«ኤርትራ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ቀውስ "ምንም ሚና" የለኝም አለች» BBC መካሰሱ ለሁለቱ መንግሥታት አይጠቅምም።
መካሰሱ ለሁለቱ መንግሥታት አይጠቅምም። አደብ ገዝቶ በጭብጦች ላይ ቅናዊ ውይይት አድርጎ ትውልድን ከዘላቂ ስጋት አላቆ የውስጥ ሰላምን የሚያረጋግጥ ብልህ አመራር ይጠይቃል። ወጣትነት መንፈስ የሚፈታተነው ግብግብ ኪሳራ ያሳፍሳል። የሥርጉትሻ ዕይታ።
19.03.2025
------------------------------------------------------------
የፎቶው ባለመብት, Yemane G. Meskel/X
ከ 7 ሰአት በፊት
«የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ፤ አስመራ በህወሓት እና በትግራይ ክልል "ጊዜያዊ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ግጭት" ውስጥ "ምንም አይነት ሚና" እንደሌላት ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ "የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር" ግፊት እንዲደረግባት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጥያቄ አቅርበዋል።
ኦስማን ይህንን የተናገሩት ማክሰኞ፣መጋቢት 9/2017 ዓ.ም. መቀመጫቸውን አስመራ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እንደሆነ የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል።
ማክሰኞ ጠዋት በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ማብራሪያ የተሰጣቸው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፤ "አምባሳደሮች" እና "የዲፕሎማቲክ ኮር አባላት" እንዲሁም በሀገሪቱ "እውቅና የተሰጣቸው የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት ተቋማት አመራሮች" መሆናቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ እና በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የከረረ ውጥረት ተፈጥሯል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ሳምንት አንደኛው የህወሓት ክንፍ የአገሪቱ ተቀናቃኝ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እና ትብብር አለው በማለት መውቀሱ አይዘነጋም።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ማብራሪያ፤ ሶስት ጉዳዮችን በዋናነት ማንሳታቸውን የማነ ተናግረዋል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጉዳዮች በኤርትራ ላይ የቀረቡ "ሀሰተኛ ክሶችን" የሚመለከቱ እንደሆኑ በማስታወቂያ ሚኒስትሩ መረጃ ላይ ሰፍሯል።
በቀዳሚነት የተጠቀሰው "ኤርትራ በኢትዮጵያ ጦርነት ለመክፈት እያደረገች" ነው ስለሚለው "ግምታዊ" ክስ ነው። ሁለተኛው ክስ የፕሪቶሪያ ስምምነትን የተመለከተ እንደሆነ ተገልጿል።
ማብራሪያ ተሰጥቶበታል የተባለው ሶስተኛው ጉዳይ ደግሞ፤ "የኢትዮጵያ የባህር በር [የማግኘት] አባዜ" እንዲሁም "ይህንን ተከተሎ" የመጣው "ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ" እና "አብሮት ያለው" ተንኳሽ ድርጊት እንደሆነ ተጠቅሷል።
የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ይህንን ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጤሞቲዮስ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመሆን በተመሳሳይ አዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ከሰጡ ከቀናት በኋላ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን እና ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 5/2017 ዓ.ም. የሰጡት ማብራሪያ በትግራይ ክልል በህወሓት አመራሮች መካከል ከተፈጠረው ቀውስ ጋር የተገናኘ ነበር።
በዚህ ማብራሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ "ለኢትዮጵያ ጠበኛ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ እና እየተባበሩ" መሆኑን በመጥቀስ ከስሰው ነበር።
በወቅቱ ገለጻ የሰጡት አቶ ጌታቸው በበኩላቸው በሌላኛው ክንፍ የሚገኙ "የተወሰኑ" የህወሓት እና ወታደራዊ አመራሮች "ከፌደራል መንግስት ጋር በሚደረግ ንግግር የመደራደር አቅማቸውን ለማሳደግ በሚል የኤርትራ" አመራሮችን ማግኘታቸውን ተናግረው ነበር።
ይህንን ክስ ህወሓት የማይቀበለው ሲሆን በቅርቡም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሌተናንት ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ የጸጥታ ሃይሎች ከኤርትራ ጋር ግንኙነት አላቸው መባሉ ስህተት ነው ብለዋል።
የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ ግን "የኤርትራ መንግስት በህወሓት እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል እየተካሄደ ባለው ውስጣዊ ግጭት ምንም አይነት ሚና የላትም" በማለት ማስተባበላቸው ተገልጿል።
ኤርትራ ከዚህ ውጪ የሚቀርቡ "ክሶች እና ውንጀላዎችን ሙሉ በሙሉ"ውድቅ እንደምታደርግም አስረድተዋል ተብሏል።
የኤርትራ መንግስት፤ የፕሪቶሪያ ስምምነትን "የሚመለከተው የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ" አድርጎ መሆኑን የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሀገራቸው በስምምነቱ "ሂደት ጣልቃ የመግባት ምንም ፍላጎት እንደሌላት" እንደገለጹ ተጠቅሷል።
"በጥቅምት 2015 ዓ.ም. ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ" የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት "ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው የኤርትራ ድንበር ውስጥ መልሶ መሰማራቱን" የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዲፕሎማቶች ማስረዳታቸውን ተገልጿል።
ኦስማን፤ "የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት አሁንም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዳለ የሚናገር ወይም የሚያመለክት ማንም [አካል] ይህንን የሚያደርገው ለኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሮች ኤርትራን ማምለጫ ለማድረግ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ወግኖ የተዋጋው እና በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጸም ወንጀልን ጨምሮ በተለያዪ የጦር ወንጀሎች እንደፈጸመ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሪፖርት ያወጡበት የኤርትራ ጦር አሁንም በትግራይ መሬቶች እንዳለ በተደጋጋሚ ጊዜ ተነግሯል።
የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ወሲባዊ ባርነት፣ ግድያዎችን እና ሌሎች ከባድ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው አምነስቲ ማስታወቁ ይታወሳል።
እነዚህ ክሶች በኤርትራ ላይ "የሚነዙት" የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኮሚሽንን "አሳሪ እና የመጨረሻ" ውሳኔ "ገና ከጅምሩ ውድቅ ካደረጉ እና እየተቃወሙ ከቀጠሉ የቀድሞ የህወሓት አባላት" እንደሆነ ኦስማን ተናግረዋል ተብሏል። እነዚህ አካላት "በኤርትራ የስርዓት ለውጥ እንዲደረግ ሲሰሩ" የነበሩ እና "ያልተሳካላቸው" እንደሆኑም በጠቀሱ በመረጃው ላይ ሰፍሯል።
የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳልህ፤ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ባላት "በዲፕሎማሲያ ወይም ወታደራዊ ኃይል" "የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ" የማግኘት "የተሳሳተ እና ያለፈበት አባዜ ግራ መጋባቷን" ለዲፕሎማቲክ አባላቱ መግለጻቸው ተነግሯል።
ይህንን በተመለከተም፤ "ኢትዮጵያ የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የሚመለከታቸው አካላት ኢትዮጵያ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ" ኤርትራ ጥሪ እንዳቀረበችም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ከሁለት ዓመት አንጻራዊ ሰላም በኋላ እንደገና ወደ ዳግም ቀውስ ለመግባት ጫፍ ላይ ደርሷል። በትግራይ ጦርነት በአንድ ጎራ ሆነው የአዲስ አበባን መንግሥት የተዋጉት የህወሓት አመራሮች አሁን በሁለት ጎራ ተከፍለው ተፋጠዋል።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ