ለሦስተኛ ጊዜ የሰማይ ምልክት።
እዩት እስኪ ውዶቼ። „በረድኤታችን በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲውዘርላንድ። በ2015 መግቢያ ወር ላይ ሰማይ ላይ ብዙ ሠረገላዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው አያለሁኝ። ለአንዲት መነኩሲት እህቴ ደውዬ ነገርኳት። ለቤተሰቦቼም ሲደውሉልኝ ውጪ አገር ለሚኖሩት እንዲሁ ነገርኳቸው። ከዛ የካቲት 24 ቀን እዚህ ሲዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በጀግና ሃይለመደህን አበራ አማካኝነት ካለምንም እንከን ጄኔባ አረፈ። ያው አዬር መንገዳችን ነጹሁን ሰንደቅ ተሸላሚ ስለሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ይህን ነው ያሳዬሽ ተባብለን አለፍነው። ሌላ እውነት ደግሞ ልንገራችሁ። እዚህ ሲዊዘርላንድ የ193 አገሮች ገጽ በሚመለከት አንድ ጥናት ነበር። እኔ ለካስቲንግ ተጋብዤ ተሳታፊ ነበርኩኝ። ካስቲንግ ከመሄዴ በፊት ለብሼው የምሄደውን መምረጥ ፈልግኩኝ። ጉትቻው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ተገዝቷል። ልብስ ግን ከምገዛ በቤት ውስጥ ባለው ልጠቀም ብዬ የቤቱ ሁሉ ልብስ ወጣ። መዘነጥ ዋናው ሆቢዬ ነው ከምል መደበኛ ተግባሬ ነው ከልጅነት እስከ እውቀት። እርግጥ ነው ፎቶው ከአንገት በላይ ነበር - ገጽ ብቻ ነበር የሚፈለገው። ነገር ግን ከወገብ በላይ ያለው የፊትን ገጽ የማድመቅ ድርሻ የሚኖረው ልብስ አስፈልጎኝ ነበር። የቤቱ ሁሉ ልብስ ተዘርግፎ ተሞከረ፤ ሁሉም ሊያደምቀኝ አልቻለም። መጨረሻ ላይ ቲ ሸርት ነበርኝ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያን አውጥቼ ስለብሰው ምኑን እነግራችሁዋለሁኝ ቦግ አደረገኝ። በቃ ደስ አለኝ። የሚገረመው ክረምት ላያ ስለነበር ስሄድ ደረብረብ ያለ የሚመጥን አለባባስ ነበረኝ። ስገባ ካስቲንግ ቲሙ ተመልክቶ...