አህዱ ራዲዮ እና ዕድምታው በጥቂቱ።
አህዱ አሰገዱ። „ተግሳጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ፤ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቁጣው ፈጥና ትነዳለችና። መዝሙር ፪ ምዕራፍ ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የላቀው ሊሂቅ! · ግ ራሞተ ሰሞናቱ።፡ አህዱ በሚባል ራዲዮ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ በቀለ ገርባ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ትንሽ በትንሹ እንዬው እስቲ ብዬ አስባለሁኝ። በውይይቱ የተሻለ የመልስ መስጠት ጥበብ በአቶ ሌንጮ ለታ አይቻለሁኝ ስልታዊ እና ግልጻዊ ለመሆን ጥረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ወደ መንፈስ ለመቀረብ ማዶኛ ሆኗል - ለእኔ። ያልመድኩት ነገር የሳቸው ጉዳይ ነው። ጊዜ ያስፈልገኛል። አድማጮች ሲጠይቁ ነበር። ጠያቂዎች እና አስተያዬት ሰጪዎች አቶ ሌንጮ ለታን ከፍ አድርገው „ክቡር“ እያሉ ማቅረባቸው አቶ በቀለ ገርባን አልተመቻቸውም የመረጋጋት ሁኔታ አላዬሁባቸውም። እኔ ሁለመናን ነው የምከተታለው። ይህን ሳይ ሚሊዮኖች የሰገዱለት የአብይ ለማ ፍቅረ አክብሮት እንዴት እንዳስተናገዱት ወፌን ጠይቅኳት። ይገባል አይደል። በሁለቱ ሊሂቃንም ብዙ ሰው ነው የሚጸፈው አክብሮ። ወዶ ናፍቆ አልቆ እና .... እናማ አቶ ሌንጮ ለታን አምስገነው አድማጮች ሲናገሩ ፊድባኩን ለኩት፤ ይህን ወስጠቱን ቪዲዮውን እያዬ መገመት ነው። https://www.youtube.com/watch?v=if...