ተፈጥሯዊ አቀባበል።
ተፈጥሯዊ አቀባበል። „አንተ ፊቴን እሹት ባልክ ጊዜ አቤቱ ፊትህን እሻለሁ፤ ልቤ አንተን አለ።“ መዝሙር ፳፮ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ © ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 08.11.2018 · መነሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=N01J5vKDPbQ Ethiopia: የፈረንሳይ ወጣቶች “ ንግስታቸዉን ” ብርቱካን ሚደቅሳ በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋታል !! ዛሬ ክብርት ዳኝ ብርቱካን ሜዲቅሳ ኢትዮጵያ ገብታለች። የመንግሥት አቀባልን ፎተውን አይቸዋለሁኝ። እኔ የመሰጠኝ ግን የወጣቶቹ ልዩ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል ስለሆነ ትንሽ ልልት ወደደኩኝ። ባጋጣሚው አንዳፍታንም ላመስግን ለቅንብሩ ጥራት ሙሉውን ተከታትዬዋለሁኝ። ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ውስጧን አቅሟን ጥረቷን በቅንነት ለማበርከት አገር እንደገባች አምናለሁኝ። እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ የጥጋናዊ ለወጡን በመደገፍ፤ በማገዝ፤ በማበረታት ጥንካሬ በመስጠት ላይ እንደምትተጋም አስባለሁኝ አምናለሁኝ። ለረጅም ጊዜ በአካል እንዲህ ልናያት ባለመፈቅዷ ብከፋባትም ዛሬ ሳያት ግን ሰውነቷም መንፈሷም ሙሉ መሆኑን ለመመልከት ችያለሁኝ። የሆነ ሆኖ ዛሬ በነበረው የጀግኖቹ የፈንሳይ ለጋሲዮን ኢትዮጵያዊ አንበሶች የአቀባባል ዝግጅት ላይ ቁምነገሩ ተፈጠሯዊ መሆኑ ነው ቀልቤን ስቦት ብዕሬን እንዳነሳ ያደረገኝ። በነገራችን ላይ በድምጽ እማውቃቸውን ወላጅ እናቷን መኪና ውስጥ ወ/ሮ አልማዝን በጨረፍታ ለማዬት በመቻሌ እንኳን ለዚህ አበቃቸው ማለትን እሻለሁ...