"በሰሜን ጎጃም ዞን ድሮንን ጨምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" bbc
https://www.bbc.com/amharic/articles/c8elz7gzg8jo በሰሜን ጎጃም ዞን ድሮንን ጨምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ 18 ጥቅምት 2024 በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ “ የመንግሥት ኃይሎች ” ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ ፈጸሟቸው በተባሉ ጥቃቶች ከ 100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። በወረዳው ዋና ከተማ ገርጨጭ ከጥቅምት 01 እስከ ጥቅምት 04/2017 ዓ . ም . በድሮን ጥቃት እና በዘፈቀደ በተፈጸሙ ጥቃቶች ህጻናትን ጨምሮ ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) ስለተፈጸሙት ግድያዎች ሪፖርቶች እንደደረሱት እና መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፋኖ ኃይሎች አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጾ፤ “53 የጽንፈኛው አባላትን ” መግደሉን አስታውቋል። አርብ ጥቅምት 01/2017 ዓ . ም . እኩለ ቀን 7 ፡ 00 አካባቢ በከተማው የሚገኘው መሀል ገነት ጤና ጣቢያ ላይ በተፈጸመ “ ተደጋጋሚ ” የድሮን ጥቃት የዘጠኝ ዓመት ህጻንን ጨምሮ ስምንት ሠዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተፈጸመው ተደጋጋሚ ጥቃት ከጤና ጣቢያው ባሻገር በአቅራቢያ የነበሩ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ገልጸዋል። “ ጢዝ የምትል ድምጽ ዓይነት አላት። አሞራ መስላ