የኢትዮ አፍሪካኒዝም ህሊና ፕ/ ማሞ ሙጭ አትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች" ይላሉ ...
„ኢትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች! ለዓለምም የመንፈስ ጸጋ የሰጠች አገር ናት!“ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፤ ተማመኑ አንተም አዳንህቸው። (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፩ ምዕራፍ ፬) ከሥርጉተ© ሥላሴ 2.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ኢትዮጵያ ካሏት ዓራት ዓይናማ ሊሂቀ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነት ከሚንገበግባቸው ጥቂት የምርምር ሊሂቀ ሊሂቃን ቤተኛም ናቸው። ችግሩ አለተጠቀምንብትም። ድህነታችን ማን ታቅፎ ይኑርልን? እኒህ እውቅ ኢትዮ አፍሪካዊ ሐዋሪያ እኛ ጥበባቸውና እና ዐውቀታዊ ክህሎታቸውን ባንጠቀምበትም ሌሎች ብልሆች ግን ከልጅነት እስከ ዕውቅት በአህጉራዊ እና በሉላዊ ጉዳዮች ላይ ሁለገብ ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በዕውቀታዊ ብቃታቸውም ተጽዕኖ ማሳረፍ የቻሉ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ በማናቸውም አገራዊ ሆነ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ፤ ያደረጉም ቅን ሊቀ ትጉሃን ናቸው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህሊናችን እና መንፈሳቸውን ግን ዕውቅና ከመስጠት በታዕቆቦ የቆዬ ቢሆንም፤ ታሪክ ግን ምንግዜም ሲያስባቸው የሚኗሩ ባለውለታችን ናቸው። የሆነ ሆኖ እኛ ባናውቅበትም አፍሪካውያን እንደ ልዩ ዓርማቸው የሚዮዋቸው፤ ልክ እንደ የቅኔው ልዑል ብላቴው ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን፤ እንደ የእግር ኳስ እስፖርት ልዑል አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አፍካዊነትን አጉልቶ በማውጣት፤ ጉልበት እንዲያገኝ በማድረግ እረገድ ድርሳን የሆኑ የአፍሪካውያን የጸሎት መጸሐፍ ናቸው። እኒህ ታላቅ ኢትዮ አፍሪአካዊ የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍናንም በልዩ ክህሎት አቅሙ በልጽጎ፤ ጎልቶ እና ጎልበቶ እንዲታይ ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ጸጋቸው ዕውቀ...