የህሊና ሪህ

የህሊና ሪህ።
„እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።“
መዝሙር ፪ ቁጥር ፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
12.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


  • መነሻ።

«እኔን እጎዳለሁ ብለህ መሃል ሰፋሪውን አድማ አስተማርክ» | አቻምየለህ ታምሩ
  • ነገረን ነገር ሲያመጣው ...

እኔ አማራ የሆንኩት አቶ አቻምየለህ ታምሩ በቪዥን ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ ተጋብዞ ጊዜ ፈጀህ ተብሎ ሁለት ደቂቃ ሲለምን እና ሌሎች ደግሞ የተሰጣቸውን ዕውቅና አክብሮት ሳይ ነበር በዛች ቅጽበት አማራነቴ ውስጤን ያሟሸው። ጥቃት አልወድም! እና ሁልጊዜ ሥሙን ሳይ የአቻምን የእኔ አማራነት የመሆን ፈቀድ ከሱ ነፍስ ጋር የተያዘዘ ስለመሆኑ አዘክረዋለሁኝ።

የአማራነቴ ሥጦታ የመጣው ከአቻም መገለል ጋር በፅኑ የተያየዘ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ እንደ አልመለስ አድርጎ ደግሞ ቅኑ የጎጃም ህዝብ በደሙ አትሞበታል። የጎጃምን የመሆን ልቅና ያዬሁበት ዘመን በዚህ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ አብዮት ዘመን ነው።  የጎጃም ህዝብ የቅኔ ጉባኤ አቅም እና ቃልኪዳን አማራነቴን የበለጠ አድምቆልኛል።  

እሰቃለሁኝ እኔ እዚህ በአማራ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ብቻ አማራነትህን ጣል ቲያትር ሲተውን። እሚሆን አይደለም። በልዩ ሁኔታ አማራኔቴ ልክ እንደ ፆታዬ ክብሬ ሆኗል። የአብይ ሌጋሲ ይልቅ ባይደክም ደስ ይለኛል።

ሥርጉተ ሥላሴ እኮ ሞገደኛ ናት። የእሷን ልብ፤ የሷን ፍቅር፤ የእሷን ታማኝነት ለማግኘት ብዙ መድከም ያስፈልጋል። እኔ ስላልኩት ሳይሆን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያውቁኝ ሰዎች ያውቁኛል። አብሬያቸው የሠራሁት እንደ ዕድል ሆኖ የ አገር አውራዎች ናቸውና። አጋጣሚዎቼም ብዙ ህብረ ቀለማት አሉባቸው። 

በልጅነትም በሥራ ዓለምም ወጣ ያሉ ፍነገጥ ያሉ ባህሪዎች ነበረቡኝ። ቤት ደግሞ አባ ዝምታ ነበርኩኝ። መልካም ሰው ደግ ሰው እዬተባልኩ ነበር ያደግኩት። ጫጫታ፤ ሁካታ ካለበት ቦታ ድርሽ አልልም ነበር። ሳምን ብቻ ነው ሎሌ ለመሆን የምፈቅደው። ሥራ ቦታ ሞገደኝነቴ ለአለቆቼም እጅግ ፈተና ነበር። ወጣት እያለሁኝ በማንኛውም ሁኔታ ለጥ ሰጥ ብዬ ተገዝቼ አላውቅም።

ለፓርቲዬ ለኢሠፓ የነበረኝ ታማኝነት እና በእኔ ሰብና ፓርቲዬን አስከብሮ መኖር ትልቁ ፍልስፍናዬ ነበር። እኔን የኮተኮቱኝ፤ ያሳደገኙ፤ የቀረጹኝ፤ ስለ እኔ ልባቸውን ሞልተው የመሰከሩልኝንም ቢሆን ለሰከንድ አንዲት ግድፈት ውስጥ ተዘፍቄ የሞያ አባቶቼን አስወቅሼ አላውቅም - በፍጹም። አይደለም ትናንት ዛሬም። ሰብዕናዬ ዝገት ነክቶት አያውቅም። ታማኝነቴ ሲጠቀጠቅ ደግሞ መለማመጥ የለም። በልባም ብልህነት ማናቸውንም ግንኙነት ላልመለሰብት ወሰኜ ማቆም። መወሰን ህይወቴ ነው። 

ሥራ ቦታ አለቃዬም ቢሆን ጉዳዬ አልነበረም። እና እኔን አማራ ለማድረግ ከቶውንም ትውልድ የማይተካቸው የፕ/ አስራት ወልደዬስ የአማራነት ፍልስፍና፤ የተከታዩ የሞረሽ ወገኔ ጥረት፤ ከዛም ያለፈው የጎንደር የአማራነት ተጋድሎ ይህልውና አብዮት አማራ ነኝ ብዬ እንድወጣ አላደረጉኝም።

ይህን ጥሶ የወጣው ጥቃት መቀበል ለማይሻው ስብዕናዬ ዕድሜ ለቪዢን ኢትዮጵያ የግለት ሂደት በአቻም ሳይ አማራነቴን እንደ ቀበል እንዳጸናውም አድርጎኛል።ከእንግዲህ በምንም ታምር ከልቤ አማራነቴን ላወጣው አልችልም። 

እርግጥ ነው ልጫነው እችላለሁኝ ራሴ ፈቅጄ። ኢትዮ አፍሪካዊነቴ አንጎሌ ስለሆነ። የሎሬቱ ሌጋሲም ነባቢቴ ስለሆነ። ከዚህ ባሻገር ግን እንደ አንድ የእድር ስምምነት አልፈልግህም አቤቶ አማራነቴ ከዛሬ ጀምሮ ብዬ ውል እማቋርጥበት ጉዳይ የለም። ሴትነተቴን እንዲህ እንደማልለው ሁሉ፤ የህዝብ አደራጅነቴን ወግድልኝ እንደማልለው ሁሉ።

እውነት ብናገር እወደዋለሁኝ አማራነቴን። አማራነቴ የነሳኝ ምንም ነገር የለም። እርግጥ ነው ጫና እንዳለበት አውቃለሁ፤ ጫነው የመጣው ደግሞ አማራነት ተፈሪነት በመሆኑ ስለሆነ ክብራችን ነው። የበታችነት አይሰማነም። ይህ ታላቁ ጸጋችን ነው።

አሁን ወደ አቶ አቻምየለህ ጹሑፍ …

„የእቴጌ“ „ እኔን እጎዳለሁ ብለህ ለመሃል ሰፋሪ አድማ አስተማርክ» የሚለው ምክር ዘመን ተሻጋሪ ነው። በዛሬው እለት በቤተ መንግሥት ዙሪያ የዚህ ዘመን መሃል ሰፋሪዎች አድማ መትተው እንደ ነበር ሰምተናል። ታሪክ ሁልጊዜ አሻራ ወይንም ጠባሳ ይተዋል። ዐቢይ አሕመድ ከአድማው በኋላ በቴሌቭዥን ቀርቦ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጎ በመናገር ከወታደሮቹ ጋር ፑሽ አፕ እየሰራ ፎቶ መነሳቱ ባይከፋም የአድመኞቹ ወታደሮች ድርጊት ግን ለሌላው ወታደር አድማ ወይንም አመጽ ማስተማሩ የማይታበይ ሃቅ ነው።“ ይላል አቶ አቻምዬለህ ታምሩ።

እኔም ትናንት ይህን አበክሬ ገልጫለሁኝ። ብቻ ጥቂት ነገር ማለትን  ወደድኩኝ ስንት ወራት አሳለፍኩኝ እኔ የራስ ተሰማ ናደው የአድማ ጠረን ቤተ መንግሥት አካባቢ እዬሸተተኝ ነው ካልኩኝ። 

ወደ አምስት ወራት ይሆነዋል። የራስ ተሰማ ናደው አድማ ለኢትዮጵያ ነቀርሳ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ነበር በአጽህኖት በተከታታይ ስጽፍ የባጀሁት።

በሌላ በኩል ዶር አብይ አህመድ ልጅ እያሱን የሚመሰል ነገር እንዳለባቸውም እንዲሁ በተለያዬ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። አሁን የአማራ የማንነት ተጋድሎ የህልውና አክቲበስት አቶ አቻምየለህ ታሪክን መሰረት አድርጎ ዘርዝር አድርጎ ጽፎታል። ጥሩ ገልፆታል። ታሪክ እሱን ይወደዋል። 

እኔ በሥም ጠቅሼ ሁሉ እቴጌ ጣይቱትን ግዞት ያስቀመጠው፤ ክብራቸውን የገፈፈው፤ የራስ ተሰማ ናደው አድማ ስለመሆኑ በአጽህኖት ነበር ስጽፍ የባጀሁት። አሁን ከትናንት በስትያ በነበረውም የአመጽ ደወልም ትዕይንት የተደገመው ያ ነበር። ለእኔ የኩዴታ ሪሄርሳል ነው።

የራስ ተሰማ ናደው የአድማ ቋጠሮ ሌጋሲ የግራው ርዕዮት ጋር አዳምሮ 50 ዓመት የኢትዮጵያን ትውልዱን ሲያባክን የኖረው። ይህ ነቀርሳ ሥር ሰደደድ ነው። ያ ፈሊጥ አቅምን በመሸርሸር እና አቅም ያላቸውን ማህበራዊ መሰረታቸውን በማናገት፤ የጸኑ፤ የተረጋጉ መንፈሶችን በማወክ የራስን ሰብዕና ከፍ ከፍ በማድረግ ነው አስተምህሮቱ።

በዬትኛውም ሁኔታ የሚከሰቱ ህውከቶች አስተምህሯቸው ከራስ ተሰማ ናደው የአድማ ሴራ እና ጥንስስ የሚያልፍ አይደለም። ቅንነት ጎድሎበት ካያችሁ ጠረኑ የራስ ተሰማ ናደው ብሂል ነው። እና ለዚህ ነው እኔ ሳያቸው ሳጠናቸው በቆዬሁት ስውር ህውከቶች ዙሪያ እማዬው የራስ ተሰማ ናደውን ሌጋሲ ለማስቀጥል የታፈነ ነገር ጠረኑ ይሸተኛል እያልኩኝ ስከትብ የባጀሁት።

የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ ዞጋዊ አይደለም የሴራ ጥንስሱ። ከዞግ ጋር ንክኪ የለውም። ግን ቤተ መንግሥት ከእኛ ውጪ ሌላ መታሰብ የለበትም ባይ ስለሆነ በምርኩዝም ቢሆን ተጋድሎው ይቀጥላል። ያው የሚጠቀለልበት ደግሞ ያ ፍደኛ ኢትዮጵያዊነት ነው። ውስጡ ግን የታመለ ነው። 
  
የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሌጋሲ ጉዳዩ ስለገባው እኔ ደስ ብሎኛል። ያ ጠረኑ እንዳለ ስለተረዱም ነው ፑሻ አፑ የተቋጠረው በዚህ በእቴጌ ጣይቱ ተደሞ የሆነው። አቶ አቻምየለህ ታምሩም ይህንኑ ነው በአጽህኖት የጻፈው እሱም ግበቶታል ማለት ነው። 

እሱ የጻፈው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከጠቀሱት ከትናንት በስትያው ሁነት ነተስቶ ነው። እኔ ግን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የውስጣቸውን አውጥተው ከመናገራቸው እጅግ ቀድሜ ከ5 ወራት በፊት ነው ከግንቦት መጨረሻ ጀምሮ የዛ ጠረን እንደ ነበረው አስባለሁኝ እያልኩኝ ስጽፍ የባጀሁት።

ዶር አብይ አህመድም ቢሆኑ ባለቀ ሰዓት ቢሆንም በቅርብ ሆነው የሚያዮቸውን ጉዳዮችን፤ የሚፋለሟቸውን ስውር እና የፊት ለፊት ውጊያዎች አስተውለው ነው ሥርጉተ ሥላሴ ግን ሩቅ ሆና ለዛውም ገድማ በተቀመጠችባት ውቢቷ ሲውዝ እና ድንግሏ ጎጆዋ ውስጥ ሆና ነው አብክራ ስታሳስብ የባጀችው።

ይህ የራስ ተሰማ ናደው የአድማ ሴራ በዬትኛውም ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። ወደፊትም ቀጣይ ነው፤ ጠንቁ ለልጅ ልጅ ተራፊ ነው። የበሽታው ምንጭ ሥልጣን ከኛ አይወጣም፤ የሥልጣን ማዕከሉ የእኛ ነው፤ ሥልጣን ከእኛ ከወጣ ውግዝ ከአርዮስ አይነት ነው። በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ይህን መሰል ውግዘት እንደ ነበር አቦው ሲናገሩ አድምጫለሁኝ።

የራስ ተሰማ ናደው ሴራ መንፈሱ ጅማ ባይታዋሩ ነው። ጅማን አይሻም። ጠ/ ሚሩ ደግሞ ከፌ ናቸው። ይህ ለራስ ተሰማ ናደው የሴራ መንፈስ መቸውንም እረፍት አይሰጠውም። መደመሩ በዕብለት የተሞሸረ ነው። ስለዚህ ህውከቱን ይቀጥላል። ህውከቱ አገር ወስጥ ያልነበረበት ጊዜ ነበር ማለት የሚቻለው በዘመነ ሃይለማርያም ደስአለኝ ጊዜ ነው።

እኔ እንደሚገባኝ ልቅና ስላላዮባቸው ይመስላል ዝምታቸው እንጂ ልቅና ካዩ እነሱ አያርፉም። እንዴት ከእኛ ውጭ ልሁቅ ሊመጣ ይችላል ባይ ናቸው። አሁን ትልቁ ራስ መርዝን የሚሆነው የዶር አብይ አህመድ ሌጋሲ ለራስ ተሰማ ናደው ህልመኞች ነው።

ቀደም ባለው ጊዜ ዘመቻውን በወበራ አስነክተውታል፤ አሁን ሰብሰብ ያሉት የስልት ለውጥ ስለደረጉ ነው። ደጋፊ መስለው ሥራና ሴራቸው ግን ቀጣይ ነው። አይራፉም። ምክንያቱም ሙሉ አቅም፤ የዳበረ ክህሎት - የማይታመን ብቃት፤ ድንቅ ችሎታ፤ ልዩ መክሊት፤ የተወዳጅነት መስህብ፤ ሙሉ ሰብዕና ለአንድ መሪ የሚያስፈልገው ሁለመና አላቸው ዶር አብይ አህመድ። 

ይህ ሁለመናነት፤ ይህ ሁለገብ ልቅና ከሁሉም በላይ ለራስ ተሰማ ናደው የሴራ ማህበረተኞች እጅግ የህሊና ሪህ ነው።

ዶር አብይ አህመድ ከወጣት የልዩ ሃይል አባላት ጋር ያደረጉት ውይይት መልካም ነው። አብሶ ፑሽ አፑ አዲስ ታሪክ ነው። ልክ አጤ ፋሲል ለአድን ወጥተው፤ መንገድ ጠፍቶባቸው መንገድ ያሳያቸውን አንድ ገበሬ በፈረሳቸው አፈናጠው/ አሳፍረው ቤተ መንግሥት ወስደው ሸልመው፤ አከብረው፤ አስከበረው እንደ ሸኙት ዓይነት ነው ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም።

በዚህ ትውፊትን፤ ትሩፋትን በመጠበቅ እረገድ ሁለቱንም አጣመረዋል፤ የደጉ ንጉሥ የአጤ ፋሲልን የዜጋን አክብሮት ብልህነት እና የእቴጌ ጣይቱን ጥበበ መክሊት ዘመን ተሻጋሪ ንጽህና የታማኝነት አስተምህሮ አጣምረው ለ21ኛው ምዕተ ዓመት አዲስ ትውፊት ጠገብ ቅርስ አዋውለዋል። ለእኔ ድርሳን ነው። 

ፑሽ አፕ አብሮ መስራት የመሪነታቸውን ጥበብ በከፍተኛ ደረጃ ያልቀዋል። የተለዬ ጣዕም፤ የተለዬ ጠረን፤ የተለዬ ተወዳጅ የሆነ የህሊና ስንቅ ነው ለእኔ። ይህ ቁጣን የማብረድ ጥበብ ውበቱ ለልጅ ልጅ ነው። ይህን መሰሉ ልዩ የሚያደርጋቸው ያልተለመዱ ክህሎቶች ሲጠፋ ነው እኔ አብዩ የት ሄዴ ብዬ ፍለጋ ላይ እምሆነው።

ያልተመ=ለመዱ ነገሮች ከአብዩ ዘንድ ሲሆኑ ጣማቸው ልዩ ነው። ይመስጣል። ራስን የመረምራል፤ መሪነት የሚበለውን ፍልስፍና ያበለጽገዋል። አሁን በዚህ መልካምነት፤ ትሁትነት፤ ቅንነት ቁጣን ገፋ አድርገው፤ ብስጭትን ገፍተረው፤ ድንጋጤን ከቁብ ሳይቆጥሩ በተረጋጋ መንፈስ ሦስት ምዕቶችን አንድ ላይ አዋደዋል። ዘመነ አጤ ፋሲልን፤ ዘመነ እቴጌ ጣይቱን፤ ዘመነ አብይን። 

መንፈሳቸው የአድማጩን የልጅ እያሱን ከሃሊንት የዋጠ ነው፤ መከፋታቸው ለመግለጽ የሄዱበት መንገድ ከብልኋዋ አስተዋይ ልዕልት ከእቴጌ ጣይቱ ጋር ያመሳስላቸዋል፤ አክብሮታዊ ትህትናቸው ደግሞ አጤ ፋሲልን ይጠራል። ብቻ የታደሉ ናቸው። እንዲዘልቅላቸው መጸለይ ያስፈልጋል።  

የሚቀራቸው ግን ይህ የመጀመሪያ ሪሄርሳል በልኩ በመጠኑ ዘመኑ በፈቀደው የህግ አግባብ እርምጃ ካልተወሰደበት አደጋው ሰፊ ነው። ትናንትም ጽፌበታለሁኝ። የመንግሥት አካላት ብቻ አድርጎ መመልከትም አይገባም። ለረጅም ጊዜ መደባቸው የጠፋን ብዙ ጹሑፎች አቋም ያለዬላቸው ዘንበል ቀና እያሉ ባጅተው አሁን ጥርት እያሉ እዬወጡ ነው። ዘመን ጥሩ ነው፤ ዘመን መስታውት ነውና።

እያደር ሲሄድ የሚጠራ ነገር ቢኖረውም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሁነቶችን የልቤ ብሎ መርምሮ አንቴናን በሁሉም መስክ አሰሳ እንዲያደርግ መፍቀድ ግድ ይላል። አቶ አቻምዬለህ ታምሩም የሚለው ይህንኑ ነው። 

እኔም እምለው ግብታዊ አይደለም። ከመሬት የተነሳ አይደለም። ተባባሪ አደራጅ አቀናጅ አካላት አሉበት። ስለሆነም ከመንግሥት አካላትም ከዛም ውጪ የሆኑ አካላት እጅ አለበት ብዬ ነው እኔ እማምነው። በቅይጡ መደመር ዝንቅንቅ መከራንም አብሮ ከች እንደሚያደርግ ማሰብ ይገባል።

ስለሆነም ህውከት ፈጣሪ ሲባል „ማንነታቸው ያልታወቀ“ እዬሉ ራስን ከማስታመመ አካባቢውን ማጥናት ያስፈልገዋል የአብይ ካቢኔ። እኔ የዶር ለማ መገርሳ እና የዶር አብይ አህመድ በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊው ደህንንት ውስጥ መስራት ለዚህ ካረዳ ለመቼ ሊሆን ነው? የዛለ ነገር ነው እኔ የማዬው።

ለዚህም ነው አማካሪ ጽኑ የሆነ መንፈስ ያለው፤ ከራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ አድማ መንፈስ ውጪ የሆኑትን ኮ/ ጎሹ ወልዴ ከፈቀዱ በአስቸኳይ አገር ገብተው ይህችን መከረኛ እናታቸውን አለዛሯን ኢትዮጵያን እንዲታደጓት በትሁት ቅንነት የጠዬቅኩት።

የሆነ ሆኖ ደወሉ ልብ ላለው ነው። ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ በደህንነት ውስጥ ያላቸውን ክህሎተ - ሙያቸውንም ተግባራዊ ለማድረግ ድካም ስለሚታይባቸው ቀበቷቸውን ጠበቅ አድርገው ኢትዮጵያን ከጥፋት ይታደጓት ዘንድ በዚህ አጋጣሚ በትህትና አሳስባለሁኝ።  

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልን።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።