖለቲከኛ የህሊና ጓዳ ታደመ?
14) መሪነት አዛዥነት ብቻ ሳይሆን፤ ታዛዥነትም ስለመሆኑ የታዬ ግብረ መልስም ከኖረ ታክሎ ቢገመገም።
የት ላይ አቅም ከሞላ ጎደል #መስከን እንደሚችል የቤት ሥራውን ለፁሁፌ ታዳሚወች መተው የተሻለ ሲሆን። የመነሻ መገምገሚያ ፭ቱ ፖለቲከኞች ከዕለተ መጋቢት 18/2010 ጀምሮ በወጠኗቸው የአካሄድ ስኬት እና ቀጣይነት፤ ወይንም የውጥን መንኮላሸት እና የአቅም ፍሰት ከንቱ መቅረትን በምልሰት የግምገማ መነሻ ማድረግ የሚቻል ይመስለኛል።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሸበላ ምሽት። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergure©Selassie
19/03/2025
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ