የሰማይ እና የምድር ንጉሥ እዬሱስ ክርስቶስ "#ክንፍ" አለውን? የወሮ ዝናሽ ታያቸው ውኃ ያልነካው ፈጣጣ ፈንጣጣም አስተምህሮ ሃግ ሊባል ይገባል።
የሰማይ እና የምድር ንጉሥ እዬሱስ ክርስቶስ " #ክንፍ " አለውን? የወሮ ዝናሽ ታያቸው ውኃ ያልነካው ፈጣጣ ፈንጣጣም አስተምህሮ ሃግ ሊባል ይገባል። ስለ ቃሉ ንሰኃ እገባበታለሁ አይደለም ብራና ዘርግቶ ሥንኝ ጽፎ በአደባባይ ለመዘመር ቀርቶ? #ለሚመለከተው ሁሉ። "አቤቱ ከድፍረት ኃጢያት ባርያህን ጠብቀኝ። ወደ እግዚአብሄር አምላክ ለሚቀርብ ምስጋና እንዲህ በድፍረት እና በማናአለብኝነት ተንጠራርቶ ጥሰት ውስጥ መዘፈቅ የጤና አይመስለኝም። ለነገሩ የ፬ኪሎው ቤተ መንግሥት ሽብር፤ ጭንቅ ውስጥ እንደባጀ ያመሳጥራል። ሌላላው የሰማይ እና የምድርን ፈጣሪ አማኑኤል ለእነሱ ዬግፍ ሥልጣን ብቻ ምርቃት እንዳደረገም ያሳጣል። ሥንኞቹ የባለቤታቸው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አይደሉም። ዘዬው፤ ዘኃ ግራው የሳቸው የቀዳማዊዋ እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸው ይመስላል። ምቱም በዚህው ዙሪያ ነው። ጭንቀት፤ መራድ፤ ሽብር እና ራድ ቤተመንግሥቱን መናጡን ያመሳጥራል። ለምን ፈታ ደይሊ እንደዘለለው ሥንኙን አላውቅም። የአነበበውም አሟልቶ አይደለም። አንዷ ፊደል ስትጠብቅ፤ ስትላላ ብዙ እጅግ ብዙ ጉዳዮችን ታመሳጥራለች። አማርኛ ቋንቋ ቅኔም ነው የምለውም ለዚህ ነው። ዘማሪ ዝናሽ ታያቸው አዲስ የዶግማ ፍልሰት መጥረቢያ ይዘው ከች ብለዋል። ጭብጡ እግዚአብሄር ክንፍ አለው ከሚለው አፈንጋጭ ዕምነት እና ዕሳቤ ይመነጫል። እዬገረመኝ ያለው ጉድ የኢትዮጵያ አንስት አማንያን በሃይማኖት ዙሪያ ያላቸው አሁናዊ ድፍረት ነው። ሎቱ ስብኃት። አበስኩ ገበርኩኝ። አሁን በዘመናችን ወደ አራት ተጠግተዋል። በአዲስ ፍልስፍና ፍልሰት ላይ ያሉት ማለቴ ነው። አባቶቻችንም ሃግ አይሉም። እሱ ብቻ ሳይሆን አንጡራ ጥሪታቸው ለሌላ ሃይማኖት ተቋም መጠሪያ ሲሆንም አንተ ታውቃለህ ብለው ዝም ሆኋ...