ቅጣት እንዳያመጣ፤ ፈጣሪ የእውነት መስራች ነውና።
በመገፋት ላይ የሰከነ 30 ኛ የ4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መሪቆርዮስ በዓለ ሲመት አከባበር በአዲስ አባባ። „ደቀ መዛሙርቱም፤ --- የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደተጻፈ አስቡ“ ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። v በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! እንዴት ናችሁልኝ ደህና ናችሁ ወይ ውዶቼ? ዛሬ አንድ ዜና አዬሁኝ። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ባዕለ ስመትን በሚመለከት። ውስጤን ቀዘቀዘቀዘው። ብርድ ብርድ አለኝ። ለብጹዕን አባቶቻችን ውጪ አገር እኮ ቁልምጫው ከ - እስከ አይባልም ነበር። እንዲያውም አንድ ጊዜ ይህ የበዕለ ሲመት ሲዘጋጅ የሊቢያ ሰምዕታት ጉዳይ ስለነበር አልሻም ማለታቸውን አውቃለሁኝ። ንዑዱ - ብጹዑው አቡነ መሪቀርዮስን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር መዘገበ ቃላት የለውም። ለኢትዮጵያ ልዩ ምርቃት ናቸው። ለ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክስተት ናቸው። እርጋታቸው የሰማይ እና የምድር ያህል ነው። ዜናው ላይ ብጹዕ ወቅዱስ 6ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያን አቡነ ማትያስን አላዬሁኝም። ያዬኋቸው የቀድሞው ፕ/ ግርማ ወልደጊዮርጊስን አሳቸውን ነው። እሳቸው መገኘታቸው ለይምሰል ወይንም ለላንቲካ አለመሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። ቀድሞም ሲጥሩ ነበር ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ ለማድረግ፤ በጫና ብዛትም ቃላቸውን ሲያጥፉም አዳምጬ ነበር። የሆነ ሆኖ መሰረታዊ ጉዳዩ ከልባቸው ስለመሆኑ ስለማምን የተባረከ ተግባር ከውነዋል። እንዲያውም...